Back

በህዳሴው ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙ መደነቃቀፎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጂ የሚያደርጉ በመሆናቸው በንቃት ሊታገልዋቸው እንደሚገባ ተገለጸ

በሀገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ፈተናዎችና መደነቃቀፎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጂ የሚያደርጉ በመሆናቸው ሴቶች መብታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስከበር በጽናት ሊታገሉ እንደሚገባ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ጓዲት ሙፈርያት ካሚል ገለጹ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ነው፡፡
የሊጉን ስብሰባ ዛሬ በተጀመረበት ወቅት ዋና ሊቀምነበሯ እንደተናገሩት ሊጉ የ15 ዓመታት የተሃድሶ እንቅስቃሴ በሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ላይ ያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ በስፋት ይመክራል፡፡ መሪ ድርጅት ኢህአዴግ መንግስትን እየመራ ባለፉት 15 ዓመታት በርካታ ለውጦችን ማስመዝገቡን ገልጸው በሂደቱ ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ቀርበው ወይይት እንደሚደረግባቸውም ነው የተናገሩት፡፡
እንደ ሊቀመንበሯ ገላጻ ባለፉት የተሃድሶ ዓመታት ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኮች ያላቸው ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህ ሴቶችን በስፋት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ነው የሚገልጹት፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ሂደት የታዩ ጉድለቶች የሉም ማለት እንዳልሆነም ይናገራሉ፡፡
ባለፉት 15 ዓመታት ልማቱን በማፋጠንና ዴሞክራሲውን ጥልቀት እንዲኖረው በማድረግ በኩል የሴቶች ሚና ምን ይመስል እንደነበር ማየት እንደሚገባ ጠቁመው በአሁኑ በተሃድሰው ጉዞ ላይ እያጋጠሙ ያሉ መደነቃቀፎችና መሰናክሎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጆ የሚያደርጉ በመሆናቸው ሴቶች አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን ለማክሸፍ በንቃት ሊታገሉ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
አጠቃላይ ልማትና ኡንዲስትራላይዜሽን በምስፋን የሴቶችን የኑሮ ጫና መቀነስ እንደሚቻል አመልክተው እስከታችኛው የሊጉ መዋቅር ያሉ ሴቶችና እዲሁም በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ሴቶች የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት መፋጠን የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በአግባቡ ተግንዝበው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የሉጉ አባላት በጽሁፍ በቀረበው የስራ አስፈጻሚው ሪፖርት ላይ ሰፊ ወይይት በማድረግ የተላያዩ አቅጣጫዎች ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።