Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

“ማርች 8” ሴቶቻችን ከፍ ባሉበት አመት

አቡ ኬ

በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአሜሪካ ኒውዮርክ ጎዳናዎች ያልተለመደ ሰልፍ ታየ፤ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሴት ሰራተኞች የአነስተኛ የደሞዝ ክፍያንና ለጤና ምቹ ያልሆኑ የሥራ ሁኔታዎችን በመቃወም ነበር ሰልፉ የተካሄደው፡፡ ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) እንዲወለድ ምክንያት የሆነ ታሪካዊ ተቃውሞ።

በዚህም የተነሣ የሴት ሠራተኞቹና ተባባሪ ወንድ አጋሮቻቸው በሚያደርጉት አመጽ በኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ ላይ ተደጋጋሚ የሆነ ኪሣራ መድረሱ እየተባባሰ ሄደ፡፡ የሠራተኛ ማህበራት እየተጠናከረ መምጣት በሌላ በኩል ለሴቶች እንቅስቃሴ አጋዥነቱን እያጐላው መጣ፡፡ በአውሮፖ፣ በታላቋ ብሪታንያ፣ በአሜሪካና በትንሹም ቢሆን በአውስትራሊያ ሴቶች የመምረጥና መመረጥ መብታቸው እንዲከበር የሚመለከታቸውን ሁሉ ማግባባት የጀመሩት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነበር፡፡ ይህ ትግላቸው በሴቶች ዙሪያ ይታዩ የነበሩ ማንኛውም ጭቆናዎች እንዲወገዱ አመላካች ከመሆኑም በላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲከሰት በር ከፋች ሆነ፡፡

እ.ኤ.አ በ191ዐ የሴቶች ቀን እንዲከበር በመላው የአሜሪካ ግዛቶች በሚኖሩ የሴት ሶሻሊስቶችና ፌሚኒስቶች ዘንድ ተቀባይነትን አገኘ፡፡ በ191ዐ እንደዚሁ በዴኒማርክ ኮፐን ሃገን ከተማ በተደረገው 2ኛው አለም አቀፍ የሴቶች ሶሻሊስት ኮንፈረንሰ ላይ የሴቶች ቀን አለም አቀፍ ተቀባይነት ኖሮት እንዲከበር ከሴት ሠራተኞች ማህበራት ሊግ ተወካዮች ሃሳቡ ቀረበ፡፡

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እ.ኤ.አ. ከ1910 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሐገራት መከበር ቢጀምርም በሩሲያ የ1917 አብዮት ወቅት በሴቶች አመጽ አስገዳጅነት መንግስት የሴቶችን መብት የተቀበለበትና በዓሉ የተከበረበት ታሪካዊ የመጨረሻ ቀን የካቲት እ.ኤ.አ ማርች 8 ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ3 ዓመታት በኋላ በ1921 ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ይፋ ሆኖ መከበር ጀመረ፡፡ የተጋጋለው የሴቶች ቀን ተፋፍሞ ባለበት በመቀጠል በ1977 እ.ኤ.አ. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር ወሰነ፡፡

ይህ ቀን ታዲያ የሚከበረው በአለም አቀፍ ዙሪያ ያለምንም የዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ወዘተ ልዩነት ሴቶች ላስመዘገቡት አስተዋጽዖ እውቅና የሚያገኙበት፣ ስለመብታቸውና እኩልነት የሚሰብኩበት ልዩ ቀን ናት።

በአገራችንም ይሄው ቀን መከበር ከጀመረ እነሆ 43 አመታት አለፉ፡፡ በአለም ዙሪያ ደግሞ 108 አመታትን አስቆጥሯል። በአገራችን በተለያዩ የስራ መስኮች እኩልነት ላይ የሚታዩ ችግሮች  አሉ። በመሆኑም ከወንድ እኩል ሁሉም ነገር ላይ እንሳተፍ፤ አቅሙ አለን የሚሉ ተደጋግመው የሚደመጡትም በዚሁ ምክንያት ነው።

ከዚሁ መነሻነት ድርጅታችን ኢህአዴግም አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ ስለ ሴቶች እኩልነት ጠንካራ አቋም ነው ያለው። በመሰረታዊ ፕሮግራሙ ለሴቶች ተሳትፎና በፖሊቲካ፣ ኦኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መታገልን ነው የሚያስቀምጠው።

የመደረጃት መብታቸው እንዲከበር፣ በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ለማሰተፍ ብቁ አንዲሆኑም በልዩ ማበረታቻ ወይ አፈርማቲቭ አክሽን ሲሰራበት ቆይቷል።

ዛሬ ላይ ደግሞ የሄው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ሴቶቻቸን የካቢኔውን ግማሽ ቁጥር ይዘዋል፡፡ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአገር ርዕሰ ብሄር፣ የመከላከያ ሚንስትር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡

ይህ በአገሪቱ ታሪክ ሴቶቻችን በፖለቲካ ተሳትፎአቸው ከፍ ያሉበት አመት እንደመሆኑ በነዚህ ስኬቶች ላይ ሆኖ ይህን ቀን ማሰብ ለመጪው ትውልድ ትልቅ የሞራል ስንቅ ይሆናል።

ኢህአዴግ ባጋኘውና ባስገኘው ድል የሚኮራ ሳይሆን ለቀረው የሚተጋ ተራማጅ ድርጅት እንደመሆኑ አሁንም ሴቶች ካለቸው አቅም ጋር የሚመጣጠን በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚገባቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት እስኪረጋገጥ ይተጋል፡፡ በሀዋሳ በተካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የሴት አደረጃጀቶች የሴቶችን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ መድረስ በሚገባቸው የጥንካሬ ደረጃ የደረሱ ባለመሆናቸው ቀጣይ የማጠናከርና የማጥራት ስራ ያስፈልጋል የሚል አቅጣጫ ያስቀመጠው።

 

እንኳን አደረሳቸሁ 

 


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.