Back

በዓሉ የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል እሴቶች ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

11ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ቀን "ሕገ መንግስታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን!" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል የተለያዩ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበትበሀረር ከተማ አው አባድር ስታዲየም  በመከበር ላይ ነው፡፡  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ ደሳለኝ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል መከበር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
 ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል እሴቶች ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል፡፡  የሀገሪቱ ዜጎች ዋነኛ ጠላት የሆነውን ድህነት ለማስወገድ እና የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ አሁንም ርብርቡ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የሀገሪቱ ሁሉም ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለታሪኳ፣ ባህሏ እና ገናናነቷ አስተዋፅኦ ያደረጉባት ጥንታዊ ሀገር ናት ያሉት አቶ ኃይለማርያም፥ ኢትዮጵያውያን የቀደሙ የተዛቡ ግንኙነቶችን በማደስ መልካም እሴቶችን፣ የጋራ እቅዶች እና አመለካከቶችን ለማክበር የገቡትን ቃል በተግባር እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተጋን ነው፤ ሀገሪቱ በአፍሪካም ሆነ በአለም ተሰሚነቷ እንዲጎለብት የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በሁሉም ዜጋ ዘንድ በጥልቀት መስረፅ ይኖርበታል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው ሁሉ የጋራ የሆነ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ማንነት አላቸው፤ በዚህ በመመራትም እጅግ ፈተኛ በሆነው የአለም ሁኔታ ውስጥ ሀገሪቱ በድል ጎዳና እንድትገሰግስ ሁሉም ወገናዊ ሀላፊነት ተሸክሟልም ነው ያሉት።
የሀገሪቱ ዜጎች ዋነኛ ጠላት የሆነውን ድህነት ለማስወገድ እና የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ አሁንም ርብርቡ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የባለፉት 15 አመታት ሀገራዊ የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች በህዝቡ ተሳትፎ እና ውጤታማነት በአለም ቀዳሚ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከዚህ ፈጣን እድገትም ህዝቡ ደረጃ በደረጃ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን አብራርተዋል።
የተመዘገቡት አስደናቂ ለውጦች ብሩህ የተስፋ ፋና ከመፈንጠቅ ባሻገር የህዝቡን ተጨማሪ የእድገት ጥማት መቀስቀሱንም ነው የገለጹት።
መንግስትም ይህን የህዝብ የማያቋርጥ የእድገት ፍላጎት ለማርካት ከህዝቡ ጋር በመሆን በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል።
በህዝብ ይሁኝታ ያገኘው መንግስት ባለፉት አመታት ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ ቢችልም ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል ዝንባሌዎች ታይተዋል።
በጥቂቶች ዘንድም የህዝበ እና የምንግስት ሀብትን አለአግባብ ለራስ ብልፅግና መጠቀም፣ ብልሹ አሰራሮች እና ሙስና መንፀባረቃቸው ታይቷል ብለዋል።
ባለፉት አመታት የሁሉንም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢከናወኑም ህብረ ብሄራዊነትን የማያስተናግዱ የጠባብነት እና ትምክህት አስተሳሰቦች በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ማድረሳቸውንም ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ያስመዘገበችውን አሰደናቂ እድገት ለማጎልበት እና የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ለማስወገድ በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትም አሳስበዋል።
የተሃድሶ ንቅናቄው በመሪው ኢህአዴግ እና አባል ድርጅቶቹ ተጀምሮ ህብረተሰባዊ የለውጥ እና የተሃድሶ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል ነው ያሉት።
የአስተሳሰብ እና የተግባር ጉድለቶችን ለማረም እንዲሁም ህብረተሰቡ የሚማረርባቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በጥልቅ የመታደስ ንቅናቄው ወሳኝ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የተሃድሶ ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን መላው ኢትዮጵያዊ የነቃ እና የማያቋርጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል። በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያሱት።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የፌዴራል ስርዓቱ ሁሉንም ፍላጎቶች ማስተናገድ የሚችል ነው!

እነአሜሪካና ስዊዘርላንድ ፌዴራላዊ ስርዓትን ተቀብለው መተግበር ከጀመሩ ምዕተ አመት አስቆጥረዋል። እንደተባለው ስርዓቱ ሀገርን አደጋ ውስጥ የሚጥልና አንድነትን የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካም ሆነ ስዊዘርላንድ የሚባሉ አገራትን ላናይ እንችል ነበር። አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1789 በህገመንግስት የተረጋገጠ ፌደራላዊ ስርዓትን በሀገሯ ላይ እውን አድርጋለች። ስዊዘርላንድ ደግሞ እ.ኤ.አ በ1848 ስርዓቱን በህገመንግስቷ እውቅና ሰጥታ ዘርግታለች። ጀርመንም እ.ኤ.አ.በ1871 ፌዴራላዊ መንግስትን ይፋ አድርጋለች። በመቀጠልም ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተለያዩ ግዛቶች፣ ቼኮስሎቫኪያ፣ ከኮሚኒዝም መፈራረስ በኋላ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ወደ ፌዴራል ስርዓት በሂደት እንደተቀላቀሉ የዘርፉ ምሁራን ከጻፏቸው ሰነዶች መረዳት ይቻላል።

ብርቅዬው ግድባችንን ከዳር ማድረስ-አማራጭ የሌለው ጉዳይ…!

ከስምንት ዓመታት በፊት መላ ኢትዮጵያውንን ቀልብ የሳበ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ፡፡ የአባይ ወንዝ ጥቅም ላይ አለመዋል በቁጭት ሲንገበገቡ የነበሩ መላው ኢትዮጵያውን ደስታቸው ወደር አጣ፡፡ ፕሮጀክቱ

ከ‹‹እኔ ብቻ›› ስሜት መሻገር ይገባል!!

በመደመር እሳቤ የጀመርነው ሁሉን አቀፍ አገራዊ ለውጥ እንደ ንብ ታታሪ ሆኖ በመስራት ለውጡን ዳር ማድረስ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው፡፡ በእኛነት ስሜት በመደራጀት በአገራችን ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በጋራ በመታገል ዛሬ የደረስንበት ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ተችሏል፡፡ በተባበረ አንድነታችን ያቀነቀንለት የለውጥ ዝማሬ አልፎ አልፎ አንዳንድ መሰናክሎች እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በቁልቁለት መንገድ ለማስገባት ከኋላ የሚገፉ ከፊት የሚስቡ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሯራጡ ሃይሎች እዚም እዚያም ይስተዋላሉ፡፡ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ኋላ ለመመለስ በርካታ ወጥመዶች እየዘረጉ ይገኛሉ፡፡ በብሄሮች መካከል ያለውን ልዩነት በማጉላት በሕዝቦች መካከል ጭቅጭቅና ንትርክ ለመፍጠር የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ በበርካታ ውጣውረድ ታልፎ የተገኘውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በሠለጠነ እና በሰከነ መንገድ በመፍታት የዴሞክራሲ ባህላችንንም ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

Visitorcounter Visitorcounter

Today       

530

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1120

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

9367

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

236973

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

364964

       አጠቃላይ ጎብኚ