Back

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከ2008 እስከ 2010 ባሉት ሶስት ዓመታት ዓመታዊ እድገቱ ከነበረበት 10.1 በመቶ ወደ 8.6 በመቶ ዝቅ ማለቱን እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገቱ እየተቀዛቀዘ መምጣቱንም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ገምግሟል። እየተመዘገበ ያለው የመዋቅራዊ ለውጥም አዝጋሚ መሆኑን ገምግሟል። በአገራችን ባለፉት ዓመታት በተፈጠረው አለመረጋጋት የተነሳም የውጭና የአገር ውስጥ ኢንቨስትመንት መቀዛቀዙን ነው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የገመገመው።

የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ በማስፈን የዋጋ ንረትን በነጠላ አሃዝ የመገደብ አጠቃላይ ግብ ከ2003 እስከ 2010 ባሉት ዓመታት የተሳካ እንዳልነበረ የገመገመው ኮሚቴው በ2010 በጀት ዓመት መጨረሻ በአገሪቱ ባለው አለመረጋጋትና የውጭ ምነዛሬ ቅነሳ የዋጋ ንረቱ 13.1 በመቶ መድረሱን አስቀምጧል።

ባለፉት ዓመታት በአጠቃላይ በአገራችን ተግባራዊ የተደረገው የልማት ፋይናንስ ሞዴል በብድር ላይ የተመሰረተ መሆኑና የፋይናንስ አቅርቦት የተመደበላቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች የፕሮጀክት አስተዳደር ብቃት ማነስ ኢኮኖሚውን ችግር ውስጥ እንደከተተው ገምግሟል። በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚወሰዱና አጭር የመክፈያና የችሮታ ጊዜ ያላቸው ብድሮች የአገሪቱን የውጭ ብድር ጫና እንዲገዝፍ በማድረጋቸው ላልተወሰን ጊዜ እንዲቋረጡ መደረጉን ጠቁሟል።

ኮሚቴው ሀገራችን ያጋጠሟትን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን እና ሀገራዊ ለውጡ ያስገኛቸውን መልካም እድሎች በዝርዝር ከፈተሸ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

ለሁለንተናዊ እንቅስቃሴያችን የሰላም መስፈን፣ ፍትህ፣ መልካም አስተዳደርና ሰብዓዊ መብት መከበር መሰረት መሆናቸውን ያወሳው ኮሚቴው ባለፉት ወራት የአገራችንን ህዝቦች ለቅሬታ የዳረጉ በርካታ ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸው ህዝቡ ወደ ልማት በመመለስ በተሻለ የለውጥ መንፈስ ለመስራት የሚያግዝ ምቹ ሁኔታ መሆኑን አመልክቷል።

አገራችን በዓለም አቀፍም ሆነ በአህጉራዊ ደረጃ ያላት ተሰሚነትና ተቀባይነት ማደጉ ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ለመፍታት እንደ መልካም አጋጣሚ የሚያግዝ መሆኑንንም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ገምግሟል።

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን በአገራችን የልማት አጀንዳ ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ መቻሉ፣ ህብረተሰባችንም በአገራችን የፖለቲካና የልማት እንቅስቃሴ ላይ ያለው ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለማለፍ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥሩ ናቸው ብሏል ኮሚቴው። በመሆኑም እነዚህን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ያለፉ ስህተቶችን በማረምና በተሻለ ግልፅነትና ተጠያቂነት መንፈስ ስራዎችን በማከናወን ውጤታማ ልማትን ማስቀጠል እንደሚገባ አስምሮበታል።

የመንግስትን ወጪ ውጤታማና ከገቢው ጋር የተቀራረበና የተገደበ ማድረግ፣ የታክስ ገቢን ማሳደግ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ ብድር አቅርቦትን ላለመሻማት ለበጀት ጉድለት ማሟያ መንግስት ከባንክ የሚበደረው ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው 3 በመቶ እንዳይበልጥ ገደብ መደረጉንም ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለማሻሻል የንግድና የስራ ፈጠራን ማሳለጥ ማሻሻያ ፕሮግራም ተነድፎ ስራው መጀመሩን ጠቅሷል። የስራ እድል በሁሉም የልማት ዘርፍና በሁሉም የልማት ተዋናዮች የሚፈጠር ቢሆንም ስራውን በባለቤትነት የሚመራና የሁሉንም ተዋናዮች ሚና የሚያስተባብር ኮሚሽን መቋቋሙን ጠቅሷል።

የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች በአገራችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በተደራጀ መልኩ ተሳታፊ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲመቻች መደረጉንም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ጠቅሷል። የኢኮኖሚ ሴክተሮችን የሚያነቃቁ እርምጃዎች መውሰድ፣ ብክነትና የአመራር ዝርክርክነት የሚታይባቸውን የመንግስትን የልማት ድርጅቶችን ማስተካከል ባለፉት 12 ወራት ከተወሰዱት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መካከል መሆናቸውን አስገንዝቧል።

ስራ አስፈፃሚው በማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት፣ የፊሲካል ፖሊሲና የውጭ ንግድ ቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቅሷል። የኢኮኖሚ እድገቱ ከጥራት አኳያ ያሉበትን ጉድለቶች በዝርዝር አጥንቶ የሪፎርም እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የታክስ አሰባሰብን ማዘመን፣ የግብር ግዴታቸውን በማይወጡ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፣ የኮንትሮባንድ ንግድን ከምንጩ ማድረቅ፣ የዕዳ ጫናቸው ከፍተኛ የሆኑ ብድሮችን ማገድ፣ ቀድሞ የተወሰዱ ብድሮችን የእዳ ክፍያ ጊዜ ማሸጋሸግ በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አስታውቋል። የውጭን ንግድን በዓይነት በብዛትና በጥራት ማሳደግም ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው።

የግብርናው ዘርፍ ሌላው የትኩረትና ርብርብ ማዕከል መሆኑን በማንሳት አነስተኛና ሰፋፊ የመስኖ ልማት፣ የግብርና ግብዓት ፋይናንስ አቅርቦት፣ እንስሳት እርባታ ምርታማነት፣ የግብርና አመራረት ዘዴን ማሻሻል፣ ድህረ ምርትን ብክነት መቀነስ፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ የምግብ ዋስትና ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ፣ የተፈጥሮ ሃብት አጠባበቅ የሁሉንም ትኩረትና ተሳትፎ አግኝቶ ተግባራዊ  እንዲደረጉ ይሰራል ብሏል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው። በእነዚህ ማሻሻያዎች መነሻነትም በአጭር ጊዜ ስንዴን፣ የቢራ ገብስን፣ የምግብ ዘይትና ጥሬ እቃዎችን ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ማድረግ ይገባል ብሏል። ማዕድን ምርት፣ ማኑፋክቸሪንግ እና የቱሪዝም ዘርፍም በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ናቸው።

መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ የሚገባበት አግባብ ላይ የተለየ ዲስፕሊን መከተል፣ ሁሉንም የኢኮኖሚ ተዋናዮች በእኩል የሚያሳትፍ፣ ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት የውድደር ሜዳን መዘርጋት በቀጣይ ከሚወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ መሆኖቸውን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አስቀምጧል።

የሀገር ውስጥ የስራ ፈጠራንም ሆነ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት መሰረት ልማትን በተለይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መሰረት ያደረጉ የኢኮኖሚ እርምጃዎች ይወሰዳሉ። ነፃ የሰው ሃይል ዝውውር፣ የሲቪክ ማህበራት ተሳትፎ፣ የኢንቨስትመንት ከባቢያዊ ሁኔታን ማሻሻል ሪፎርሙ ትኩረት ከሚያደርግባቸው መስኮች ተጠቃሽ ናቸው።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቀጣይ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ መደረሱን የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት አስታውቋል።


ጉባኤ ጉባኤ

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የ28ኛውን የግንቦት ሀያ በዓልን አከበሩ

የበዓሉ መርሃግብር በጽዳት ስራ የተጀመረ ሲሆን በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና ርዕዬተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ጓድ መለሰ ዓለሙ ግንቦት ሀያ በሀገራችን ለተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ፈር ቀዳጅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

“በኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባዎች የመሳተፍ ዕድላችን መስፋት በክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንድንወያይ አስችሎናል ” አጋር ፓርቲዎች

የድርጅቶቹ አመራሮች ላለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባን አስመልክቶ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ወክለው መግለጫውን የሰጡት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አደም ፋራህ፣ የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ወክለው በመወከል ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ፣ አቶ አሻድሊ ሃሰን የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንትና የቤንሻንጉል ጉምዝ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ወክለው የፓርቲው ሊቀ መንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡመድ ኡጁሉና የሀረሪ ብሄራዊ ሊግን በመወከል ደግሞ የሊጉ ሊቀ መንበርና የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳነት አቶ ኦርዲን በድሪ ናቸው፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ያለፉትን ወራት የእቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ።

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከሚያዚያ 7 - 8 /2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ሀገራዊ የለውጥ ሂደቱ ያለበትን ደረጃና የተከናወኑ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎችን አፈፃፀም ገምግሟል። ባለፈው አንድ አመት በተለይም 11ኛው የኢሕአዴግ ጉባኤ ከተካሄደበት መስከረም ወር ጀምሮ የጉባዔውን ዋናዋና ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች መሰረት በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ያስቻሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ምክር ቤቱ በዝርዝር ተመልክቷል። የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አኳያ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መኖራቸውን፤ እህት እና አጋር ፓርቲዎች እያደረጓቸው ያሉ እንቅስቃሴዎች በመልካም ጅምርነት የገመገመው ምክር ቤቱ በቅርቡ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተፈረመው የቃል ኪዳን ሰነድ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ቦታ ያለው እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ኢህአዴግ የቃል ኪዳን ሰነዱን አክብሮ በመንቀሳቀስ ሃላፊነቱን በተሟላ መልኩ እንዲወጣ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ህገ መንግስቱን፤ የሀገሪቱን ህጎች አክብረው በሰላማዊ የሀሳብ ትግል ብቻ በመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ ውስጥ ያለባቸውን ሃላፊነት ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪውን አስተላልፏል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ም/ቤት ከፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 7ቀን 2011 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ተገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ ያለፉት ወራት የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊና ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡

በደርጅቱ ውስጥ የነበረ ጸረ ዴሞክራሲያዊነት መገንገን፣ የክራይ ሰብሳቢነት ፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት የያዘ ስለነበረ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማጥፋት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ተስኖት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከውስጥም ከውጭም አገሪቱ የመፍረስ አደጋ እንደተደቀነባት ሲተነበይ አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ሳቢያ አገሪቱን ከገባችበት አደጋ መታደግ የሚችል ትግል በድርጅቱ ውስጥ መካሄድ መጀመሩንና ጠንካራ ውሳኔ መወሰኑን የጠቀሱት አቶ ተፈራ ውሳኔውንም "ከሞላ ጎደል ለአብዮት የተቃረበ የሪፎረም ውሳኔ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

448

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

0

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

48698

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

332234

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

447359

       አጠቃላይ ጎብኚ