ዜና ዜና

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ • በአዳማ ከተማ የአባላትና የአመራር መረጃ ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ዲጅታላይዜሽን) የተደገፈ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በአዳማ ከተማ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ የብሄራዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት በዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አጠቃላይ የድርጅቱ አደረጃጀትን በተመለከት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የ28ኛውን የግንቦት ሀያ በዓልን አከበሩ

የበዓሉ መርሃግብር በጽዳት ስራ የተጀመረ ሲሆን በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና ርዕዬተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ጓድ መለሰ ዓለሙ ግንቦት ሀያ በሀገራችን ለተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ፈር ቀዳጅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መግለጫ መግለጫ

Back

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ራሱን ISIS ብሎ የሚጠራው የሽብር ቡድን በንጹሃን ኢትዮጵያን ላይ የፈጸመው አሰቃቂ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንደሚያወግዘውና የጸረ አክራሪነትና የጸረ አሸባሪነት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ኢህአዴግ ISIS የተባለው አሸባሪ ቡድን በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው አሰቃቂና ዘግናኝ የግፍ ግድያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በዜጎቻችን ላይ በተፈጸመው ህገ ወጥ ድርጊት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማው በመግለፅ ለአደጋው ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

የሃማኖት ነጻነትና እኩልነት አስተማማኝ ህገ መንግስታዊ  ጥበቃ በተደረገበት ሁኔታ በአገራችን ለዘመናት ጸንቶ የቆየው በሃይማኖቶች መካከል የመቻቻልና የመከባበር እሴት ለማጥፋትና ሃይማኖትን ለእኩይ የፖለቲካ አላማ መጠቀሚያ ለማድረግ በአክራሪዎችና በአሸባሪዎችን ሲካሄዱ የነበሩና በመካሄድ ላይ ያሉ ህገ ወጥና ጸረሰላም እንቅስቃሴዎችን ኢህአዴግ ከመላ የአገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን በፅናት ሲታገለው እንደቆየና አሁንም እየታገለው መሆኑን መግለጫው አመላክቷል።

 ISIS የሽብር ቡድኑ የፈፀመው ዘግናኝ ተግባር በአሸባሪነትና አክራሪነት ላይ የተጀመረው ትግል አጠናክረን ካልቀጠልን በአገራችንንና በዜጎቻችን ላይ የተጋረጠው አደጋ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ነው ያለው መግለጫው ኢሕአዴግ የፀረ ሽብርተኝነትና የፀረ አክራሪነት ትግሉን ከመላ አገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

የጸረ አክራሪነትና የጸረ አሸባሪነት ትግላችን አንድ ጊዜ ከሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት ጋር ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ጋር በማያያዝ የማደናገሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡ የውጭና የአገር ውስጥ ጽንፈኛ ሃይሎች ውግንናቸው ህዝባዊ ባለመሆኑ መላ የአገራችን ህዝቦች ከፅጥታ ሃይላችን ጎን በመሆን አክራሪነትና የጸረ ሽብርተኝነት ትግላቸውን አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብሏል ኢህአዴግ በመግለጫው፡፡   

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜጎቻችን በተለይ ደግሞ ወጣቶች በአገራቸው ሰርተው ሕይወታቸውን የሚለውጡበት ሰፊ እድል በመጠቀም እራሳቸውን በመጥቀም የሀገራቸውን እድገት ሊያፋጥኑ እንደሚገባና ህይወታቸውን አደጋ ውስጥ ከሚጥል ህገ ወጥ ስደት እራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል ብሏል ኢሕአዴግ በመግለጫው።