መጣጥፎች መጣጥፎች

በደማቅ ቀለም የተጻፈ ታሪክ

ታክሲ ውስጥ ነኝ፣ አንድ የኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓም በኢትዮጵያ ታሪክ ስለተከሰተው ሁኔታ እየተረከ ነው፡፡ አዎ ይህቺ ቀን በታሪክ በየዓመቱ ትዘከራለች፡፡ ከግንቦት ወር 1983 ዓም ቀደም ብለው የነበሩ ዓመታት በኢትዮጵያ ከጦርነት ውጭ ሌላ የሚሰማ መልካም ዜና አልነበራቸውም፡፡ ዘወትር ሁካታ ግርግር የማይለይባት አዲስ አበባ በወርሃ ግንቦት 83 ዓም ትካዜ ገብቶባታል፡፡ ነዋሪቿ ስለቀጣዩ ሁኔታ መገመት የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ አንዳንዶቹ ለወራት የሚሆን ስንቅ ማዘጋጀታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ለብዙኃነት መከበር ፈር የቀደደ ፌዴራላዊ ስርዓት

የአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአገራቸው ባይተዋር ተደርገው ይቆጠሩበት የነበረው ያ ከእሬት የመረረ ዘመን ላይመለስ ከተቀበረ ሁለት አስርት ዓመታት አለፉ፡፡ የቁርጥ ቀን ልጆች በከፈሉት መሪር መስዋዕትነት ከእኔ ዘመን ወደ እኛ ዘመን ከተሸጋገርን፤ በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ስር ሆነን በጋራ መትመም ከጀመርን 26 ዓመታት ተቆጥሩ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም የጦርነት ታሪኳ ላይመለስ ወደ መቃብር ተወርወሯል፤ የህዳሴ ዘመንም ተበስሯል፡፡

የጋራ መግባባት የፈጠረ ግድብ

በተፈጥሮ ፀጋዋ የታደለችና የአለም የጥንት ስልጣኔ መነሻና የሰው ልጅ መገኛ ሃገር-ኢትዮጵያ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የገፀ-ምድሯ አቀማመጥ ሲታይ ተራራ እና ስምጥ ሸለቆ የበዛባት ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ የብዙ ሃይቆችና እንደ አባይ፣ ተከዜና ባሮ የመሳሰሉት አገር አቋራጭ ወንዞች ምንጭና መነሻም ናት፡፡ በሰንሰላታማና የሚማርኩ ተራሮች፤ በበርካታ የዱር እንስሳትና አእዋፋት የበለፀገች ባለፀጋ ሃገር ናት-ኢትዮጵያ፡፡

እንደ ንስር ራሱን የሚያድስ ተራመጅ ድርጅት

በሀገራችን የሚከናወኑ ማንቸውም ተግባራት በሁሉም ዜጎች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ማሳደራቸው የማይቀር ነው፡፡ ይህን ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሀገር ስታድግ የሚደሰት፤ ስትታመም የሚታመም፤ በክፉ ስተነካ የሚኮሰኩሰው በጥቅሉ ለአገሩ መፃኢ እድል ማማር ሌት ተቀን የሚተጋ ቅን ዜጋ ሁሉ በአገሩ የሚከወኑ ሁለንተናዊ ተግባራትን በንቃት መከታተሉ አይቀሬ ነውና የኢህአዴግ የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት ጉዳይም የበርካቶቻችሁ መነጋጋሪያ አጀንዳ እንደነበረ መገመት አያዳግትም፡፡

ለተሻለ ውጤት የጋራ ጥረት

"በኤፊ ሰውነት" ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ ፋና ወጊ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በአገራችን አሁን እየተተገበሩ ያሉት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችም አገር በቀልና ውስጣችንን ያገናዘቡ መሆናቸው ከነተግዳሮታችንም ቢሆን በለውጥ ውስጥ...