ትኩስ ዜና

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል። ግዴታዬን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ጓድ መለስ አለሙ የሚመራው የድርጅታችን የልኡካን ቡድን የቻይና ጉብኝት እንደቀጠለ ነው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ30 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር የኢትዮጵያን የለውጥ ምዕራፍ በተመለከተ ዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሄዱ ነው:: በጓድ አቶ መለሰ አለሙ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ሚኒስትር የተመራ የልኡካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው። አብሮነት፣ መቻቻልና ሰላም ታላቅ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነትን ልዩ ልዩ ፀጋዎች እያሳየን፣ እያከበርንና እየጠበቅን የምናከብረው በዓል ነው - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ 13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በአዲስ አበባ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጽህፈት ቤቱ ተልዕከውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል፡፡ “የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

ጉባኤ ጉባኤ

Back

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ የብድር ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ በማድረግ የበጀት ጉድለትን በማስተካከል ያከናወነችው ተግባር ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት በአማካይ አስከ 14 በመቶ ሆኖ የቆየውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር የመንግስት ፕሮጀክት በጀትንና ባንኮች የሚሰጡትን ብድር በመቀነስ እንደዚሁም በሥራ ላይ ያሉ የተለያዩ የልማት ውጥኖች ኢኮኖሚውን ለተጨማሪ ወጪ እንዳይዳርጉ ለማድረግ በፍጥነት የሚጠናቀቁበትን መንገድ በማመቻቸትና መሰል እርምጃዎች በመሰዳቸው ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት የግሽበቱ መጠን 10 ነጥብ 3 በመቶ መውረዱን ጠቅሰዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን በተለይም ደግሞ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት በኢትዮጵያ ከመዋቅር ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን የምጣኔ ኃብት ችግር መከላከል እንደሚቻልም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡  

ጠቅላይ ሚንስትሩ በመንግስት ከፍተኛ ወጪ ወደአገር ውስጥ የሚገቡትን ስንዴንና ዘይትን የመሳሰሉ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት የንግድ ሚዛኑን ማስጠበቅና ምጣኔ ሃብቱን ከጉዳት መታደግ እንደሚቻል በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰፋፊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ዘርፉን ማዘመን አንዱ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል። 

የዴሞክራሲ ስርዓቱን በማጎልበት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ በተሰራው ስራ ውጤቶች መገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ምህዳሩ ቢሰፋም በዚህም የረጅም ርቀት ለመሮጥ ትንፋሽ የሚያጥራቸው ፓርቲዎች እንዳሉ አመላክተዋል። ዶር አብይ 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በመግለፅ የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ ወደ አገር ውስጥ የገቡ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አብዛኛዎቹ ዴሞክራሲ በሀገሪቱ እንዲሰፍን እየሰሩ መሆኑን በመጠቆም ከገቡት መካከል ጉራማይሌ የሆነ ባህሪ ያላቸው መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት አንድነቷን፣ ሰላሟን እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀሳብ ያለው ፓርቲ መሆኑን በመግለፅ ፓርቲዎቹ ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ሰላሟን የሚያረጋግጥ ሀሳብ ማፍለቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡  

በሌላ አጀንዳ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ ለመመለስ እንደሚሰራ ዶር አብይ አህመድ ለምክር ቤት አባላቱ አብራርተዋል። የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥ ይኖርበታልም ብለዋል። መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑን በመጠቀስ በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በማብራሪያቸው አመላክተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ዶር አብይ አሕመድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎችም የማንም ፖለቲካ ኃይል ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ እራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ግለሰቦችን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት አስተያየትም ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ መንግስት ወንጀለኛ መሆኑን መንግስት ካወጀ በኋላ ያልታሰረ ግለሰብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ የጊዜ ነገር እንጂ ወንጀል ሰርቶ ተሸሽጎ የሚቀር እንደማይኖርም አስገንዝበዋል፡፡

 


ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

862

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

5826

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

43874

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

196032

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

300606

       አጠቃላይ ጎብኚ