Back

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

"በየማነ ገብረስላሴ"

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ  ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን  በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ  የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡ የዘንድሮ ድርጅታዊ ጉባኤ አዘጋጅ ብሄራዊ ድርጅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) በመሆኑ ጉባኤውን በመቐለ ከተማ ሊያካሄድ ችሏል፡፡ በጉባኤው አንድ ሺ በድምፅ 533 ደግሞ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በድምሩ 1ሺ533 ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ አጋር ፓርቲዎችና 12 የውጭ አገራት ወዳጅ ፓርቲዎችም በጉባኤው በወኪሎቻቸው ተሳትፈዋል፡፡ የቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ፣ የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነፃነት ግንባር፣ የሱዳንናሽናል ኮንግረስ፣ የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር፣ የኡጋንዳው ናሽናል ረሲስታንስ ሙቭመንት፣የሩዋንዳው አርበኞች ግንባር፣ የታንዛንያው ቻማ ቻማ ሙፒንዲዚ፣ የደቡብ አፍሪካው ኤ ኤንሲና የናሚብያው ስዋፖ በጉባኤው ላይ ከታደሙ ፓርቲዎች  ይጠቀሳሉ፡፡

ጉባኤው  ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን  ፓለቲካዊ፣ ድርጅታዊ፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እንዲሁም የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች አፈፃፀም ከ9ኛው ጉባኤ አቅጣጫዎች አንፃር በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ከ2008 እስከ 2012 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የሚተገበረውን የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችና አጠቃላይ አቅጣጫዎች ላይም ተወያይቷል፡፡

እንደሚወቀው ኢህአዴግ ከህዝብ ተፀንሶ በህዝብ ያደገ  ድርጅት ነው፡፡ እጅግ ጨቋኝ የነበረው የደርግ ስርዓት ለማስወገድ ታግሎ ያታገለ ህዝባዊ ድርጅትም ነው፡፡ ባለፉት 24 የሰላም ዓመታት ደግሞ በልማት፣ በሰላም ማስፈንና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ደማቅ ታሪክ የፃፈ ሁሌም ለህዝብ ጥቅም ዘብ የቆመ ድርጅት ነው፡፡ ኢትዮጵጵያ ዜጎቿ ከጦርነት ተላቀው ሰርተው ስለመለወጥ እንዲያስቡ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ሁለንተናዊ ለውጥ በማቀጣጠል  በየደረጃው ያለው የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፈጣን ልማት በማስመዝገብ ኢትዮጵያ ከድርቅና ረኃብ ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረውን  ስሟን ከማደስ አልፋ በዓለም መድረኮች ላይ  በአብነት የምትጠቀስባቸው በርካታ ስኬቶችን እንድትጎናፀፍ ያስቻለ ድርጅትም ነው ኢህአዴግ፡፡

የኢህአዴግ የስኬት ምስጢር የዓላማ ፅናቱ፣ የጠራ ፓሊሲና ራዕይ ያለው መሆኑ ሲሆን እስከ አሁን የተካሄዱ ድርጅታዊ  ጉባኤዎች የድርጅቱን  ግቦች ለማሳካት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ኢህአዴግ የካቲት ወር 1983 ዓም አምባገነኑን የደርግ ስርዓት በመደምሰስ የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ያላቸው ፓርቲዎች የሚሳተፉበትን የሽግግር መንግስት መመስረት በሚቻልበት ሁኔታ በማተኮር  ነበር አንደኛ ድርጅታዊ  ጉባኤውን  ያካሄደው፡፡ ኢህአዴግ የሚናገረውን የሚፈፅም ነውና ከጉባኤው በኃላ ደርግን ለማስወገድ ከሶስት ወራት ያነሰ ጊዜ በቂው ነበር፡፡ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓም የደርግን ግብዓተ መሬት ተፈፀመ፡፡ ሁሉንም በአገራችን ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ሃይሎችን ያካተተ የሽግግር መንግስትም ተቋቋመ፡፡

ሁለተኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ለሰላምና መረጋጋት ልዩ ትኩረት በመስጠት በ1987 ዓም በሀዋሳ የተካሄደ ሲሆን በጉባኤው በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት በሀገራችን አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ተችሏል፡፡ አራተኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በድርጅቱ ተደቅኖ የነበረውን የዝቅጠት አደጋን ለማምከን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የተካሄደ ሲሆን ይህም የድርጅቱን ህልውና መፈታተን ጀምሮ የነበረውን የመበስበስ አደጋን በማክሸፍ ረገድ ትልቅ ሚና የተጫወተ ጉባኤ ነበር፡፡ ሁሉም የኢህአዴግ ድርጅታዊ  ጉባኤዎች የየወቅቱን አደጋ እየለዩ ሰፊ ወይይት የተካሄደባቸውና ችግሩን በመፍታት ረገድ ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል፡፡ ድርጅቱና ሀገሪቱ አሁን ለደረሱበት የዕድገት ደረጃ እንዲደርሱም አስችለዋል፡፡

ኢህአዴግ በድል የማይኩራራ ድርጅት ነው፡፡ የተራራን ያህል ድል በሚያስመዘግብበት ወቅት  ጠጠር የምታክል ስህተት ካለች የስህተትዋን መንስኤ ፈትሾ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ በሳል ፓርቲ ነው፡፡ ይህ ስልት በትጥቅ ትግልም በሰፊው እንደተጠቀመበት ነባር ታጋዮች ይገልፃሉ፡፡ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል በሚጎናፀፍበት ወቅት በጥቃቅን ስህተቶች ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በመወያየት ስህተቶቹ እንዳይደገሙ የማድረግ ልምድ ነበረው፡፡ አሁንም አለው፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ በሁሉም መስኮች አንፀባራቂ ድል እየተጎናፀፈ ኢትዮጵያም በስኬት ጎዳና እንድትራመድ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ የስኬት ጉዞ ላይ የስርዓቱ  አደጋዎች ብሎ የለያቸው ችግሮች አሉ፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር አንዱና ዋናው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው የመልካም አስተዳደር ችግር የተሟላ የህዝብ እርካታ እንዳይፈጠር እንቅፋት እየሆነ ይገኛል፡፡ በእርግጥ በመልካም አስተዳደር መስክ መጠነኛ መሻሻሎች እንዳሉ የሚካድ አይደለም፡፡ ጠቅለል ብሎ ሲታይ ግን መልካም አስተዳደር የማስፈን ጉዳይ በቀጣይ ርብርብ የሚጠይቅ ሆኗል፡፡ በዚህ ረገድ እንደ በፊቱ ሁሉ ኢህአዴግ የመሪነት ሚናውን መወጣት እንዳለበት እሙን ነው፡፡

 

ኢህአዴግ ውስጡን የሚያይ ድርጅት እንደ መሆኑ መጠን በጉባኤውም ትኩረት ሰጥቶ ከተወያየባቸው ጉዳዮች ወስጥ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ የችግሩ መንስኤዎች፣ ችግሩ ጎልቶ የሚታይባቸው የስራ መስኮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች ዙርያ በጥልቀት ተወያይቷል፡፡ ጉባኤተኞቹ ‹‹የመልካም አስተዳደር ችግር ለምን መሻገር አቃተን?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ የችግሩ ዋና መንስኤ የውስጠ ድርጅት ትግል በሚፈለገው ያህል አለመቀጣጠሉ መሆኑንም መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህም ባለመሆኑ አድርባይነት፣ የቁርጠኝነት ማነስና የትግል መቀዛቀዝ በየደረጃው በሚገኘው አመራር መታየቱን ተዳስሷል፡፡ በውስጠ ድርጅት ጠንካራ ስራ በመስራት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታት ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አቋም ተይዞበታል፡፡

ጉባኤተኞቹ መልካም አስተዳደርን ማስፈን የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ በአገሪቱ የተጀመረው ሁለንተናዊ ለውጥ ከዳር ማድረስ የሚቻለው መልካም አስተዳደር ሲሰፍን ብቻ በመሆኑ ጉባኤተቹ በጊዜ የለንም መንፈስ በመልካም አስተዳደር መስክ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት እንደሚረባረቡ ባወጡት የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡ 

የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጉባኤው እንደተናገሩት በመልካም አስተዳደር መስክ የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት በተሃድሶ መንፈስ መረባረብ አለባቸው በማለት ገልፀዋል፡፡

ከ14 ዓመታት በፊት የተሃድሶ ማዕበሉ ከተቀጣጠለ ወዲህ አገራችን ለ12 ተከታታይ ዓመታት ባለ ሁለት አሃዝ ዕድገትን አስመዝግባለች፡፡ የዚህ ስኬት ምስጢር ኢህአዴግ በከፍተኛ ቁርጠኝት ድህነትን ተረት ለማድረግ ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ ርብርብ በማድረጉ ነው፡፡ አሁንም እያደረገ ይገኛል፡፡  

በታሃድሶ ወቅት ታላቁ መሪ ጓድ መለስ ድህንትን የመታገል ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አስመልክቶ በፃፈው ፅሁፍ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ ‹‹….  የእኛን የልማት ጉዞ ከተራራ ላይ በፍጥነት ከሚወርድና በየደቂቃው ፍጥንት እየጨመረ ከሚጓዝ ናዳ አምልጦ ወደ ጠንካራ ከለላ ለመጠጋት ከሚሮጥ ሰው ጋር ማመሳሰል ይቻላል፡፡ ይህ ሰው ከለላው ያለበትን አቅጣጫ አውቆ ወደዚያ የሚያመራ አቋራጭ መንገድ ይዞ ካልተጓዘ በስተቀር በናዳው እንደሚዳፈን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ አኳያ ቀና አቅጣጫ ተይዞም ቢሆን ሰውየውን ከናዳው ፍጥነት በላይ መሮጥ ካልቻለ ባለበትም ቢቀበር ለውጥ የለውም ዞሮ ዞሮ በፍጥነት ምክንያት መሞቱ አልቀረም…››

ጓድ መለስ ያለንበት ሁኔታ ቀና መንገድም ይዘን፣ ከአደጋው ለማመለጥ የሚያስችል ብቃት ያለው ፍጥነት ስለሌን በእርግጠኝነት የምንሸነፍበት አደጋ እየተከሰተ መሆኑን ተንትኗል፡፡ ‹‹ስለዚህ ሀገራችንን፣ መንግስታችንንና ድርጅታችንን ሊበታትን ከሚችለው ናዳ እጅግ በላቀ ሁኔታ መፍጠን ይገባናል›› ሲልም አጽንኦት ሰጥቶ አስቀምጧል፡፡

በድህረ ተሃድሶ በዚህ መነሳሳት ወደ ስራ የገባው መላው የኢህአዴግ አመራር፣ አባልና ህዝቡ አገራችን በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ እንድታስመዘግብ አስችሏታል፡፡ ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝም በዚህ ጉባኤ መላው የድርጅቱ አመራሮችና አባላት በተሃድሶ መንፈስ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንዲረባረቡ ማሳሳባቸው ታድያ የመልካም አስተዳደር እጦትም እንደ ድህነትና ኋላ ቀርነት ለአገራችን ልማት፣ ሰላምና አንድነት ጠንቅ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡

ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ህዝቡ ይሁንታውን ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ሰጥቷል፡፡ ህዝቡ ለኢህአዴግ ይሁንታውን ሲሰጥ አንድም ኢህአዴግ ላስመዘገባቸው ስኬቶች እውቅና በመስጠት ሲሆን ሁለትም ኢህአዴግ በተለይም ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዘው የሚታዩ ችግሮች ከድርጅቱ ህዝባዊ ባህሪ በመነሳት ይፈታቸዋል በሚል መሆኑን ኢህአዴግ በውል ተገንዝቧል፡፡ ጉባኤው ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን››በሚል መሪ ቃል የህዝቡን አደራ ለመወጣት በሚቻልበት ሁኔታ በጥልቀት የመከረውም ለዚህ ነው፡፡ጉባኤው ከመልካም አስተዳደር ጉዳይ በተጫማሪ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተጀመረው ፈጣን፣ ተከታታይነት ያላውና ፍትሓዊ ልማት አጠናክሮ ለመቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይም በጥልቀት መክሯል፡፡  

በጉባኤው ላይ የተሳተፉ አጋር ፓርቲዎች በጉባኤው የሚወሰኑ ውሳኔዎችን በመተግባር የተጀመረው ፈጣን ልማት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡የውጭ አገራት እህት ፓርቲዎችም ከኢህአዴግ ጋር ያላቸው የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት እንዲሁም አገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁሉትዮች ግንኙነት እያጠናከረው መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ኢህአዴግ የትጥቅ ትግልን መርቶ አስተማማኝ ሰላምን ከማስፈን አልፎ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ከኢህአዴግ ጋር ጠንክራ ወዳጅነት ካላቸው ፓርቲዎች የቻይና ኮሚዩንስት ፓርቲ አንዱ ነው፡፡  የፓርቲው ተወካይ ሚስተር ዞንግዌዩንግ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የተወሰኑ ኢህአዴግ ጉባኤዎች መሳተፋቸውን ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ሀገራችሁ በፈጣን እድገት መሆኗን ታዝቤያለሁ›› ብለዋል፡፡  ሚስተር ዞንግ ዌዩንግ  ኢትዮጵያ እያስመዘገበችውካለው ፈጠን ዕድገት ጀርባ ኢህአዴግ መኖሩን  አስታውሰው ‹‹ ኢህአዴግ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ፈጣንእድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት መካከል አንዷ እንድትሆን  አስችልዋታል፡፡›› በማለት ለኢህአዴግ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ 

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነፃነት ግንባር ተወካይ ኢትዮጵያ በኢህአዴግ መሪነት በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማስፈን እያደረገችው ያለችውን ጥረት አድንቀዋል፡፡ 12ቱም ፓርቲዎች‹‹አጋርነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡

እንደበፊቶቹ ሁሉ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም መስኮች የተጀመሩ ለውጦች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጥርጥር የለውም፡፡ በተለይ በመልካም አስተዳደር እምርታ የውስጠ ድርጅት በማቀጣጠል በመልካም አስተዳደር መስክ አመርቂ ውጤት እንደሚመገዘብ ጥርጥር የለውም፡፡ ኢህአዴግ በችግሮች የተፈተነ፣ በችግር አፈታት የተካነና ልምድ ያዳበረ የተግባር ድርጅት ነው፡፡ ኢህአዴግ ቃሉን ጠብቆ ህዝቡን እያማረሩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደሚፈታቸው እምነቴ የፀና ነው፡፡

ጉባኤ ጉባኤ

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣትና ጨለማውን ሊያበራው የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችዋን አፍሪካንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ጨለማውንም ለማብራት መሠረታዊ ነገር እውቀት ነው ፤ የትምህርት ዕድሉን አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ተማሪዎችም ይህንን በመገንዘብ ራሳቸውን ከውሸካና ከአሉባልታዎች በማራቅ ከትምህርት መልስ ለአገሪቷ ብርሃን ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡

በደርጅቱ ውስጥ የነበረ ጸረ ዴሞክራሲያዊነት መገንገን፣ የክራይ ሰብሳቢነት ፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት የያዘ ስለነበረ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማጥፋት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ተስኖት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከውስጥም ከውጭም አገሪቱ የመፍረስ አደጋ እንደተደቀነባት ሲተነበይ አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ሳቢያ አገሪቱን ከገባችበት አደጋ መታደግ የሚችል ትግል በድርጅቱ ውስጥ መካሄድ መጀመሩንና ጠንካራ ውሳኔ መወሰኑን የጠቀሱት አቶ ተፈራ ውሳኔውንም "ከሞላ ጎደል ለአብዮት የተቃረበ የሪፎረም ውሳኔ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ሊቀ መንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኦዲፒ 29ኛ ዓመት የምስረታ ባስተላለፉት መልዕክት የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል። ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅርፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ «ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ

ተጨማሪ ያንብቡ…

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 13 results.