Back

ኢህአዴግ በአጋርነት ለመስራት የሚመርጡት በሳል ህዝባዊ ፓርቲ

ኢህአዴግ በአጋርነት ለመስራት የሚመርጡት በሳል ህዝባዊ ፓርቲ

‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ኃሳብ በመ‚ለ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምረው በሰባት ቡድን ተከፋፍለው በኢህአዴግ ምክር ቤት ለጉባኤው በቀረበው ሪፖርት ላይ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡

በጉባኤው የተገኙት የ12 የወዳጅ ፓርቲ ተወካዮች በጉባኤው ላይ በመገኘት የአጋርነትና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የወዳጅ ፓርቲ ተወካዮቹ ባደረጉት ንግግር በአንድ ድምፅ ኢህአዴግ በአገሪቱ እያስመዘገበ ያለው ሰላምና ልማት ለበርካታ የአፍሪካ አገራት ምሳሌ የሚሆን መሆኑና ኢትዮጵያውያንም በዚህ የሰላምና የልማት ትሩፋት ህይወታቸው እየተቀየረና እየተሻሻሉ መሆናቸውን ካዩት ሁኔታ በመነሳት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የቻይና ኮሚዩንስት ፓርቲ ተወካይ ሚስተር ዞንግ ዌዩንግ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ካለው ፈጠን ዕድገት ጀርባ ኢህአዴግ አለ ይላሉ፡፡ ‹‹በአለም ላይ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ባስመዘገበችው ፈጣን እድገት እየተለወጠች ሲሆን ህዝቦቿም የተሻለ ኑሮ መኖር ጀምረዋል፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ሚስትር ዞንግ ዊንግ እንደገለፁት ኢህአዴግ በአገሪቱ ለውጥ ውስጥ ከፍተኛውን ሚና እየተወጣ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ከኢህአዴግ የበሰለ የአመራር ሚና ውጭ ኢትዮጵያ ይህንን ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ትችላለች ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ከኢህአዴግ ጋር በቀጣይነት በአጋርነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

የሱዳን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ተወካይ መሃሙድ ኢብራሂም አህሚድ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ሱዳን በባህል፣ በንግድና ህዝብ ለህዝብ ትስስር የረጅም ዓመት ታሪክ ያላቸው መሆኑን ገልጸው ይህ ግንኙነት በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደረገችውን አስትዋፅኦም አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነፃነት ግንባር ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር አኔል ቶሌርናዶ በበኩላቸው ‹‹የደቡብ ሱዳን ህዝብና መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከመለስ ዜናዊ አመራር ጀምሮ በአስጨናቂና ከባድ ጊዜም ቢሆን ከጎናችን ስለሆናችሁ ያለንን አክብሮት እንገልፃለን፡፡ በአገራችን ያለውን ግጭት እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እናደንቃለን፡፡›› በማለት ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እያደረገችው ያለውን ወሳኝ ሚና አስታውሰዋል፡፡ ‹‹የኢዮጵያ ህዝብና መንግስትን በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው እድገት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለ‹ት እንወዳለን፡፡ አፍሪካ ወደ ላይ ትመነጠቃለች፡፡ ኢትዮጵያውያንም ለእኛ መልካም ምሳሌ ለመሆን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡›› ብለዋል ፡፡ 

የ12 አገራት ፓርቲ ተወካዮች «አጋርነታችን ይቀጥላል! ከኢህአዴግ ጋር በአጋርነት በመስራታችንም ትልቅ ክብርና ደስታ ይሰማናል!» ሲሉም ከኢህአዴግ ጋር በአጋርነት መስራት ያለውን ፋይዳ በራሳቸው አንደበት ገልፀዋል፡፡

ተወካዮቹ እንደሚሉት ኢህአዴግ በትግልና ራሱንም ሆነ አባላቱንም በማረም ዓርዓያ የሚሆን ፓርቲ  ነው፣ የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ በየጉባኤዎቹ በተጋባዥነት የሚገኙ ወዳጅ ፓርቲዎች ኢህአዴግ በሳልና በአፍሪካ ላሉም ፓርቲዎች ጭምር በሳልነቱ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ሲናረጉ ተደምጠዋል፡፡  

ኢህአዴግ አምባገነናዊ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ መስዋዕትነትን ከፍሎ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ በሰላም ተረጋግተው ፊታቸውን ወደ ልማት እንዲያዞሩ ሳይታክት የሰራና እየሰራ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ኢህአዴግ በትግል ታሪኩ በሳል የፓርቲ ስብዕናን እንዲይዝም በየደረጃው ያሉ አባላቱ የማይተካ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በርካታ አገራዊ ጉዳዮች እየተወሰኑባቸውና አገሪቱ የምትመራበት አቅጣጫን እያመላከቱ የመጡት የእስካሁን የኢህአዴግ ጉባኤዎች ታሪካዊና ወሳኝ እንደነበሩም የሚታወስ ነው፡፡ 

የኢህአዴግ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤም አገሪቱን ወደተሻለ የእድገት አቅጣጫ ሊመሯት የሚችሉ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት የሚጠበቅ ሲሆን ድርጅታዊ ጉባኤው ትናንት ከሰዓት ጀምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰባት ቡድን በመከፋፈል ዛሬ ግማሽ ቀን ድረስ በኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሪፖርት ዙሪያ በሳል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በቡድን ውይይቱ በሳል ሃሳብና ትግሎች መንሸራሸር እንደሚገባቸው ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጋራ በሚኖር የውይይት ጊዜ ሪፖርቱ በተሻለ ሁኔታ ይዳብራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

 


ጉባኤ ጉባኤ

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣትና ጨለማውን ሊያበራው የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችዋን አፍሪካንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ጨለማውንም ለማብራት መሠረታዊ ነገር እውቀት ነው ፤ የትምህርት ዕድሉን አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ተማሪዎችም ይህንን በመገንዘብ ራሳቸውን ከውሸካና ከአሉባልታዎች በማራቅ ከትምህርት መልስ ለአገሪቷ ብርሃን ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡

በደርጅቱ ውስጥ የነበረ ጸረ ዴሞክራሲያዊነት መገንገን፣ የክራይ ሰብሳቢነት ፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት የያዘ ስለነበረ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማጥፋት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ተስኖት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከውስጥም ከውጭም አገሪቱ የመፍረስ አደጋ እንደተደቀነባት ሲተነበይ አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ሳቢያ አገሪቱን ከገባችበት አደጋ መታደግ የሚችል ትግል በድርጅቱ ውስጥ መካሄድ መጀመሩንና ጠንካራ ውሳኔ መወሰኑን የጠቀሱት አቶ ተፈራ ውሳኔውንም "ከሞላ ጎደል ለአብዮት የተቃረበ የሪፎረም ውሳኔ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ሊቀ መንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኦዲፒ 29ኛ ዓመት የምስረታ ባስተላለፉት መልዕክት የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል። ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅርፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ «ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ

ተጨማሪ ያንብቡ…

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 13 results.