ትኩስ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተወያዩ፡፡ ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ የማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ዩሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡ የሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ አቶ አህመድ ሽዴን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ውይይትና ድርድርን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ ኢህአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት፣ ክርክርና፣ ድርድር ለማድረግ በሚያስችላቸው ደንብ ረቂቅ ላይ ቀጣይ ውይይታቸውን ዛሬ አደረጉ፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ “በሀገራችን የተገነባው ዴሞክራሲዊ አንድነት የእግር እሳት የሆነባቸው የጥፋት ኃይሎች ሴራ መታግል ይባል ” ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር ለማካሄድ ተስማሙ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጣት አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ በኪራይ ሰብሰቢነት ላይ በሚደረገው ትግል ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንደሚገባቸው ተገለጸ በህዳሴው ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙ መደነቃቀፎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጂ የሚያደርጉ በመሆናቸው በንቃት ሊታገልዋቸው እንደሚገባ ተገለጸ በዓሉ የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል እሴቶች ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓም ጠዋት በቢሯቸው ተወያይተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል፡፡ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች ‹‹በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ ነጻ ማውጣትና ጨለማውን ሊያበራው የሚችለው እውቀት ብቻ ነው›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ ቻይና ለሚሄዱ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ በብዙ ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለችዋን አፍሪካንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ጨለማውንም ለማብራት መሠረታዊ ነገር እውቀት ነው ፤ የትምህርት ዕድሉን አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ተማሪዎችም ይህንን በመገንዘብ ራሳቸውን ከውሸካና ከአሉባልታዎች በማራቅ ከትምህርት መልስ ለአገሪቷ ብርሃን ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል። በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያሱት።

ተጨማሪ ያንብቡ…

Back

አብሮነታችንን ማን አየብን?

                                                                                                                                                                                            በሚራክል እውነቱ

የኖሮዌይ ስደተኞች ካውንስል በጁን 2018 ባወጣው ዓለም አቀፍ የስደተኞች መረጃ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ኢትዮጵያ በአውዳሚ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ካለችው ሶርያ ትይዩ ላይ ተቀምጣለች፡፡በዚህ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በመያዝ የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ ሶርያ ደግሞ በ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የስደተኛ ቁጥር ትከተላለች፡፡

ኢትዮጵያ ሰላም ያለባት ሀገር እየመሰለች፤ ነገር ግን በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን ቁጥር ከመያዝ ባሻገር በዚህ በኩል በእርስ በእርስ ጦርነት እየታመሱ ካሉት ሶርያ፣ ሶማሊያ፣ የመንና ደቡብ ሱዳን ጋር አብሮ ስሟ መጠራቱ ለኢትዮጵያዊ ማንነት የማይመጥን የአብሮነትየመደጋገፍ ባህላችንን የሚያጠለሽና በሁላችንም ዘንድ በእጅጉ ሀዘኔታን የሚፈጥር ነው፡፡

ሁኔታውን አስፈሪ የሚያደርገው ደግሞ አሁን ካለው አፍራሽ አካሄድ አንፃር በቀጣይም ዜጎች በነፃነት መኖር የሚችሉበት ሁኔታ እንደሌላ ፍራቻ ውስጥ መግባታቸውና ሁኔታው ከመሻሻል ይልቅ መፋናቀሉ ተስፋፍቶ መቀጠሉ ነው፡፡ የዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀል ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመክተት የአገርን ህልውና የሚፈትን መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

እንደኛ ባለች ታዳጊ ሀገር ውስጥ የዜጎች መፈናቀል አብሮ የመኖር ታሪክና ባህል የሚያደበዝዝ፣ የኢትዮጵያን አንድነት የተሰናሰለበትን የአብሮነት ባህልና እሴት የሚሸረሽር  የጥፋት ጉዞ ነው፡፡ አንተ ከዚህ ወገን ነህ አንተ ከዛ ወገን በሚል ዘርን ማዕከል ያደረገ ያረጀ አጥፊ አስተሳሰብ ተሸካሚ መሆን አፈናቃዩንም ተፈናቃዩንም በአንድ ላይ የሚያጠፋ፤ የአገርንም ሆነ የግለሰብን ልማት ወደኋላ የሚጎትት የኋላ ቀርነት መገለጫም ጭምር ነው፡፡

በሌላ በኩል ዜጎች ከአንድ አካባቢ ሲፈናቀሉ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ለዓመታት ያፈሩትን ሀብትና ንብረታቸውን ጥለው ነፍሴ አውጭ በማለት ነው የሚሰደዱት፡፡ ይህ ለዓመታት ያካበቱትን ሀብት በቀላሉ ትተው መሰደዳቸው የዘራፊዎችን ጉልበት በማፈርጠም ለሌላ ዘርፊያ  የሚጋብዝ   አገርንም ወደ ፍፁም ደህነት የሚያወርድ እኩይ ተግባር ነው፡፡

በዚህም ሳያበቃ መንግስት ዜጎች ከተፈናቀሉ በኋላ መልሶ ለማቋቋም የሚያደርገው ጥረት ደግሞ ሌላ የኢኮኖሚ ጫና ነው፡፡ መንግስት እንደ አገር የተደቀነብንን ድህነት ለማስወገድ የሚያደርገውን ጥረት የሚያስፈጓጉል ኢኮኖሚያዊ አቅሙን የሚያዳክም ነው፡፡ በዋናነት ዜጎች የሞላ ቤታቸውን ጥለው በመውጣት በድንገት ወደ ፍፁም ድህነት ሲገቡ የሚኖረውን ማህበረሰባዊ ጫና መገመት አያዳግትም፡፡ የአገርን ምስል የሚያበላሽ ሄዶ ሄዶ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ጭምር በመግታት አገራዊ ሁኔታችንን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከትም ይሆናል፡፡

አገራችን ያላት የተፈጥሮ ሃብት መሬት እንኳንስ ለገዛ ወንድም እህቶቻችን ይቅርና ጦርነትንና የእርስ በእርስ ግጭትን ፈርተው ከተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን መርጠው ለመጡ ለሌላማ ቢሆን በአግባቡ መጠቀም ከቻልን የሚያንስ ሆኖ አይደለም፡፡

ያ ሁሉ መተሳሰባችን፣ የአለምን ቀልብ የገዛው አብሮነታችንና መቻቻላችን ወዴት ሄደ? የእኔ ይቅርብኝ ብሎ ለተራበ አጉራሽ፣ ለታረዘ አልባሽ የሆነ ምስጉን ህዝባችን እሴት ስለምን በጥቂት ሆደ አደር ሰዎች ይሸርሸር? ዛሬ በሁሉም ጫፍ ያለ ኢትዮጵያዊ ተፈናቃይ ወገኖቻችንን ማቋቋም ላይ ትኩረቱን አድርጓል በእርግጥም ይህች ናት አገሬ……በሃዘን፣ በደስታ አብሮ መኖርን፣ አብሮ መራብን፣ አብሮ መደሰትን ያውቅበታል፡፡ እናም ሁላችንም አብሮነታችንን ማን አየብን ልንል ይገባል…ማን አየብን?

 

 


Visitorcounter Visitorcounter

Today       

387

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

374

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

18684

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

252428

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

398484

       አጠቃላይ ጎብኚ