ዜና ዜና

የሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ አቶ አህመድ ሽዴን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

አቶ አህመድ ሽዴ የሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።
የሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ሶዴፓ) እያካሄደ ባለው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሊቀ መንበሩን እና ምክትል ሊቀ ምነበሩን መርጧል።
በዚህም አቶ አህመድ ሽዴ ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ዑመር ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው
ተመርጠዋል።
ይህ በእንዲ እንዳለ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጅግጅጋ ገብተዋል።
ጅግጅጋ ሲደረሱም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ/ሶዴፓ/ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ መዝጊያ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ
ይጠበቃል።