Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

ከሁሉም በፊት የሀገር ሰላም ይቅደም!

                                                                                                                                                                                                                                                         በሚራክል እውነቱ

''ሰላም'' የሚለው የአማርኛ ቃል ከጦርነትና አመፅ ነጻ መሆን ከሚለው የአንዳንድ መዝገበ ቃላት ፍቺ የዘለለ ትርጉም አለው። የቃሉ ምንጭ "ሻሎም'' የሚለው የእብራይስጥ ሥርወ ቃል ሲሆን በሰዎች ህይወት ውስጥ ተሟልቶ መገኘት የሚገባውን ደህንነት፣ ምሉዕነት፣ ፍፁምነትና ዋስትናን የሚያመለክት ሰፊ ፅንሰ ሐሳብ የያዘ ነው።

ሰላም ማግኘት የሚቻለው ፍትህና ማህበራዊ መረጋጋት በሰፈነበት የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ መኖር ሲቻል ነው። በአጠቃላይ ሠላም ማለት ሰዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና መንፈሳዊ ዘርፎች ውስጥ ዋስትና ያለውን ህይወት የሚመሩበት የሰከነ ስርዓት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።

ጠዋት ወጥቶ ማታ ለመግባት፤ ለፍቶ ጥሮ ግሮ ለመኖር፣ የሐይማኖት ተቋሞቻችን ዘንድ ሄደን ደጀ ሰላም ለማድረስ፣ ነግዶ ለማትረፍ … በሶስት ፊደላት አንሳ የምትታየን ግን ደግሞ የምድር ስፋቱ፣ የሰማይ ርቀቱ የማይገድባት፣ ሰው የተባለ ፍጡር ዋጋዋን አሳንሶ የሚያያት በተቃራኒው በምንም ያህል ገንዘብ መግዛት የማንችላት ሰላም ለሁላችንም ግድ የምትለን የመኖራችን ዋስትና ናት።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ አካባቢዎች በውሃ ቀጠነ ሰበብ የህዝብን ሰላምና የተረጋጋ ኑሮ ለማደፍረስ ሌት ተቀን በሚኳትኑ ጥቂት ፀረ ሰላም ሀይሎች እየተካሄደ ያለው ሀገርን የማበጣበጥ ሴራ መልክ ሊይዝ ይገባዋል፡፡ በሰላም ማጣት የተተራመሱ የዓለም አገራት ኢኮኖሚያቸው ምን ያህል ደቆ፣ በጦርነት ተራቁቶ፣ ህዝባቸው ተጎሳቁሎና በየሀገራቱ ተበትኖ ለስቃይና እንግልት እንደተዳረገ አይተናል። አይተንም አዝነናል። በእኛም ሀገር ይህ ሁኔታ እንዳይደገም ከእነዚህ ሀገራት መማር ለምን ተሳነን? ይህ ጥያቄ በሁላችንም አዕምሮ መመላስ የሚገባው፤ ፈጣን ምላሽም የሚያስፈልገው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡  

ሰላምን ማደፍረስ ቀላል መስሎ ቢታይም መመለሱ ግን ክንድን የሚያዝል ነው። መንግስት እመራዋለሁ ብሎ የሚያስበውን ህዝብ እና ሀገር ህልውናው የሚቀጥለው ህዝቡ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ብቻ ነው። ሁሉም ነገር ከሰላም በኋላ የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ችግር፣ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የስራ አጥነት ችግር፣ መሰረተ ልማት አለመሟላት፣ የወሰንና የማንነት ጉዳዮች … ወዘተ ማሰብ የሚቻለው ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ እዚህ ጉዳዮች የጋራ የሆነውን ሰላማችንን ካረጋገጥን ማግስት በተረጋጋ አዕምሮ ውስጥ ሆነን መፍትሔ ለመስጠት ቀላል የሆኑ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ለሰላም መሰዋዕትነት መክፈል የግድ ይላል። አንዴ ከእጅ ከወጣ በኋላ መመለሱ ከባድ ነውና። በሀገር ላይ ሰላምን ለማስፈን፣ መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መተሳሰብ፣ መከራከር እና በሀሳብ ልዕልና ብቻ ማሸነፍ እንደሚቻል መገንዘብ ከአስተዋይ ዜጋ የሚጠበቅ ነው፡፡

ፍላጎቶቻችንን በአመጽ፣ በጉልበት፣ በፉከራና በማስፈራራት መግለፅ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው እንደሚያይል መረዳት ይገባናል። በሰላም እጦት የማይጎዳ ዜጋ የለም፡፡ ህፃናት፣ እናቶች፣ አዛውንቶች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሰላም እጦት የሚፈጠረው አደጋ ገፋት ቀማሾች ናቸው፡፡ በመሆኑም የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን መግራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጥበብ ባለሙያዎች ፖለቲከኞች የሐይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሰላም ከሁሉም ነገር በፊት መምጣት ያለበት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ከልብ በመቀበል መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

1496

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

798

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

47393

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

205497

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

310214

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.