Back

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

"የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የሊጉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ መኖር ለሀገራዊ ለውጡ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የተገፀ ሲሆን ኢህአዴግ በሴቶች ዙሪያ እያደረገው ላለው እንቅስቃሴ ጉባኤው ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆን ተጠቅሷል።

የጉባኤውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበሯ ጓዲት ሙፈሪያት ካሚል ላለፉት 2 አመት ተኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ከባድ ትግል መደረጉን እና በአሁን ሰአት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን ጠቅሰው እንደ ሀገር የሚታዩ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንዲቻል ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

"ህዝብ እንደ ህዝብ ሊጣላ አይችልም ከፍቅር ውጪ የሚያውቀው አጀንዳ የለውም" ያሉት  የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 'የሚያጋጥሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን ቆም ብሎ በሰከነ መንገድ ራስን ማየት እና ከችግሩ ጋር ባለመደራደር ከችግር ተላቆ ወደ ፊት በመገስገሰ ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር ይገባል' ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ አሁን እየተካሄደ ባለው ለውጥ በአንድ በኩል ተስፋ በሌላ በኩል ጠንካራ ትግል የሚጠይቅ ፈታኝ ሁኔታዎች እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ያወሱት ወ/ሮ ሙፈርህያት የሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪ ለሰላም የቀረበ በመሆኑ ሴቶች ሁለተኛ የሚባል አማራጭ እንደሌለ ተገንዝበው ለሰላም መምጣት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

''የጥላቻ መርዝ ስካር እየሆነ በመጣበት በአሁኑ ወቅት አንዳችን ወደ ሌላችን ጣታችንን መቀሰር ትተን ወደ ራሳችን ከተመለከትን አሳሳቢ ቢሆንም የማንሻገረው ችግር የለም'' ሲሉም ተናግረዋል።

በጉባኤው በክብር እንግድነት የተገኙት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ሴቶች ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ እንዲከበር ሰላማዊ ትግል ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ትልቅ መስዋትነት የተከፈለበት ህገ መንግስታችንን ለማፍረስ ከውስጥም ከውጪም እየተደረገ ያለውን ዘመቻ በተግባር የተረጋገጡትን የሴቶች መብቶችና ጥቅሞች የሚንዱና የሚጎዱ በመሆኑ ልክ እንዳለፈው አኩሪ ታሪካችሁ ትክክለኛውን መስመር በመያዝና ህዝቡን በማሰለፍ የመልካም አስተዳደርና የልማት ችግሮችን ለመፍታት ዝግጁነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል። ጉባኤውም አንደ ድርጅት ጉልበት የሚሆኑ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ያላቸው ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ለ 3 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል። መድረኩ እንደ ድርጅት ለሴቶች የተሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ የሚያስቀጥል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው ጉባኤውን የሚመሩ የፕሬዚዲየም አባላትን በማስመረጥ የዛሬ ውሎ የተጠናቀቀ ሲሆን በነገው እለትም በሊጉ ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡  

 

 


ጉባኤ ጉባኤ

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባኤ ወጣት አስፋው ተክሌን የሊጉ ሊቀመንበር ወጣት አክሊሉ ታደሰን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መረጠ፡፡ አመራሮቹ ሊጉን ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል የሚመሩ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤ ላይ የእለቱ የክብር እንግዶች የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁም የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሀላፊ ጓድ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡

በኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ከጥር 19-21 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሀዋሣ ከተማ ያካሂዳል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዘጋጅ ኮሚቴው ቃል አቀባይ ወጣት ጫላ ኦሊቃ የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጉባዔው ከእናት ድርጅቱ ጉባኤ ማግስትና ሀገሪቱ በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቀሴ ባለችበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ታሪካዊና ልዩ ያደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

429

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1125

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

46433

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

203632

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

308349

       አጠቃላይ ጎብኚ