መጣጥፎች መጣጥፎች

ሰላምና መረጋጋትን እያሰፈነ ያለ አዋጅ

"በክሩቤል መርሃጻድቅ" በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች በርከት ላሉ ወራት በቀጠለው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ግጭቱ በተከሰተባቸው   አካባቢዎች ሰላማዊ ኑሮ  ተናግቷል፡፡  ዜጎች በሰላም ገብተው በሰላም የመመለሳቸው ጉዳይ አመኔታ...

ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ

"ከኤፊ ሰውነት" ኢትዮጵያውያና በዓለም ታሪክ ምናልባትም ማንም ህዝብ ሆኖት ወይም ኖሮት በማያውቀው የታሪክ ሂደት ውስጥ አልፈናል፡፡ አገራችን በከፍታ ዘመን የነበረችበት ዘመን በአገራችን የታሪክ ምዕራፍ ሁሌም ሲታወስ የሚኖር የታሪካችን አንዱ ገፅታ ነው፡፡ ከዚህ የከፍታ ማማ ላይ ወደ ታች ቁልቁል መውረድ የጀመርንበት ያ! ዘመንም ሌላው የታሪካችን አካል ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ተቃራኒ የታሪክ ውጣ ውረደች ውስጥ ያለፈችው አገራችን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የቁልቁለት ጉዞዋን ገትታ ወደ ከፍታ ማማ በምትሸጋገርበት በማያቋርጥ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ገብታ ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በመልካም ገፅታውም ሆነ ለማስታወስ እንኳን በሚከብደው አስከፊ ፈተናና ውጣ ውረድ ያለፍን ህዝቦች ነን፡፡ ይሄ ደግሞ ለህዝባችን በአፈ ታሪክ ተነግሮት ሳይሆን ኖሮት ያለፈው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

የጋራ ውይይት ለስኬታማ የትምህርት ዘመን

"ክሩቤል መርሃጻድቅ" በኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በትምህርት መስክ አንጸባራቂ ድሎችን ተጎናጽፏል፡፡ ይህ ድል ኢህአዴግ ትምህርት ለሁለንተናዊ ልማት ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በመገንዘብ ለመስኩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የተገኘ ውጤት ነው፡፡ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተያዘው ሀገራዊ ግብ መሰረትም በሁሉም አካባቢዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስፋፋት ተችሏል፡፡ ቀደም ባሉት ስርዓቶች በከተሞች ብቻ ተወስነው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ኢህአዴግ በወሰደው ቆራጥ ውሳኔ አሁን አሁን ወደሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ተዳርሰዋል፡፡

በዳግም ተሃድሷችን ለህዝብ የገባውን በጥልቀት የመታደስና ዴሞክራሲያችንን የማስፋት ቃል ሳነሸራርፍ እንተገብራለን።

በድርጅታችን የመጀመሪያ ተሃድሶ ወቅት በውስጣችን የተፈጠረውን መከፋፈልና የጥገኛ ዝግጠት በዴሞክራሲያዊ አካሄድ በመፍታትና ራሱን በራሱ በማረም ከቀደመ ጥንካሬውም በላቀ ቁመና መቆም የቻለ ድርጅት መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ከተሃድሶው በኋላም በአገራችን አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን፣ ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥና ሁለንተናዊ ውስጥ እንድንገባ ያስቻለንን አቅጣጫ ነድፎና ይህንኑ መስመር በመከተል ላለፉት 15 ዓመታት በርካታ ድሎችን አስመዝግቧል።

በሰላማዊና በሰከነ ሁኔታ መወያየት የችግሮች ሁሉ ሁነኛ መፍቻ ነው

ህዝባችን ላለፉት 25 ዓመታት በመንግስት በኩል የሚታዩ ችግሮችንና መፈታት የሚገባቸው ጉዳዮችን በማመላከት መንግስትንና የመንግስት ኃላፊዎችንም ጭምር የማረምና የማስተማር አለፍ ሲሉም የማጋለጥ ተግባር ሲፈፅም እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ ህዝባችን በሚፈልገውና በሚጠብቀው ሁኔታ ምላሽ ከመስጠት አኳይ ያሉ መጓተቶች ዋጋ እያስከፈሉ በመሆናቸው መታረም እንደሚገባቸው ኢህአዴግ በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለፀ መጥቷል፡፡ በተለይ መንግስታዊ ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል ዝንባሌ አጥፊ መሆኑን ኢህአዴግ በጥልቀት በመገምገም ለህዝባችን ቅሬታ መንስኤ በሆኑት ጉዳዮች ላይ አፋጣኝና ስር ነቀል እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ የማያሻማ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በዚህም ከየአቅጣጫው እየተነሱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችም መነሻቸው ምንም ይሁን ምን መፍታት እንደሚገባ ኢህአዴግ ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጦ ለተግባራዊነቱ እየተረባረበ ይገኛል፡፡ እናም ድርጅቱ ዛሬም እንደትናንቱ ከህዝባዊ ባህሪው በመነሳት ችግሮቹን ከህዝብ አኳያ እየመዘነ የሚፈታ ጠንካር አቋም ያለው ድርጅት መሆኑ ያለፉት ዓመታት ተግባራቱ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡