መጣጥፎች መጣጥፎች

ጊዜ የማያደበዝዘው የእኛነታችን እውነታ!!

አንድ እውነት አለ ሁሌም ደጋግመው ቢናገሩለት ለማድመጥ የማይሰለች፡፡ አንድ እውነት አለ ሁሌም ስለሱ ብትዘምርለት ለጆሮህ የማይከረክር፤ጊዜ የማይሽረው፤ ሴራ የማያደበዝዘው፡፡ ያ እውነት ለእኔ ኢትዮጵያ በአለም ታሪክ አኩሪ ስም ይዛ፤ የአፍሪካ ኩራት ሆኗ የኖረች ታላቅ ሀገር የመሆኗ እውነት ነው፡፡

ጀግኒት! ከማጀት እስከ አደባባይ

ከጥንት ከጠዋቱ የአገር ምሰሶ የቤት አለኝታ ሴት ናት፡፡ በባህልና ወግ ተጠፍንጋም ሴት ለቤቷ መሰረት ናት፡፡ ትዳር አጋሯን ጨምሮ ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም ልጆቿን እንደአመላቸው አቅፋ ለወግ የምታበቃው ሴት ናት፡፡ የሴቶች ሁሉ ቁንጮ የሆኑት እቴጌ ጣይቱን ጨምሮ አገራችን በወጣቻቸው እና በወረደቻቸው አባጣ ጎርባጣዎች ሁሉ የአገራችን ሴቶች ግምባር ቀድም ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

በታሪካዊ ምዕራፍ ውስጥ የተካሄደ ታሪካዊ ጉባዔ

ሰሞኑን የበርካቶች ቀልብ ሀዋሳ ላይ ነበር፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የውጭ ሀገራት ልዑካን ወዘተ ሀዋሳ ላይ ከትመዋል፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የመገናኛ ብዙኃንም የብዝኃነት ተምሳሌት በሆነው በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ ቀድመው ተገኝተዋል፡፡

እድሉን እንጠቀምበት

ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ካካሄደ በኋላ ባለፉት ጥቂት ወራት የለውጥ ጅማሮዎች ታይተዋል፡፡ በአመራር ለውጡ ወቅት የተነገሩትን ቃላት በድርጊት ለመመንዘር ቀን ቀንን እስኪተካ መጠበቅ ሳያስፈልግ በየቀኑ ከሚታሰበው እና ከተለመደው በተለየ መልኩ ሁነቶች ተበራክተው፤ አዳዲስ ክስተቶች ተነባብረው ግርምት እና ስለ መጪው ጊዜ ተስፋን ጭሯል፡፡

ቁርኝታችን ዳግም ታድሷል

ከምንለያይባቸው ይልቅ የሚያመሳስሉን ይበዛሉ፤ ከሚያራርቁን ይልቅ የሚያቆራኙን ይገዝፋሉ፡፡ ባህል፤ ቋንቋ እና ኃይማኖትን የምንጋራ፤ ሀዘን እና ደስታን በጋራ የምንካፈል፤ ድንበር ቀርቶ አጥር የማይለያየን ቤተሰብ፤ ጎረቤት፤ አብሮ አደግ ነን፡፡ በደም እና አጥንት የተሳሰረን በሁለት ሀገራት፤ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የምንኖር አንድ ህዝብ፡፡