ጉባኤ ጉባኤ

Back

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ መልካም አስተዳደርን በተመለከተ ባደረገው ጥልቅ ውይይት ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አመራሩ በቁርጠኝነት  ለመፍታት የሚያስችለውን አቅጠጫ አስቀመጠ፡፡

በጉባኤው ላይ እንደተገለፀው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር በቁርጠኝነት መስራት አለበት፡፡ ችግሩን ለመፍታት የውስጠ ድርጅት ትግልን ማጠናከር እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ አደረጃጀቶችና የሚድያ ተቋማት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ትግል የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ  ለማድረግ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

ችግሩን ለመፈታት  ድርጅትና መንግስት ከሚያደርጉት ጠንካራ ትግል በተጨማሪ ህዝቡ የችግሩ የመፍትሄ አካል ለማድረግ ጠያቂና ምክንያታዊ ማህበረ ሰብ ለመፍጠር መረባረብ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታት የህዝቡ ተሳታፊነትና ቁርጠኝነት ምቹ ሁኔታ መሆኑን ያስገነዘቡት የኢህአዴግ ሊቀመንበር ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ ‹‹ይህን ሞጋችና በምክነያት የሚደገፍና የሚቃወም ሚዛናዊ ህዝብ ይዘን የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደረጃ አደረጃ በጊዜ የለኝም መንፈስ እልባት መስጠት ይገባል›› ብለዋል፡፡

የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ለይደር የሚቀመጥና በለዎሳስ የሚያዝ ባለመሆኑ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚሰራበት መሆኑን በጉባኤ ተሰምሮበታል፡፡

‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ኃሳብ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አሁንም በዛሬው ውለው በማክሮ ኢኮኖሚ፣ የመሰረት ልማትና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የመከረ ሲሆን በነገው ዕለት የኢዲትና ቁጥጥር ሪፖርት እንዲሁም የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀ መንበር በመምረጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡