Back

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ የብድር ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ በማድረግ የበጀት ጉድለትን በማስተካከል ያከናወነችው ተግባር ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት በአማካይ አስከ 14 በመቶ ሆኖ የቆየውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር የመንግስት ፕሮጀክት በጀትንና ባንኮች የሚሰጡትን ብድር በመቀነስ እንደዚሁም በሥራ ላይ ያሉ የተለያዩ የልማት ውጥኖች ኢኮኖሚውን ለተጨማሪ ወጪ እንዳይዳርጉ ለማድረግ በፍጥነት የሚጠናቀቁበትን መንገድ በማመቻቸትና መሰል እርምጃዎች በመሰዳቸው ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት የግሽበቱ መጠን 10 ነጥብ 3 በመቶ መውረዱን ጠቅሰዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን በተለይም ደግሞ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት በኢትዮጵያ ከመዋቅር ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን የምጣኔ ኃብት ችግር መከላከል እንደሚቻልም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡  

ጠቅላይ ሚንስትሩ በመንግስት ከፍተኛ ወጪ ወደአገር ውስጥ የሚገቡትን ስንዴንና ዘይትን የመሳሰሉ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት የንግድ ሚዛኑን ማስጠበቅና ምጣኔ ሃብቱን ከጉዳት መታደግ እንደሚቻል በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰፋፊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ዘርፉን ማዘመን አንዱ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል። 

የዴሞክራሲ ስርዓቱን በማጎልበት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ በተሰራው ስራ ውጤቶች መገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ምህዳሩ ቢሰፋም በዚህም የረጅም ርቀት ለመሮጥ ትንፋሽ የሚያጥራቸው ፓርቲዎች እንዳሉ አመላክተዋል። ዶር አብይ 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በመግለፅ የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ ወደ አገር ውስጥ የገቡ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አብዛኛዎቹ ዴሞክራሲ በሀገሪቱ እንዲሰፍን እየሰሩ መሆኑን በመጠቆም ከገቡት መካከል ጉራማይሌ የሆነ ባህሪ ያላቸው መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት አንድነቷን፣ ሰላሟን እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀሳብ ያለው ፓርቲ መሆኑን በመግለፅ ፓርቲዎቹ ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ሰላሟን የሚያረጋግጥ ሀሳብ ማፍለቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡  

በሌላ አጀንዳ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ ለመመለስ እንደሚሰራ ዶር አብይ አህመድ ለምክር ቤት አባላቱ አብራርተዋል። የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥ ይኖርበታልም ብለዋል። መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑን በመጠቀስ በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በማብራሪያቸው አመላክተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ዶር አብይ አሕመድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎችም የማንም ፖለቲካ ኃይል ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ እራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ግለሰቦችን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት አስተያየትም ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ መንግስት ወንጀለኛ መሆኑን መንግስት ካወጀ በኋላ ያልታሰረ ግለሰብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ የጊዜ ነገር እንጂ ወንጀል ሰርቶ ተሸሽጎ የሚቀር እንደማይኖርም አስገንዝበዋል፡፡

 


ጉባኤ ጉባኤ

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣትና ጨለማውን ሊያበራው የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችዋን አፍሪካንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ጨለማውንም ለማብራት መሠረታዊ ነገር እውቀት ነው ፤ የትምህርት ዕድሉን አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ተማሪዎችም ይህንን በመገንዘብ ራሳቸውን ከውሸካና ከአሉባልታዎች በማራቅ ከትምህርት መልስ ለአገሪቷ ብርሃን ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡

በደርጅቱ ውስጥ የነበረ ጸረ ዴሞክራሲያዊነት መገንገን፣ የክራይ ሰብሳቢነት ፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት የያዘ ስለነበረ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማጥፋት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ተስኖት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከውስጥም ከውጭም አገሪቱ የመፍረስ አደጋ እንደተደቀነባት ሲተነበይ አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ሳቢያ አገሪቱን ከገባችበት አደጋ መታደግ የሚችል ትግል በድርጅቱ ውስጥ መካሄድ መጀመሩንና ጠንካራ ውሳኔ መወሰኑን የጠቀሱት አቶ ተፈራ ውሳኔውንም "ከሞላ ጎደል ለአብዮት የተቃረበ የሪፎረም ውሳኔ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ሊቀ መንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኦዲፒ 29ኛ ዓመት የምስረታ ባስተላለፉት መልዕክት የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል። ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅርፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ «ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ

ተጨማሪ ያንብቡ…

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 13 results.