ትኩስ ዜና

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል። ግዴታዬን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ጓድ መለስ አለሙ የሚመራው የድርጅታችን የልኡካን ቡድን የቻይና ጉብኝት እንደቀጠለ ነው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ30 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር የኢትዮጵያን የለውጥ ምዕራፍ በተመለከተ ዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሄዱ ነው:: በጓድ አቶ መለሰ አለሙ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ሚኒስትር የተመራ የልኡካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው። አብሮነት፣ መቻቻልና ሰላም ታላቅ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነትን ልዩ ልዩ ፀጋዎች እያሳየን፣ እያከበርንና እየጠበቅን የምናከብረው በዓል ነው - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ 13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በአዲስ አበባ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጽህፈት ቤቱ ተልዕከውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል፡፡ “የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

ጉባኤ ጉባኤ

Back

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤ ላይ የእለቱ የክብር እንግዶች የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁም የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሀላፊ ጓድ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

"በተጠናከረ የወጣቶች ትግል የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ወደፊት" በሚል መሪ ቃል በአሉ በመከበር ላይ ሲሆን የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሃላፊ ጓ ብናልፍ አንዷለም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጓድ ብናልፍ በንግግራቸው ላይ የወጣቶች ሊግም ሆነ ሌሎች የወጣቶች አደረጃጀቶች ሚና በራሱ በአደረጃጀቱ ውስጥ ባሉ አባላት ብቻ ታጥሮ የሚቆም መሆን እንደሌለበት እና ከሊጉ አደረጃጀት ውጪ የሚገኙ ወጣቶችንም ፍላጎት ያጠና እና ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም እንደ ሀገር ለመጣው ለውጥ የወጣቶች ሚና የጎላ እንደነበር እና በቀጣይም እንደ ድርጅት ወጣቶች የተሰዉለትን ለውጥ በመጠበቅ እና ለውጡ የታሰበለትን አላማ እንዲመታ ለማድረግ ሁሉም ሀላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር እና የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር ጓድ ሚሊዮን ማቲዎስ በመክፈቻ ንግግራቸው ድርጅታችን ኢህአዴግ እንደ ሀገር መሪነት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያስመዘገባቸውን መልካም አስተዋፆዎችን በመጠበቅ፡ሃሳቦችን በምክንያታዊነት በመሞገት ወጣቶች ለውጡ የፈጠረላቸውን አጋጣሚ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡

 


ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

836

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

5826

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

43848

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

196006

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

300580

       አጠቃላይ ጎብኚ