Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንለይ….

(በክሩቤል መርሃጻድቅ)

እ.ኤ.አ በ2016 በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ሆን ተብሎ 25 ሚሊዮን ጊዜ የውሸት መረጃዎች እንዲሰራጩ የተደረገ ሲሆን እነዚህን ሀሰተኛ ወሬዎች በማራገብና በማሰራጨት ፌስ ቡክ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም በመጪው ወራት በአውሮፓ ሀገራት የሚካሄዱ ምርጫዎች ላይ የሀሰት ዜናዎች አሉታዊ ጥላ እንዳያጠሉባቸው ለመከላከል መስራት አስፈላጊ መሆኑን የአወሮፓ ህብረት በመግለፅ ላይ ይገኛል፡፡

በዓለማችን ከ 4ነጥብ 39 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህም በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላው 7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ከሚጠጋው የዓለማችን ህዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው ማለት ነው፡፡ ከነዚህ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ደግሞ አብዛኛዎቹ ፌስቡክን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠቃሚ ናቸው፡፡ 2 ነጥብ 77 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ማህበራዊ ሚድያን የመጠቅም ዕድል ያላቸው ሲሆን ከእነዚህም 1 ነጥብ 74 ቢሊዮን የሚሆኑት በዋናነት በስልካቸው ፌስቡክን ይጠቀማሉ፡፡

እነዚህ ቁጥሮች የሚነግሩን የዓለም ህዝቦች ትስስር ምን ያህል እየተጠናከረ መምጣቱ ነው፡፡ በሴኮንዶችና ማይክሮ ሴኮንዶች ልዩነት በፍጥነት መረጃዎችን የመለዋወጥ ዕድል ሰፍቷል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስሮች በርካታ አዎንታዊ ሚና አላቸው፡፡ የኢኮኖሚ፣ ጤና፣ ቢዝነስና ማህበራዊ ግንኙነት ስራዎች ቀላል እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ለጥናትና ምርምር የጎላ አስተዋጽዖም አላቸው፡፡ በርካታ ሰዎች የግል ስራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ተጠቅመውበታል፡፡

እንደ ማንኛውም ፈጠራ ማህበራዊ ሚድያም በርካታ ጎጂ ተግባራት ይፈጸሙበታል፡፡ የውሸት መረጃዎችን በመልቀቅ ህዝብ እንዲሸበርና በስጋት ውስጥ እንዲኖር ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ጥፋቶች ይፈጸሙበታል፡፡ በቅርቡ በኒውዚላንድ በአንድ መስጊድ ውስጥ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ጥፋት ፈጻሚው በቀጥታ በፌስ ቡክ ገጹ እንዲተላለፍ ማድረጉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ለመጥፎ ድርጊቶች የማዋል ተግባር አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡  በህይወት ያሉ ሰዎች እንደሞቱ፤ ያልተባለውን እንደተባለ እያደረጉ በምስልና በቪድዮ ቅንብር ጭምር በመታገዝ ህዝብን ለማሸበር የሀሰት ዜናዎች ይሰራጫሉ፡፡

በሀገራችን ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ሁኔታም ከዓለም አቀፍ ገጽታው የተለየ አይደለም፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት በማደግ ላይ ሲሆን ፌስቡክን ጨምሮ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች ቁጥርም እንዲሁ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በሀገሪቱ ካሉ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢንተርኔት ተጠቃዎች አብዛኛዎቹ ፌስ ቡክን በቀዳሚነት ይጠቀማሉ፡፡

የማህበራዊ ትስስር ገጾች ጥቅምና ጉዳት በሀገራችንም የሚታይ ነው፡፡ የውሸት ዜናዎች ለግጭት መንስኤዎች ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በተዋቂ ሰው ስም የሚከፈቱ የውሸት ገጾች የተሳሳቱ መልዕክቶች ሲያስተላልፉ ይታያል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣኖች ያልተናገሩት፤ ስዎችን የሚያሳዝንና ወደ መጥፎ ድርጊት የሚያነሳሱ መረጃዎች በውሸት ተቦክተው ይጋገረሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ማንነትን ወይም ኃይማኖትን ማእከል ያደረገ ጥቃት እንደደረሰ የውሸት ዜናዎችን በማስተጋባት ሌሎች ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ እንዲወስዱ ያነሳሳሉ፡፡ የሰዎችን ክብርና ስም የሚያጠፉ እና በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት የሚሸረሽሩ ሀሰተኛ ዜናዎቸ እንዲህ በብዛት እንዲሰራጩ ደደረጋል፡፡

በአጠቃላይ ሀሰተኛ ዜናዎች በዓለማችንም ይሁን በሀገራችን አሳሳቢ እየሆኑ ነው፡፡ የሰዎችን አብሮ የመኖር እሴት እንዲሸረሸር በማደረግ በተቃራኒው አለመተማመንና ግጭት እንዲከሰት ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ የውሸት ዜናዎችን ለመከላከል መንግስታት፣ የማህበራዊ ትስስር ባለ ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የራሳቸውን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ይሁንና አድማሱን እያሰፋ የመጣው የሀሰት መረጃዎችን ችግር ለመከላከል ሁሉም ኃላፊነት አለበት፡፡ በመጀመርያ ራሳችን የሀሰት መረጃዎችን ከማሰራጨት መራቅ እናም ሌሎች የሚያሰራጩትንም መከላከል ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውሸት ዜናዎችን ከማጋለጥ ጀምሮ አንድ መረጃ ስናይ እውነታውን ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆን፤ በተለያዩ አቅጣጫዎች መመልከታና እውነትነታቸውን በአስተውሎት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ እውነታውን ሳናረጋገጥ ለሌሎች አለማጋራት ይገባል፡፡ ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተን በጎ በጎውን መውሰድ መጥፎውን ማራገፍ ይገባል፡፡ የውሸት መረጃ አቀናባሪዎችን መከላከል የምንችለው ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው፡፡


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.