Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

ሀገር ወዳድነት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመያዝ ይገለፃል

                                                                                                                                                                                                                                                                 በሚራክል እውነቱ

ሁላችንም እንደምናውቀው በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መግቢያ ላይ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በራሳቸው ፈቃድ ላይ ተመስርተው ጠንካራ የጋራ ኢኮኖሚና አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት ቃል ኪዳን ስለመግባታቸው ሰፍሯል፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ አገር ለሚመዘገበው ሁለንተናዊ ልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሕዝቡ የላቀ ተሳትፎ የማይተካ ሚና እንዳለው የሚያመላክት ነው፡፡

ሕዝብ ሳያምንበትና ሳይቀበለው የሚጀመሩ ማናቸውም ልማቶች እንዲሁም የሰላምና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከዳር እንደማይደርሱ ግልፅ ነው፡፡ በኢህአዴግ መሪነት አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው ለውጥና ለውጡን ተከትሎ የተፈጠሩ መነቃቃቶችም ኢህአዴግ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ካስቀመጠው አቅጣጫ የመነጩ ናቸው፡፡ ይህ ድርጅታዊ ውሳኔ ኢህአዴግ ሀገር በመራባቸው ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችንና የተፈጠሩ ክፍተቶችንም በሚገባ በመገምገም በቀጣይ እንደ ሀገር በጋራ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን በማስፈን ወደ ህዝብ ተጠግቶ ለመስራት የሚያስችለውን ሁኔታ የፈጠረለት ነው፡፡  

ብሔራዊ መግባባት ማለት ሁሉንም ጨፍልቆ አንድ ማድረግና በአንድ ሃሳብ እንዲስማማ ማድረግ ሳይሆን መሠረታዊ በሆኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አተያይ መያዝን የሚመለከት መሆኑን በአግባቡ መረዳት ይጠይቃል፡፡ እንደሚታወቀው ብሔራዊ መግባባት በአገሪቱ የሚፈለገውን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቶች ለማፋጠን አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ነው ኢህአዴግ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳው መሆኑንን በተደጋጋሚ የሚገልፀው፡፡

በአንድ አገር ሕዝብ ውስጥ የተለያዩ አቋሞች ሊንፀባረቁ፣ አመለካከቶችና ፍላጎቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ህዝብ አገራዊ በሆኑ የጋራ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ሳይኖረው በጋራ መረባረብ መቻሉ ጥቅሙ አገራዊ ብቻ ሳይሆን ግለሰባዊም ጭምር ነው፡፡ በመሰረታዊ ጉዳዮቻችን ላይ ደግሞ ተመሳሳይ አቋም ለመገንባት የሚቻለው ብሔራዊ መግባባት ሲኖር ብቻ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በእኩልነት ላይ፣ በአገራዊ ደህንነትና ሰላም እንዲሁም በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ የጋራ አቋምና አረዳድ ሊኖራቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሀገሬን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሁሉ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትና መተማመን መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ የሀገሪቱን የአስተዳደር ሥርዓት በተሻለ መንገድ ለማስቀጠል፣ አስተዳደራዊ መዋቅሩን የተመቸ ለማድረግና በጥቅሉ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ልማትን ለማፋጠን ያግዛል፡፡

ብሔራዊ መግባባት በመወያየትና በመነጋገር ማምጣት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ያለውን አቅም ማስተባበር ይገባዋል፡፡ አሁን በአገራችን የተፈጠረው የለውጥ ሂደት ደግሞ ለዚህ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ኢህአዴግ ወደ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ከተሸጋገረ በኋላ በሀገር ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ ኑሯቸውንና የትግል ስልታቸውን በውጭ ሀገራት ያደረጉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችንና ሌሎችንም አካላት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ሁላችንም ለሀገራችን እናስፈልጋታለን የሚል መንፈስ በሁሉም ዘንድ እንዲሰርጽ ማድረግ ችሏል፡፡ ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉንም ጉዳዮች ከአገራችን ጥቅም አንፃር በመመዘንና በመግባባት ችግሮቻችንን መፍታት የምንችልበት ሁኔታ ላይ ቅድሚያ መስጠት ከሁሉም ይጠበቃል፡፡ 

 

 


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

1424

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

798

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

47321

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

205425

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

310142

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.