መጣጥፎች መጣጥፎች

ኢሕአዴግ ደምቆ ለመታየት የቀደሙ መንግስታትን አቧራ ማልበስ አያሻውም!

"በኤፊ ሰውነት" በግል ከሌሎች ሰዎች ጋር በማደርገው ውይይትና በአንዳንድ አጋጣሚዎች በተሳተፍኩባቸው የውይይት መድረኮች ላይ ኢሕአዴግ ለምን ራሱን ካለፉት ስርዓቶች ጋር ያነፃፅራል? የሚል ጥያቄ ሲነሳ እሰማለሁ፡፡ የጥያቄው መነሻ የተለያየ ገፅታ ያለው የመሆኑን ያክል የጠያቂዎቹም ፍላጎት (motive)...

ህግ መንግስታችን የብሩህ ጉዟችን ዋስትና

የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ የሆነውን ህገ መንግስት ከጸደቀ 22 ዓመታትን ተቆጠሩ፡፡ ህገ መንግሰቱ የዘመናት የህዝቦች ጥያቄ በመመለስ አገሪቱን ወደ አዲስ ተስፋና ምዕራፍ አሸጋግሯል፡፡ ህገ መንግስቱ የጸደቀበት ቀን ምክንያት በማድረግ ህዳር 29 ቀን የብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በዓል ሆኖ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ ዘንድሮም ‹‹ህገ መንግስታችን ለዴሞክራሲዊ አንድነታችንና ለህዳሲያችን›› በሚል መሪ ኃሳብ ለ11ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

የገባውን ቃል የማያጥፍ ህዝባዊ ድርጅት!

"በኤፊ ሰውነት" በመኖሪያ ቤታችን፣ በስራ ቦታችን አልያም ደግሞ በትራንስፖርት ላይ፤ ብቻ በያገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ሁላችንም እናወራበታለን፣ እንመካከርበታለንም፡፡ በአቅማችን ይሄ ቢሆን ያ ቢሆን ስንልም ሃሳበችንን እንሰነዝራለን፡፡ ካሳለፍነው ዓመት መጨረሻ የተጀመረው የኢህአዴግና ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና...

ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ህዳሴ!

"በኤፊ ሰውነት" ካሳለፍነው ዓመት መጨረሻ አካበቢ ጀምሮ እስካሁን ባሉት ጊዜያት ኢህአዴግና ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙንን እንቅፋቶች በማሰወገድ አገራችንን ወደ ፊት ለማራማድ የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ናቸው፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች በተፈጠረው አለመረጋጋት ለዘመናት የገነባናቸውን የጋራ እሴቶቻችንን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይህ ክስተት ኢህአዴግ ከመላው የአገራችን ህዝቦች ጋር በጋራ በመሆን ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ካስመዘገባቸው ስኬቶች አንፃርም ይሁን አገራችንን በሩቅ ለማድረስ ከተቀመጠው ራዕይ አንፃር ሲመዘን ጎታችና የአገራችንን የህዳሴ ጉዞ ሊያሰናክል የሚችል በመሆኑ ጉዳዩን በአግባቡ መርምሮ ሁነኛ መፍትሔ የማስቀመጡ ሁኔታ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡

የለውጥ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው

"በኤፊ ሰውነት" ባሳለፍነው ሳምንት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በቀጣይ አገሪቷን የመምራትና የህዝባችንን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል የአመራር ብቃትና ክህሎት ያላቸውን የካቢኔ አባላት ሹመት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ የካቢኔ ሹመት ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በአንድ በኩል ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የነበረውን አለመረጋጋትና የህዝብ ፍላጎት መነሻ በማድረግ ህዝቡ በተለያየ መንገድ ያነሳ የነበራቸውን ቅሬታዎች መፈታት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር በሌላ በኩል ደግሞ የሀገራችንን የህዳሴ ጉዞ እውን ለማድረግ ድርጅታችን በየጊዜው እየጎለበተ የመጣውን የሀገራችንን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ዕድገት የሚመጥን አጠቃላይ ፖለቲካዊ ቁመና መገንባት የግድ የሚልበት ሁኔታ እየተፈጠረ መምጣቱን በመገንዘብ እንደገና በጥልቀት መታደስ እንዳለበት በማመን ሰፊና ዝርዝር ግምገማ ካካሄደ በኋላ የወሰደው የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡