ትኩስ ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ “በኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባዎች የመሳተፍ ዕድላችን መስፋት በክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንድንወያይ አስችሎናል ” አጋር ፓርቲዎች የኢሕአዴግ ምክር ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ያለፉትን ወራት የእቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ። የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡ ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል። ግዴታዬን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ጓድ መለስ አለሙ የሚመራው የድርጅታችን የልኡካን ቡድን የቻይና ጉብኝት እንደቀጠለ ነው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

ጉባኤ ጉባኤ

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በርካታ ሃሳቦች የተንሸራሸሩበት 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የዛሬው ውሎው ተጠናቋል፡፡ ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ 7 የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡

ዲሞክራሲን በማስፋት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋትና የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲጠናከር አበክረን እንሰራለን፡፡ • የፌዴራል ስርዓቱ ወሳኝ ሚና እየተጫወት ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የዜጎች ሕገመንግስታዊ መብቶች ሲጣሱ ይታያል፡፡ ይህ እንዲቆምና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ የማንነት ጥያቄዎችም በህግ አግባብ እንዲፈቱ አቋም ላይ ደርሰናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ውይይቱ ከሻይ እረፍት በኋላም ቀጥሏል፡፡

ከጉባኤተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሁንም እንደቀጠሉ ሲሆን የህግ የበላይነት፣ ሴቶችን በአመራርነት ማብቃት፣ የክልል ወሰን፣ አገራዊ አንድነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የሰዎች በሰላም ተዘዋውሮ የመስራት ህገመንግስታዊ መብት፣ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያሉ ኤጀንሲዎችን የተመለከቱና መሰል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

ትናንት በቀረበው የኢህአዴግ ምክር ቤት ሪፖርት ላይ በቡድን ውይይት ከተደረገበት በኋላ በዛሬው የከስዓት ውሎው ሪፖርቱን የተመለከተ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በመቅረብ ላይ ናቸው፡፡ በጉባኤው የተመረጠው ፕሬዚዲየም የውይይቱን አጀንዳዎችንም አፀድቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ባማረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የመክፈቻ ስንስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ እና የደኢህዴን ሊቀመንበር ክብርት ሙፈርህያት ካሚል በታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ውስጥ የሚካሄድ ጉባኤ በሀዋሳ ክልሉ እንዲያካሂደ መደረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ራሱን አድሶ አዲስ ታሪክ የሚፅፍ ድርጅት!!

በሀዋሳ ከተማ ጉባኤውን ሲያካሄድ የቆየው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ድርጅት/ደኢህዴን/ ‹‹የህዝቦች አንድነት፤ ለሁለንተናዊ ለውጥ፡፡›› በሚል መሪ ቃል ሲያካሄድ የነበረው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የማዕከለዊና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በመምረት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደተናገሩት ጉባኤው ብዥታዎችን በማጥራት ወቅቱ የሚጠይቀውን የለውጥ አመራር እንደሚያደራጅ እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት ተገለፀ፡፡

የለውጡ ቀጣይት ለአማራ ሕዝቦች ተጠቃነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት; በሚል መሪ ቃል የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር ባስተላለፉት መልእክት ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት አመላክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

1412

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1381

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

55733

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

296169

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

406964

       አጠቃላይ ጎብኚ