Back

11ኛውን የብሄሮ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በዓል ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል

ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በድምቀት ለማክበር  የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የፌዴሬሽን ምክር  ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ ገለጹ፡፡  የበዓሉ አዘጋጅ የሆነው የሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዓሉ ህዳር 29ቀን 2009 ዓም ለማክበር ዝግጅቱን ማጠናቀቀንም ነው የገጹት፡፡
በዓሉ "ህገ መንግስታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሲያችን" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር አመልክተው መሪ ቃሉ ህገ መንግስቱ በኢትዮጵያ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነት እውን ከሆነ ወዲህ በሁሉም መስኮች ፈጣን ለውጥ በማቀጣጠል የህዳሴ ጉዞውን ለማሳካት እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚገልጽ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ቀደም ካሉ ዓመታት ጀምሮ በዓሉ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ተገናኝተው ከመመካከርና ተመክሮ ከመለዋወጥ ባሻገር በልማት ታጅቦ እየተከበረ መሆኑን ያስታወሱት አፈ ጉባኤው በሃረሪ ክልልም በተመሳሳይ መልኩ ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችሉ የመሰረተ ልማቶችን መገንባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብዙኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ ባለመቻሏ ምክንያት ሰላምና ዕድገት አጥታ የኃልዮሽ ጉዞ ስትጓዝ እንደነበር የተናገሩት አቶ አባተ ህዝቦች በትግላቸው ባረጋገጡት መብት ለብዙኃነታቸው ዕውቅና የሰጠ የቃል ኪዳን ሰነድ የሆነውን ህገ መንግስት አጸድቀው ራሳቸው በራሳቸው እያስታደሩና  እያለሙ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት፡፡ ህገ መንግስቱና ተከትሎ ተግባራዊ የተደረገው የፌደራሊዝም ስርዓት ኢትዮጵያ ከነበረችበት ችግር ወጥታ በፈጣን ለውጥ ውስጥ እንድትገባ ማድረጉንም ነው የተናገሩት፡፡
እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ በዓሉ ጸረ ሰላም ኃይሎች ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመናድ የብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ነጻነት ለመንጠቅ ጥረት ባደረጉት ማግስት የሚከበር ሲሆን የሃረሪ ክልል ህዝቦችም ሆነ የሌሎች ክልሎች ህዝቦች በእልህና በቁጭት በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡  ሌሎች ክልሎች አዘጋጁን የሃረሪ ክልል ህዝብና መንግስት የበዓሉን ዝግጅት ለማሳካት እያደረገው ላለው ጥረት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የበዓሉ ማጠናቅያ ህዳር 29ቀን 2009 ዓም በሃረሪ ክልል መካሄዱ ቀደም ባሉ ቀናት በተለያዩ ኣካባቢዎች እንደሚከበርም አቶ ያለው ተናግረዋል፡፡ የብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በዓል በየዓመቱ  ህገ መግስቱ በጸደቀበት ህዳር 29 ቀን እንደሚከበር ይታወሳል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል። በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያሱት።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የፌዴራል ስርዓቱ ሁሉንም ፍላጎቶች ማስተናገድ የሚችል ነው!

እነአሜሪካና ስዊዘርላንድ ፌዴራላዊ ስርዓትን ተቀብለው መተግበር ከጀመሩ ምዕተ አመት አስቆጥረዋል። እንደተባለው ስርዓቱ ሀገርን አደጋ ውስጥ የሚጥልና አንድነትን የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካም ሆነ ስዊዘርላንድ የሚባሉ አገራትን ላናይ እንችል ነበር። አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1789 በህገመንግስት የተረጋገጠ ፌደራላዊ ስርዓትን በሀገሯ ላይ እውን አድርጋለች። ስዊዘርላንድ ደግሞ እ.ኤ.አ በ1848 ስርዓቱን በህገመንግስቷ እውቅና ሰጥታ ዘርግታለች። ጀርመንም እ.ኤ.አ.በ1871 ፌዴራላዊ መንግስትን ይፋ አድርጋለች። በመቀጠልም ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተለያዩ ግዛቶች፣ ቼኮስሎቫኪያ፣ ከኮሚኒዝም መፈራረስ በኋላ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ወደ ፌዴራል ስርዓት በሂደት እንደተቀላቀሉ የዘርፉ ምሁራን ከጻፏቸው ሰነዶች መረዳት ይቻላል።

ብርቅዬው ግድባችንን ከዳር ማድረስ-አማራጭ የሌለው ጉዳይ…!

ከስምንት ዓመታት በፊት መላ ኢትዮጵያውንን ቀልብ የሳበ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ፡፡ የአባይ ወንዝ ጥቅም ላይ አለመዋል በቁጭት ሲንገበገቡ የነበሩ መላው ኢትዮጵያውን ደስታቸው ወደር አጣ፡፡ ፕሮጀክቱ

ከ‹‹እኔ ብቻ›› ስሜት መሻገር ይገባል!!

በመደመር እሳቤ የጀመርነው ሁሉን አቀፍ አገራዊ ለውጥ እንደ ንብ ታታሪ ሆኖ በመስራት ለውጡን ዳር ማድረስ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው፡፡ በእኛነት ስሜት በመደራጀት በአገራችን ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በጋራ በመታገል ዛሬ የደረስንበት ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ተችሏል፡፡ በተባበረ አንድነታችን ያቀነቀንለት የለውጥ ዝማሬ አልፎ አልፎ አንዳንድ መሰናክሎች እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በቁልቁለት መንገድ ለማስገባት ከኋላ የሚገፉ ከፊት የሚስቡ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሯራጡ ሃይሎች እዚም እዚያም ይስተዋላሉ፡፡ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ኋላ ለመመለስ በርካታ ወጥመዶች እየዘረጉ ይገኛሉ፡፡ በብሄሮች መካከል ያለውን ልዩነት በማጉላት በሕዝቦች መካከል ጭቅጭቅና ንትርክ ለመፍጠር የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ በበርካታ ውጣውረድ ታልፎ የተገኘውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በሠለጠነ እና በሰከነ መንገድ በመፍታት የዴሞክራሲ ባህላችንንም ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

Visitorcounter Visitorcounter

Today       

554

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1120

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

9391

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

236997

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

364988

       አጠቃላይ ጎብኚ