Back

የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል

የኦሮሞ ህዝብ የአስተዳደር ስርዓት የሆነው የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ በከተማችን አዲስ አበባ ከህዳር 19 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የዩኔስኮ ኮንፈረንስ በአገራችን የዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማንም ሳይጀምር አስቀድሞ ይተገብር የነበረው የገዳ ስርዓትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከወከሉት ባሻገር የሌሎች አገር ተወካዮችም ጭምር ስለስርዓቱ ምንነት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡   
በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት የተመዘገበው የኦሮሞ ህዝብ የአስተዳደር ስርዓት የሆነው የገዳ ስርዓት ካሉት በርካታ እሴቶች መካከል ለእርቀ ሰላም ያለው ቦታ ከፍተኛ መሆኑ  ነው፡፡ በስርዓቱ በህብረሰተቡ ውስጥ በሚከሰቱ ግጭቶች የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ሌሎች ችግሮችን እንዳያስከትል የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በተጋጩት ወገኖች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ይደረጋል፡፡
ከነዚህ መንገዶች መካከል የጉማ ስርዓት አንዱ ነው፡፡ ጉማ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው ከሟች ወገኖች ጋር እርቀ ሰላም የሚያወርድበት መንገድ ነው፡፡ በእርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች አማካይነት በሚደረገው በዚህ በጉማ ስርዓት የሚከፈለው የደም ካሳ የሟችን ህይወት ይተካል ተብሎ ታስቦ ሳይሆን በህዝቡ መካከል የነበረው የአብሮነት እሴት እንድጎለብትና ሀዝቡን ከእርስ በርስ እልቂት ለማዳን የሚደረግ የእርቀ ሰላም ሂደት ነው፡፡ ይህ ስርዓት የራሱ ህግና አተገባበር ያለው ሲሆን ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎችም እርቀ ሰላምን ለማውረድ የሚያገለግል ስርዓት ነው፡፡
ሌላው በገዳ ስርዓት ውስጥ ጸብን ለማራቅና እርቀ ሰለምን ለማውረድ የሚደረገው ጥረት በክበር መሳሪያዎች አማካይነት የሚከናወን ሲሆን ‹‹ቦኩ›› ወይም ‹‹በትረ መንግስት››፣ከለቻና ጫጩ እንዲሁም በሲንቄ አማካይነት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡
"ቦኩ" (በትረ መንግስት) በገዳ ስርዓት ውስጥ አባ ገዳዎች የሚይዙት በትር ሲሆን በህብረተሰቡ ውስጥ አለመረጋጋትና ግጭት ሲከሰት የሰው ህይወት እንደይጠፋ ህዝቡን ለማረጋጋት የሚያገለግል የክብር መሰሪያ ነው፡፡ በስርዓቱ መሰረት ግጭት በተከሰተበት ቦታ ላይ በመሄድ አባ ቡኩ/አባ ገዳ/ ‹‹ቡኩውን›› በመያዝ በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ ያደርጋል፡፡ ይህ ካልተሳካ አባ ቦኩው በትሩን ከመሬት በማጋጨት ተራግሞ ሲለሚሄድ እርቀ ሰላሙን ላለመቀበል የሚደፍር አይኖርም፡፡
እንደ ቦኩ ሁሉ ከለቻ አባገዳዎች በግንባራቸው ላይ የሚያስሩት የክብር እቃ ሲሆን ጫጩ ደግሞ ከጉማሬ ቆዳ የተሰራና በዛጎል/ጨሌ/ ያጌጠ ባህላዊ የክብር እቃና የአባ ገዳው ባለቤት በእጇ የምትይዘው ነው፡፡ በጎሳዎች መካከል ግጭት ሲፈጠር ሁለቱን የክብር እቃዎች ይዘው በመሄድ በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቀ ሰላም እንድወርድ ይደረጋል፡፡ የግጭቱ መንስኤ ውስብስብም ቢሆን ጉዳዩ በሌላ ጊዜ እንዲታይ ተደርጎ ሁለቱም ወገኖች በሰላም ይለያያሉ፡፡ ከለቻና ጫጩም ከእርቅ ሰላሙ በኋላ በክብር ወደ ቤት ይመለሳሉ፡፡
ሲንቄ (የሴቶች የክብር በትር) በገዳ ሰርዓት ውስጥ ትልቅ ስፋራ ከላቸው የክብር መሰሪያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ለሴት ልጅ በጋብቻዋ እለት ከእናቷ የሚለገስላት የክብር በትር ነው፡፡ ይህም በሴትነቷ የሚደርስባትን ተጽእኖ የምትካለከልበትና መብቷን የምትሳስከበርበት እንዲሁም ግጭት በተቀሰቀሰ ጊዜም እርቀ ሰላም ለማውረድ የሚያገለግል ነው፡፡ አንድ አባወራ በባለቤቱ ላይ ጥቃት ከፈጸመ ሴቶች ሲንቄያቸውን ይዘው በመውጣት ድርጊቱን በመቃወም ከተጎጂዋ ሴት ጎን ይቆማሉ፡፡ በዚህን ጊዜም አባገዳዎች ጥፋተኛውን አባ ወራ ቀጥተው፤ መክረው እንዲሁም ቃል አስገብተው ከቤተሰቦቹ ጋር በሰላም እንድኖር የሚደረግበት ስርዓት ነው፡፡
ከዚህም በሻገር በጎሳዎች መካከል ግጭት በተፈጠረ ጊዜ ሴቶች ሲንቄያቸውን ይዘው ሁለቱ ወገኖች እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ የሚጠይቁበት ስርዓትም የገዳ ስርዓት አካል ነው፡፡ ሁለቱ ወገኖች የሴቶችን ተማጽኖ ሳይቀበሉ ከቀሩ ሴቶቹ ወደ ቤት አይመለሱም፡፡ በዚህም ልጆችና ከብቶች ሊጎዱ ስለሚችሉ እርቀ ሰላም ወርዶ ሴቶች ወደ ቤታቸው እዲመለሱ ለማድረግ አባገዳዎች ለሴቶቹ ተማጽኖ አጋርነታቸውን በመሳየት የተጋጩት ወገኖች እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ያደርጋሉ፡፡ ሲንቄ የሴቶች ክብር መገለጫ በመሆኑ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ስነስርዓቶች በሚከናወኑበት ወቅት ሴቶች ይይዙታል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።