Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

አንድ ቤት የሚገነቡ….

በአቡ

አንዳንዴ አባቶቻችን በተረትና በምሳሌያዊ አነጋገር ያወረሱን አባባሎች በጣም የልብ አድርስ ናቸው፡፡ አሁን እየሆነ ያለውን ነገር ሳስበው ከነዚህ ተረቶች መካከል ‘'አንድ ቤት የሚገነባ ሳር አይሰራረቅም'' የሚለው በህሊናዬ አቃጫለ፡፡ ሃቅ ነው፡፡ አንዲት ጎጆ ቤት በጋራ እየገነቡ ያሉ ሰዎች እንዴት ብሎ ለጣሪያ ክዳን የሚሆናቸውን ሳር ይሰራረቃሉ፡፡ ባይሆን ተባብረው ቆንጆና ጠንካራ ሳር ካለበት ፈላልገው ያመጣሉ እንጂ፡፡ ይህን እንዳነሳ ምክንያት የሆነኝ በአገራችን የሚስተዋለው የመጓተትና በተለያየ ጎራ የመፈራረጅ አባዜ የተጠናወተው መብዛቱ ነው፡፡ አንዱ የአንዱን ቡድን ወይም ወገን ስም እየጠራ ያወግዛል፣ አንዱ የሌላኛውን አካባቢ ሰው እየጠራ ጠላትህ ነው እያለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀልና ጥላቻን ይሰብካል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ደግሞ ይህንን መርዝ ለመርጨት የሚጠቀሙበት ሰፊ ምህዳር እየሆነ መጥቷል፡፡

የአንድ አገር ያውም የአንድ እናት ልጆች፤ እጣ ፋንታችን ሁሉ የተሳሰረ መሆኑ ስለምን ተረሳ? አገር እኮ የጋራ ናት፣ ከክልል ክልል ከከተማ ከተማ ያለው አካፋይ ወሰኖችም እኮ ለአስተዳደር አመቺነት ተብለው የተሰመሩ እንጂ የኔ የአንተ አገር የሚንባባልበት ድንበሮች መሆን አልነበረባቸውም፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀደሙት ጊዜያት የተሰሩ ስህተቶች በይቅርታና በምህረት ታልፈው ታሪኮቻችንንም መማሪያ ብቻ አድርገን ለአገራዊ አንድነት በጋራ አዲስ ታሪክ ለመስራት መነሳት እንደሚገባ በመግለፅ ይህንን የሚያጠናክሩ በርካታ ርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በዚህ የለውጥ ሂደትም ዴሞክራሲ የሰፈነባት፣ የትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት፣ የህዝቦቿ አንድነት የተጠበቀና ፍትሃዊነት የተረጋገጠባት አገር ለመገንባት ራዕይ በመሰነቅ አዲስ መንገድ ጀምረናል፡፡

ባለፉት ወራቶች የሰዎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ መከበር አለባቸው ከሚል መነሻ የታሰሩት ተፈተዋል፡፡ በአገራቸው አኩርፈው የራቁትም እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡ መከፋፈላችን፤ መጠላለፋችን እንዲያበቃ የእንደመር ጥሪ በማቅረብ ሁሉም ከምንም ነገር በፊት አገሩን እንዲያስቀድም ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ ደግሞ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እፎይ ያስባለ እርምጃ ነው፡፡

በአገራችን የተጀመረው ለውጥ ዓላማ በአንድ ላይ ሆኖ ታላቅ የሆነች አገር መገንባት ነው፡፡ አገራችን ተባብረው እንደሚገነቧት አንድ ጎጆ ናት፡፡ ስለዚህ ይህችን የጋራ ቤታችንን ለመገንባት የጀመርነውን የለውጥ ሂደት አጠናክረን በማስቀጠል በውጤቱ የምንረካበትን ጊዜ ልናፋጥነው ይገባል፡፡  

 

 

 

 

 


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

919

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

914

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

44126

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

198060

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

302726

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.