Back

10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል፡፡

10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል፡፡

ለትግሉ ሰማዓታት የህሊና ጸሎት በማድረግ የተከፈተው ጉባኤ የመክፈቻ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን የትግራይ ባህላዊ ጨዋታ አሸንዳን ጨምሮ በብሔርብሄረሰቦች ባህላዊ ጨዋታ ሞቅ ደመቅ ብሎ የተከፈተው ጉባኤ የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችና የተለያዩ አገር ወዳጅ ፓርቲ ተወካዮች የአጋርነትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ጉባኤው እንደደመቀ ቀጥሏል፡፡

‹‹10ኛውን ድርጅታዊ ጉባዔያችንን የምናካሂደው የህዳሴ ጉዟችንን አጠናክረን ለማስቀጠል ወሳኝ ወቅት ላይ ሆነን ነው፡፡›› ያሉት ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሓሴ 25ቀን 2007 ዓም የሚካሂደው 10ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የኢትዮጵያን ህዳሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል በወሳኝ ምዕራፍ ላይ ሆነ እየተካሄደ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡  

ጉባኤን በንግግር የከፈቱት ጓድ ኃይለማርያም የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም በትልቁ ከማቀድ ጀምሮ የአይቻልምን መንፈስ በመስበር ለቀጣዩ የህዳሴ ጉዟችን ከጥንካሬዎቻችንም ሆነ ከድክመቶቻችን በርካታ ልምዶችና ትምህርቶች የተገኙበት ነው፡፡ እቅዱ ከምንጊዜውም በላይ በልማት ሃይሎች ማለትም በድርጅት፣ በመንግስትና በህዝቡ የተደራጀ ንቅናቄ በመፈጸሙ በእቅድ ዘመኑ በአማካኝ ባለሁለት አሃዝ ዕድገት በማስመዝገብ ፈጣኑን የኢኮኖሚ እድገት ማስቀጠል ችለናል ብለዋል፡፡

‹‹በአገር ደረጃ በምግብ እህል ራሳችንን የቻልነው በዚሁ የእቅድ ዘመን ባደረግነው ከፍተኛ ርብርብ ነው። በዚህ አጋጣሚ እቅዱን ለመፈጸም በግንባር ቀደምትነት ለተንቀሳቀሱ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ፈጻሚ አካላት እንዲሁም የልማቱ ዋነኛ ተዋናይ ለሆነው ህዝባችን በኢህአዴግና በእራሴ ስም የላቀ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡›› ብለዋል፡፡

እንደ ጓድ ኃይለማርያም ገለጻ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችን አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ በስኬት በተካሄደበትና ህዝቡ ለድርጅታችን ከፍተኛ ኃላፊነት በሰጠበት ማግስት የሚካሄድ መሆኑ ሌላው ጉባኤውን ታሪካዊ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡

‹‹ኢህአዴግ ህዝባችን በምርጫው ያስተላለፈውን ውሳኔ እና ከውሳኔው በስተጀርባ ያስተላለፋቸውን መልዕክቶች በአግባቡ ይረዳቸዋል። ህዝቡ የሉአላዊ ስልጣን ባለቤትነት መብቱን ተጠቅሞ የሰጠው ውሳኔ ኢህአዴግ ባስመዘገባቸው ስኬቶችና እና በእስካሁን ያልረካባቸው ጉዳዮችም ኢህአዴግ ከህዝባዊ እና አብዮታዊ ባህሪው ተነስቶ ሊፈታቸው ይችላል የሚል እምነት አሳድሮ ያስተላለፈው ውሳኔ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መራጩ ህዝብ ሊመራውና ሊያገለግለው የሚችለውን ፓርቲ በባዶ የተስፋ ቃል ብቻ ሊሸነግለው ከሚፈልገው ፓርቲ የለየበት በሳል ውሳኔ ያስተላለፈበትም ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ በአገራችን መገንባት የተጀመረው የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አሸናፊ ሆኖ የወጣበት በመሆኑ የህዳሴ ጉዟችንን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል ያስቻለ የህዝብ ውሳኔ ነበር፡፡›› ሲሉም ነው የገለፁት

‹‹ኢህአዴግም በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤው የመሪነት ሚናውን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ማስተላለፍ የሚጠበቅበት በመሆኑ ይህንን ተልእኮውን በብቃት እንደሚወጣ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡ ›› ብለዋል

በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህውሃት ሊቀመንበር ጓድ አባይ ወልዱ የ10ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤ በመ‚ለ ከተማ በመካሄዱ የተሰማቸውን ደስታ በትግራይ ህዝብ ስም የገለፁ ሲሆን በመ‚ለ ከተማ እየተካሄደ ያለው ድርጅታዊ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ላደረጉት ያልተቆጠበ ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ቆይታቸውም የተሳካና አስደሳች እንዲሆን ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀዋል፡፡

ጉባኤ ጉባኤ

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣትና ጨለማውን ሊያበራው የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችዋን አፍሪካንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ጨለማውንም ለማብራት መሠረታዊ ነገር እውቀት ነው ፤ የትምህርት ዕድሉን አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ተማሪዎችም ይህንን በመገንዘብ ራሳቸውን ከውሸካና ከአሉባልታዎች በማራቅ ከትምህርት መልስ ለአገሪቷ ብርሃን ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡

በደርጅቱ ውስጥ የነበረ ጸረ ዴሞክራሲያዊነት መገንገን፣ የክራይ ሰብሳቢነት ፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት የያዘ ስለነበረ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማጥፋት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ተስኖት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከውስጥም ከውጭም አገሪቱ የመፍረስ አደጋ እንደተደቀነባት ሲተነበይ አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ሳቢያ አገሪቱን ከገባችበት አደጋ መታደግ የሚችል ትግል በድርጅቱ ውስጥ መካሄድ መጀመሩንና ጠንካራ ውሳኔ መወሰኑን የጠቀሱት አቶ ተፈራ ውሳኔውንም "ከሞላ ጎደል ለአብዮት የተቃረበ የሪፎረም ውሳኔ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ሊቀ መንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኦዲፒ 29ኛ ዓመት የምስረታ ባስተላለፉት መልዕክት የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል። ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅርፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ «ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ

ተጨማሪ ያንብቡ…

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 13 results.