ትኩስ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡ የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት ኢህአዴግን አጋር ድርጅቶቹን በማካተት ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ የተካሄደው ዝግጅት መጠናቀቁን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ውይይትና ድርድርን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ ኢህአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት፣ ክርክርና፣ ድርድር ለማድረግ በሚያስችላቸው ደንብ ረቂቅ ላይ ቀጣይ ውይይታቸውን ዛሬ አደረጉ፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ “በሀገራችን የተገነባው ዴሞክራሲዊ አንድነት የእግር እሳት የሆነባቸው የጥፋት ኃይሎች ሴራ መታግል ይባል ” ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር ለማካሄድ ተስማሙ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጣት አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ በኪራይ ሰብሰቢነት ላይ በሚደረገው ትግል ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንደሚገባቸው ተገለጸ በህዳሴው ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙ መደነቃቀፎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጂ የሚያደርጉ በመሆናቸው በንቃት ሊታገልዋቸው እንደሚገባ ተገለጸ በዓሉ የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል እሴቶች ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል የቻይና ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋንቻኦ በኢትዮጵያ ይፋዊ ስራ ጎብኝት እያካሄዱ ነው፡፡ 11ኛውን የብሄሮ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በዓል ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል አዲስ የሚዋቀረው የፌዴራል መንግስት ካቢኔ በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል እድገቱ የወለዳቸውንም ሆነ በአፈፃፀም ችግር ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በተከተለ አግባብ እንደሚፈቱ ተገለፀ፡፡ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በንግግር ከፍቱ የገዳ ስርዓት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ በኢህአዴግ እንደገና በመታደስ ዙሪያ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የድርጅቱ የመካከለኛ አመራር አካላት የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና መድረክ ተካሄደ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ማምሻቸውን በጠቅላይ ሚኒስተሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫቸው ሀገር ውስጥ ላሉ እና በውጭ ሀገራት ለሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ሰላም፣ ይቅርታና ፍቅርን ከማቀንቀን አቋርጠው እንደማያውቁም አንስተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የነበረውን አስፈሪ የፖለቲካ ፍጥጫ በማርገብ፣ በውጭ ሀገር የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ በማድረግ፣ ያለፈውን ታሪክ ዕሴቶች አስጠብቀን እንድንጓዝ ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት

ስለ አዲሱ ውህድ ፓርቲ በተሻለ ለመገንዝብ ይረዳ ዘንድ አላማውና አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው በስፋት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የሳምንት መወያያ ርዕስ ላይም ስለ ውህደቱ ላነሳችው ስጋትና ጥያቄዎች በተወሰነ መልስ ይሆናችሁል፡፡ በተከታታይነትም ግልጽነት የመፍጠር ስራ ይቀጥላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግን አጋር ድርጅቶቹን በማካተት ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ የተካሄደው ዝግጅት መጠናቀቁን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ።

የግንባሩ አባላት፣ ሕዝቡና የመንግስት ሠራተኛው ለውህደቱ ተግባራዊነት የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ላለፉት 29 ዓመታት ከአራት ፓርቲዎች ጋር ግንባር ፈጥሮ ሀገሪቱን ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል። በሀገሪቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄደው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በመጣው ለውጥ አማካኝነት ግንባሩን ወደሀገራዊ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲነት ለማምጣት በግንባሩ ጽሕፈት ቤት በኩል የዝግጅት ሥራ ሲያከናውን ቆይቷል። ውህደቱን ከግንባሩ አባል ድርጅቶች ባሻገር ላለፉት ዓመታት ከግንባሩ ጋር በአጋርነት ሲሰሩ የቆዩትንም ሌሎች ፓርቲዎች የሚያካትት መሆኑም ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

Back

እንደገና ወደ ኋላ ለማን በጀ?

በሚራክል እውነቱ

በአንድ ወቅት በስልጣኔ ማማ ላይ የነበረች የምስጉን ህዝብ ሀገር፣ በእንግዳ ተቀባይነቷ አለም የመሰከረላት፣ ከገባችበት የድህነት አዘቅት ውስጥ ለመውጣት ትግል የጀመረች፣ እንኳን ለሀገሬው ሰው ይቅርና ለሌሎች ሀገራት ህዝብ እንኳ የሚበቃ የለምለም ምድር ባለቤት-ኢትዮጵያ፡፡ አሁን አሁን ለዘመናት አብሮ የኖረው ሰላማችንና አብሮነታችን ከእጅ መዳፋችን ሲርቅ እያስተዋልን ነው፡፡ እንደሚታወቀው አገራችን በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋ ዛሬ አዲስ የለውጥ ኡደት ውስጥ ገብታለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ታዲያ በማናቸውም የውጭም ሆነ የውስጥ ሀይል ሰላሟና መረጋጋቷ ሊረበሽ አይገባም፡፡ ወደኋላ የምንመለስበት ሁኔታ መቼም አይኖርም ብቻ ሳይሆን አገርና ህዝብ ቁልቁል የሚወስድ የጥፋት አስተሳሰብ ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ጠበቅ ያለና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡

ኢህአዴግ መስከረም ወር ላይ ካካሄደው ጠበቅ ያለ ግምገማ በኋላ በሀገሪቱ መሰረታዊና ተጨባጭ ለውጦች መጥተዋል፡፡ ይህንንም በብቃት መወጣት የሚያስችል የአመራር ስብስብ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ መሪው ድርጅትም ሆነ መንግሥት ከምንም ነገር በላይ ሀገራዊ ጥቅምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት የክልሉን ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በመተሳሰብና በመቻቻል አብሮ ከኖረው ከወንድሙ የኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና እርስ በእርስ የጥርጣሬ መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ የመተባበርና የመደጋገፍ አቅሙን ለማዳከም ታልሞ የተሰራ ሴራ ነው፡፡

በአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተጀማመሩና የኢኮኖሚ ምህዋሩን አንድ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችሉ ልማቶችን ከመደገፍና ደጀን ከመሆን ይልቅ ኢ-ምክንያታዊ በሆኑ ነገሮች ሰበቦችን በመፍጠር ብሔርን መሰረት አድርገው ሁከትና አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ አንዳንድ አፍራሽ ኃይሎች መንግስትን የማዳከም ስራ ላይ ተጠመደዋል፡፡ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ የህዝብና መንግስት ንብረቶችን ማውደም፣ እንዲሁም ይህንኑ ግርግር መነሻ በማድረግ በዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ በመሰማራት በህገ ወጥ መንገድ የግል ሀብታቸውን ለማፍራት የሚኳትኑ ጥቂት እፉኝቶች የሌት ተቀን ስራቸው አድርገውታል፡፡

እነሱ የሚለኩሱት እሳት ህዝብ ለህዝብ ከማጫረስ አልፎ የሐይማኖት ይዘት እንዲኖረው በማድረግ አገራችንን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ በዚህም የራስን እርባና ቢስ ጥቅም ለማጋበስ ሲኳትኑ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረው አሳዛኝ ድርጊትም ከዚህ አኩይ ሃሳብ የመነጨ ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም በሰዎች መልካም ይሁንታና በጎ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ከፍና ዝቅ የሚል፤ ወደ ኋላና ወደ ፊት የሚመለስ መሆን አይገባውም፡፡ የአገራችንን ልማት ማረጋገጥ የሚቻለው ከምንም በላይ የህዝቦቿን ሰላም ማስጠበቅ ሲቻል ነው፡፡  ሰላም በሌለበት ልማትን ማሰብ አይቻልም፡፡ ትኩረታችንን ወደልማት እንዳናዞር እዚህም እዚያም እሳት በመለኮስ ወደኋላ እንድንመለስ የሚደረገው የሴራ ጉዞ በህዝባችን የተባበረ ክንድ ከመንገድ የሚቀር እንጂ የሚሳካ እንዳይሆን ሁሉም መንቃት ይገባዋል፡፡ ላይበጠስ የተጋመደው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ መካከል ቁርሾ ለመፍጠር የሚለኮሰው እሳት ላይ በስሜት ጭድ ከመጨመር መቆጠብ ይገባል፡፡ እነዚህ የደም ትስስር ያላቸው ህዝቦች እንደ አንደ ሆነው ድህነትን ለመታገል የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያደናቅፋቸውን አካል ከመንገዳቸው እንዲወገድ አብረው መታገል ይገባቸዋል እንጂ እርስ በእርስ ቁርሾ ለመፍጠር ለሚጥረው አካል ሰለባ ሊሆኑ አይገባም ባይ ነኝ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረው ችግርም የሁለቱን ህዝቦች የማይወክልና በእነዚህ ህዝቦች መካከል ያለውን ገመድ የሚያጠብቅ እንጂ የሚያላላ አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ነገም የሚጠነሰሰውን ሴራ በብልሃት ለማለፍ የሚፈጠሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ዘለቅ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ወደኋላ ከሚመልሰን ነገር ይልቅ ወደፊት የሚያሻግረን ጉዳይ ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ድህነትን ፊት ለፊት ተዋግቶ ብልጽግናን ማምጣት የሚያስችልና የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ የህዝባችንን ተሳትፎ ያረጋገጠ ሥራ መስራት ላይ በማተኮር ወደፊት መሻገር ያስፈልጋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጠረው ችግር ህይወታቸውን ያጡ፤ ቤት ንብረታቸውም የወደመባቸው ዜጎቻችን ጉዳይ ሁላችንንም እንዳሳዘን ግልፅ ነው፡፡ በተፈጠረው ሁኔታ ከማዘን ባሻገር አሁንም የነበረውን ሰላም በመመለስና በቀጣይም ከጎናቸው በመሰለፍ እርስ በእርስ በመተጋገዝ የተጋረጠውን አደጋ በጋራ መመከት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡