ዜና ዜና

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ • በአዳማ ከተማ የአባላትና የአመራር መረጃ ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ዲጅታላይዜሽን) የተደገፈ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በአዳማ ከተማ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ የብሄራዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት በዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አጠቃላይ የድርጅቱ አደረጃጀትን በተመለከት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የ28ኛውን የግንቦት ሀያ በዓልን አከበሩ

የበዓሉ መርሃግብር በጽዳት ስራ የተጀመረ ሲሆን በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና ርዕዬተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ጓድ መለሰ ዓለሙ ግንቦት ሀያ በሀገራችን ለተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ፈር ቀዳጅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መግለጫ መግለጫ

Back

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአቋም መግለጫ

"የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ለውጥ"! በሚል መሪ ቃል በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ውቢቷ መቐለ ላይ የተካሄደው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን የሴቷ ተጠቃሚነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሰላሟ ሲረጋገጥ፣ ሰላሟ ለማረጋገጥ ደግሞ ያለ ማንም ጠባቂነት ሴቷ ራሷ ለሰላሟ ጉዳይ ዘብ እንድትቋም ይህንን በህዝባዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ማለት አጥፊዎችን በማጋለጥና ባጠፉት ጥፋት ልክ ህግ እንዲዳኝ በማድረግ ብሎም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የሚተገብር ይሆናል፡፡

ሴቶች በልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት በሚወሰዱ እርምጃዎች ከልማቱ ተጠቃሚ ከመሆን ረገድ ከትጥቅ ትግሉ ጊዜ ጀምሮ በተሰማሩበት ዘርፍ እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ አንድ ያላቸውን ውድ ሂወት ሳይሳስቱ ዋጋ በመክፈል ድል የተጎናፀፉ፤ ከድሉ ማግስት ጀምሮም ለያዙት አላማ ታማኝ በመሆን ውጣ ውረዱን በትግስትና በብልሃት እየተወጡ ያሉና ለወደፊቱም የዜጎች የበለፀገ ሂወት በትግላቸው ብቻ እንደሚረጋገጥ ፅኑ እምነት አላቸው፡፡

ጉባኤው በ3ኛ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ጉባኤ ላይ ትኩረት እንዲሰጥባቸው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት በተገቢው በመገምገም በታዩት ክፍተቶች በትኩረት መስራት እንዳለበት አፅንኦት በመስጠት የወቅቱን የትግል ምእራፍ ከግንዛቤ በማስገባት፣ እንዲሁን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ለቀጣይ ሁለት አመታት ሊጉን የሚመራ አመራር በመምረጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ለቀጣይ አፈፃፀም መነሻ እንዲሆነን በ7 ነጥቦች ላይ የወጣውን የአቋም መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ሰላም የነገሮች ሁሉ መሰረት በመሆኑ ያለ ሰላም ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ መለወጥ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ መርቶ ማሳካት የማይታሰብ ከመሆኑም በላይ ሰላም ለሴቶች ልዩ ትርጉም አለው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች በየአከባቢው ሰላም ሲደፈርስ ይታያል፡፡ ይህንን ከመግታት አኳያ ችግሩን የሚመጥን ትግል ለማድረግ ህገ-መንግስቱ በሰጠዉ ስልጣን መሰረት የህግ የበላይነት በማስከበር ሰላም ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ በመሆኑም ሴቶች ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አበክረን እንሰራለን፡፡

2. አገራችን ኢትዮጵያ ከኋሊት ጉዞ ወደ ህዳሴ ጉዞ እንድትራመድ በተከፈለው መስዋእትነት ድርጅታችን ኢህአዴግ በጠራ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመራችን እየተመራ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ የቻለ ስርዓት የገነባ ሲሆን፤ከስርዓቱም በርካታ ሴቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን እያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች የድርጅታችን መስመር አደጋ ላይ የሚጥሉ ኣዝማሚያዎችና ተግባራትን እዚያም እዚህም እየታዩ መሆናቸዉ በጉባኤያችን በዝርዝር ተወያይተንበታል፡፡በመሆኑም የድርጅታችን ኢህአዴግ ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ስር እንዲሰድና በመስመራችን የመጡ ለውጦች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እኛ ሴቶች የስርአቱ ባለቤትና ዋነኛ ተዋናይ በመሆናችን አሁንም በአደረጃጀታችን ትግላችን በማጠናከር ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመራችን የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሃገራዊ ሃላፊነታችን በአግባቡ እንወጣለን፡፡

3. ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መነኸርያ እንደመሆኗ መጠን የተለያዩ ባህሎች፣ እሴቶችና ሃይማኖቶች ባለቤት ነች፡፡ እነዚህ ባህሎች፣ እሴቶችና ሃይማኖቶች መኖራቸው በብሄሮችና ብሄረሰቦች መካከል መቻቻልና መከባበርን ፈጥረው ለዘመናት ኖረናል፡፡ ዛሬም በብሄርና በሃይማኖት ስም የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የብሄር ብሄረሰቦችን ለዘመናት ተከባብሮና ተፈቃቅዶ በሰላም መኖርን የሚያደፍርስ ብሎም ሀገርን ሰላምና አንድነት የሚጎዳ መሆኑ እኛ ሴቶች በእጅጉ ይቆረቁረናል፡፡ ስለዚህ ልዩነታችን አክብረን የተጎናፀፍነውን ባህልና እሴት አስጠብቀን የምንሄድ ከሆነ ሀገራዊ አንድነታችን አደጋ ላይ አይወድቅም ስለሆነም እኛ የ4ኛው ኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከምንም በላይ ሀገራዊ አንድነታችን እንዲጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ ጠንክረን እንሰራለን፡፡

4. ሴቶች ከትጥቅ ትግሉ ጀምረው በተደራጀ መንገድ ያለው ጨቋኙ የደርግ ስርአት እንዲገረሰስ የበኩላቸው አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ አሁንም ሴቶች በተለያዩ አደረጃጀት ላይ በመደራጀት በአገራቸው ጉዳይ ላይ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዙርያ ተሳትፎአቸውና ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት በመታገል ላይ እንገኛለን፡፡ በመሆኑም የሴቶች አደረጃጀት በአግባቡ እንዲጠናከሩና በአገራችን እየታዩ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችል ትግል የበኩላቸው አስታዋፅኦ ለማበርከት የሴቶች ማህበር፣ የሴቶች ፌዴሬሽን በቅንጅት በመስራት የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ህልውና ለማረጋገጥ ሊጋችን የግንባር ቀደምትነት ሚናው ለመወጣት በርትተን እንታገላለን፡፡

5. የሴቶች የውሳኔ ሰጭነት ሚና ከማጎልበትና አቅማቸውንም ከመጠቀም አኳያ፡- ሴቶች አይችሉም የሚለውን የተዛባ አመለካከትን በመስበር፣ ድርጅትና መንግስታችን በተለይም በፌዴራል ደረጃ አለምን ባስደመመ ሁኔታ ለወንዶች ብቻ የተፈጠሩ የሚመስሉ ቦታዎችንም ጭምር በመስጠት የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ቦታ ከ50% በላይ መሆኑ በትክክል እንደምንችልም የምናሳይበትና ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ ለማድረስ በሚደረገው ጉዞ ጉልህ ሚናችንን የምናበረክትበት መድረክ በመሆኑ በእጅጉ ተደስተናል፡፡ በመሆኑም በፌዴራል የተጀመረው የሴቶች የውሳኔ ሰጭነት ቦታ ወደ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌዎች እንዲሰፋ አበክረን እንታገላለን፡፡

6. በሀገራችን ተግባራዊ መደረግ በተጀመሩ ሪፎርሞችና ለውጦች ጋር ተያይዞ ገና ከጅማሬው የሴቶችን እኩልነት ማረጋገጥ የቻለው ለውጥ ፍጥነቱን ጨምሮ በኢኮኖሚውም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል የሴቶች ሊጋችን በተጀመረውን የሀገራችን አዲስ ምእራፍ እንዳይቀለበስ እና ይበልጡንም ለምልሞ ፍሬውን እንድናጣጥም የግንባር ቀደምነት ሚናችንን እንወጣለን፡፡

7. ባሁኑ ጊዜ እኛ ሴቶች አቅጣጫዎች እየተቀያየሩ የጥቃቶች ሰለባ ስንሆን ይታያል፡፡ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አንስቶ የሴቶችን አዕምሮ አካልና ህይወት የሚያጠቁ ክስተቶች ሲደርሱብን መላው ሴት ትታመማለች ትደማለች፡፡ ስለዚህ በሴቾች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ከማንም በፊት እኛ ሴቶች በትጋት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ከዚያ አልፎ ጥቃት ሲፈፀም ጥቃት ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁ በፅናት መታገል አለብን፡፡ ስለዚህ እኛ የ4ኛው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ጉባኤተኛች የሴትን ህመም ታመን ችግራቸውን ተካፍለን በማንኛውም መንገድ የሚቃጣባቸውን ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንንና ሀላፊነታችን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡

ታህሳስ 09/2011 ዓ/ም
መቐለ
ክብርና ሞጎስ ለትግሉ ሰማእታት!!