ትኩስ ዜና

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡ ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ/ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ኢህአዴግ በአጋርነት ለመስራት የሚመርጡት በሳል ህዝባዊ ፓርቲ 10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ትናንት ነሓሴ 22ቀን 2007 ዓም በመቐለ ከተማ ሲጀመር የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጉት ንግግር 10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል፡፡ ጉባኤው ሰፋፊ አቅጣጫዎችንና የእቅድ ግብአቶችን እንደሚያስቀምጥ ተገለፀ

ጉባኤ ጉባኤ

Back

ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት ተገለፀ፡፡

የለውጡ ቀጣይት ለአማራ ሕዝቦች ተጠቃነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት; በሚል መሪ ቃል የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር ባስተላለፉት መልእክት ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት አመላክተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ብአዴን ያጋጠሙትን ፈተናዎች በተለመደው ጽናቱ እያለፋቸው ወደ ተሻለ ምእራፍ መነሻ እያደረገ ዛሬም ድረስ መቀጠሉን ጠቅሰዋል፡፡ ብአዴን ለአማራውና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል መነሻ በመሆን ክፉውንም በጎውንም በትእግስት፣ በአስተዋይነትና በጥበብ በማለፍ ለአሁኑ ለውጥ የበቃ አንጋፋ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ብአዴን ከእህት ድርጅቶችና አጋር በመሆን አገር ችግር በገጠማት ገዜ ከራስና ድርጅት በላይ ሕዝብና አገርን ለማዳን አስቀድሞ የሚያይ የካበተ ልምድ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስትጀመር አብረን ጀምረናል፤ ስትሰራ ሰርተናል፤ ስትሰለጥን ሰልጥነናል፤ ስታሸንፍ አሸንፈናል፤ በዘመናት በተለያዩ ችግሮች ስትወድቅ አብረን ወድቀናል፤ ከቁልቁለት ጉዞ ለመውጣት ተስፋ ሰንቃ ስትነሳ አብረን በተስፋ ተነስተናልም ብለዋል ። ይህችን አገር ወደ ገናናነቷና ክብሯ ለመመለስ ለድህነትና ኃላቀርነት ጋር በምናደርገው ትንቅንቅ የለውጥ ተስፋ ፍንጣቂዎችን ማየት ችለናል ብለዋል በመልእክታቸው፡፡

በሀገሪቱ በሁለት ፅንፈኛ ሀይሎች መካከል በተወጠረ ፖለቲካ ውስጥ እንደምትገኝ እና ሁሉን የደፈጠጠና የጨፈለቀ ልሙጥ ሀገራዊ ማንነት ብቻ አንግቦ ጠቅላይና አሃዳዊ አመለካከት የኢትዮጵያን መልከ ብዙ እውነታ በካደ ደረጃ የቆመ ፅንፍ በአንድ በኩል፥ በሌላ በኩል ደግሞ ብሄረሰባዊ ማንነትን ከሌሎች መነጠያና ማግለያ ያደረገና ፅንፈኛ ብሄርተኛ በሚቀነቀንበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል አቶ ደመቀ ።

በዚህ በሰለጠነ ዘመን አካሄዳችን በኃይል አስገዳጅ ከመሆን ይልቅ በሃሳብ ልዕልና አስረጂና አሳማኝ መሆን ይኖርብታል፤እያንዳንዱ ወቅትና ዘመን አርበኝነትንም ይጠይቃል ብለዋል ፡፡ ለዚህ ትውልድ የ"አርበኝነት" ብያኔ ድህነትን ከልብ መጠየፍ እና በልማት ድል መንሳት እንደሆነ ተናግረዋል።

የአማራ ሕዝብ ራሱን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እኩል የሚያይና ራሱን ከልክ በላይ የማወደስ ማንነት የሚሸከም ትከሻ እንደሌለውም ገልጸዋል፡፡ ብዙ ወጣ ውረዶችን አሳልፍን የምናካሄደው 12 ድርጅታዊ ጉባኤ የመጣንበትን መንገድ በጥልቀት በመገምገም በማስተዋል የምንማርበትና የቀጣይ አቅጣጣጫ የምናስቀምጥበት ይሆናል ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን ፡፡

ጉባኤው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችንም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡