ዜና ዜና

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ • በአዳማ ከተማ የአባላትና የአመራር መረጃ ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ዲጅታላይዜሽን) የተደገፈ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በአዳማ ከተማ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ የብሄራዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት በዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አጠቃላይ የድርጅቱ አደረጃጀትን በተመለከት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የ28ኛውን የግንቦት ሀያ በዓልን አከበሩ

የበዓሉ መርሃግብር በጽዳት ስራ የተጀመረ ሲሆን በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና ርዕዬተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ጓድ መለሰ ዓለሙ ግንቦት ሀያ በሀገራችን ለተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ፈር ቀዳጅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መግለጫ መግለጫ

Back

ዳግም ተሃድሷችን ለህዝብ የገባውን በጥልቀት የመታደስና ዴሞክራሲያችንን የማስፋት ቃል ሳነሸራርፍ እንተገብራለን።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ለመላው የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ አዲሱ ዓመት የሀገራችንን ህዳሴ እውን ለማድረግ ያዘጋጀነውና በናንተው ሰፊ ተሳትፎ የዳበረው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ሁለተኛው ዓመትና ኢህአዴግ የባለፉት 15 የስኬትና የትግል ዓመታትን በዝርዝርና በጥልቀት በመገምገም ራሱን ዳግም በማደስ የሀገራችን ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲን በማስቀጠልና በማስፋት እንዲሁም መልካም አስተዳደር በማስፈን የሀገራችን ህዝቦች እርካታ በተሻለ ሁኔታ ለማረጋገጥ የገባውን ቃል ወደ ተግባር የሚቀይርበት ዓመት ነው፡፡

ባሳለፍናቸው ሁለት አስርት ዓመታት ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን የቀየስናቸው ሀገር በቀል ፖሊሲዎቻችን በሰፊ የህዝቦች ተሳትፎ በመተግበራችን አማካይነት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማረጋገጥ ሀገራችን ለዘመናት ትታወቅበት የነበረው የድህነትና የኋላቀርነት ታሪክ ቀስ በቀስ እየተቀየረ መጥቶ በአሁኑ ስዓት በዓለም ደረጃ ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ችለናል፡፡ በዴሞክራሲ ረገድም ብዙህነታችን ውበታችንና የጥንካሬአችን ምንጭ መሆኑን የተቀበለ ሕገ-መንግስት ባለቤት በመሆናችን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ የሃይማኖቶችና የእምነቶች እንዲሁም የፆታ እኩልነት ሕገ-መንግስታዊ ዋስትና በማግኘታቸው በመተማመን፣ በመቻቻልና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመጠናከር ላይ ይገኛል፡፡ ሰላምን በተመለከተም እንዲሁ ሀገራችን ወትሮም ቢሆን ሁከትና ብጥብጥ በማይለየው የአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ ብትሆንም በተከተልነው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ባረጋገጥነው ፈጣን፣ ተከታታይና ፍትሐዊ ዕድገት አማካይነት የራሳችንን አስተማማኝ ሰላም ከማረጋገጥ  በተጨማሪ ለአፍሪካዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አጋር መሆን ችለናል፡፡ በዚህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ አስተማማኝ የሰላም አጋር ተደርጋ የምትወሰድበት ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡ በእነዚያ ዓመታት ያስመዘገብናቸው ሁሉን አቀፍ ስኬቶች በእናንተው ያልተገደበ ተሳትፎና ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ የተገኙ ድሎች ናቸውና ኢህአዴግ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡
በቀጣይም በአንድ በኩል እስካሁን ያረጋገጥናቸው ስኬቶች በሰፊ ህዝባዊ ተሳትፎ ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት በሌላ በኩል ህዝባችንን እያማረሩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ትርጉም ባለው ደረጃ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ በማረም የህዝባችንን እርካታ ለማረጋገጥ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስና ዲስፕሊን በመፈፀም የተጀመረው የህዳሴ ጉዞአችንን እውን ለማድረግ እንደሚረባረብ ኢህአዴግ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡ሁሉም የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችም ኢህአዴግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚያደርገው ዘርፈብዙ እንቅስቃሴ የተለመደው ተሳትፎአችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉና ኢህአዴግ የጀመረውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንድታጎለብቱ ጥሪውን ሲያቀርብላችሁ ከአደራ ጭምር ነው፡፡

ከላይ የጠቀስናቸውና በአንክሮ ተመልክተን ከሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ልንፈታቸው የተዘጋጀንባቸው ጉዳዩች እንደተጠበቁ ሆነው በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ የሁከትና የብጥብጥ አዝማሚያዎች በተመለከተም የሀገራችን ዕድገትና ብልፅግና እየተጠናከረ በሄደ ቁጥር ህልውናቸው እንደሚያከትም የተገነዘቡ አንዳንድ የውስጥና የውጭ ኃይሎች  የሞት የሽረት ዕድላቸውን ለመሞከር የሚያደርጉት የጣረ-ሞት ትንቅንቅ እንጂ የማንንም ብሔር አሊያም ህዝብ ጥያቄና ፍላጎት እንደማይወክሉ ኢህአዴግ በውል ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሕገ-መንግስታዊ ዋስትና ባገኙባት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ኑሮን በሚያውክ መልኩ ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ሳያስፈልግ ማንኛውንም ጥያቄ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ በማቅረብና ከዚህ ውጭ ለሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎችን በፅናት በመታገል የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድረባረብ ኢህአዴግ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ኢህአዴግ የህዝብ ሉአላዊነትን ጠንቅቆ የሚረዳ ለዚህም የታገለና እየታገለ ያለ ህዝባዊ ድርጅት በመሆኑ ለህዝብ ጥቄዎች ሁነኛ ምላሽ መስጠት የሚያስችለውን ጥልቅ ተሃድሶ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻችሁ ተገቢ የሆነ ምላሽ በመስጠት እርካታችሁን ለማረጋገጥ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስና ቁርጠኝነት እንደሚሰራ ሲገልፅላችሁም በአዲሱ ዓመት ቃሉን በማደስ ነው፡፡

መላው አመራሮቻችን፣ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችንም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የስኬትና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንላችሁ ኢህአዴግ ከልብ እየተመኘ የተጀመረውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንደ ከዚህቀደሙ ሁሉ በማጠናከር ህዝባችን የሰጠንን አደራ በከፍተኛ ቁርጠኝነትና የኃላፊነት መንፈስ በመወጣት የህዝቡን እርካታ ለማረጋገጥ የግንባር ቀደምትነት ሚናችሁን በአግባቡ እንድትወጡ ድርጅታችሁ ጥሪ ሲያደርግላችሁ በከፍተኛ መተማመን ነው፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!!