Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

ለሚወረወርልን እሳት ጭድ እየመገብነው ነው ወይስ ውሃ እየቸለስንበት?

                                                                                                                                                                                                አብዲ ኬ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች መልካቸውን እየቀየሩ ሁለት የአንድ እናት ልጆች /ሁለት ኢትዮጵያ የምትባል መሬት ላይ አብረው ተፈጥረው አብረው የኖሩ ወንድማማች ህዝቦች ወይም ብሄሮች/ መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች እንዲመስሉ እየተደረገ ነው፡፡

በዚህ ይህ የኔ አካባቢ ነው፣ አንተ መጤ ነህ፣ ውጣልኝ/ውጭልኝ እስከ መባባል ተደርሶ፤ የሰው ህይወት እየጠፋና በርካቶች ለዘመናት ከኖሩበት የትውልድ ቀዬአቸው እየተፈናቀሉ ነው፡፡

ይህ ግጭት እውነትም በህዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለ ግጭት ነው ወይ? ሲባል ሁሉም አፉን ሞልቶ በጭራሽ፤ እንዴት ተደርጎ፤ በተድላ ጊዜ በደቦ አመርተን ለአገር የምንተርፍ፣ በችግራችን ጊዜ ደግሞ አንድ ቂጣ ተካፍለን በልተን አድረን ክፉ ደጉን አብረን ያሳለፍን፤ አንድ እናት ገቢያ ስትሄድ የአንዷን እናት ጡት ለሁለት ጠብተን ያደግን ሰዎች ምን ቆርጦን ጦር እንማዘዛለን? እንላለን፡፡ ከግጭት መልስ በየአካባቢው የሚደረዱ ህዝባዊ ውይይቶች ላይም አዘውትረን የምንሰማው ይህንኑ ነው፡፡ ደግሞም ሀቅ ነው፡፡

ታዲያ ምንድነው የሚያጋጨን? ሲባል መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ያንን አብሮነታችንን አፍርሶ እርስ በእርስ አባልቶ ሊያጣፋን የሚሻ የጋራ ጠላታችን ወይም በግጭት ውስጥ ጥቅም የሚፈልግ ቁንጽል ፖለቲከኛ ወይም ብሄሩን መደበቂያ አድርጎ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ላይ ታች የሚል ሌባ/ሙሰኛ ነው፡፡ ሲጠቃለል ግን የኛም ሆነ ከውጭ የመጣ ወገንን ደም በማቃባት ትርፍ የሚፈለግ ወይም የሚደሰት ያው ጠላታችን ነው፡፡

እኛስ አብሮ እንደኖረ፣ በአንድ ጡት እንዳደገ ወንድማማች ህዝብ፤ በብዝሃነት የደመቁ ለዘመናት በሚያስቀና አይነት አብሮነት ደምቀው ሲኖሩ የነበሩ አካባቢዎች መርጠው ከውጭ እሳት ሲወረውሩልን፣ እከሌ ጠላትህ ነው፣ አይወድህም፣ እሱ የተለየ ጥቅም እያገኘ አንተ እየተበደልክ ነው…ወዘተ አየተባለ ጥላቻ ሲሰበክ ምላሻችን ምንድን እየሆነ ነው?

በተለይ ወጣቶች፤ በዘመን አመጣሹ ማህበራዊ ሚዲያ ለዓይን በሚስብ ልብን በሚገዛ ውስጡ በመርዝ በተለወሰ ጽሁፉ ተከሽኖ ሲሰራጭልን፤ ምንድነው ይህ ነገር፣ ማነው ይህን ማለት የደፈረው፣ ምንስ ፈልጎ ነው? አብሮነታችን ላይ ማን እየዘመተ ነው? መዋደዳችንን ማን እየበረዘው ነው? ብለን እየመረመርን ነው ወይስ ተነስ ያለንን ሁሉ ተከትለን ሰሜት ውስጥ እየገባን ነው?

ዝም ብዬ አይደለም ይህን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተትኩት፡፡ እንደ ቀልድ በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፉ ከፋፋይና እኛና እነሱ የሚሉ ጽሁፎች መሬት ላይ እየወረዱ በየአካባቢው ሞትና መፈናቀል ሲያስከትሉ መነሻቸው ጥያቄ ቢያጭርብኝ ነው፡፡ ተዋናይም ሰለባም እኛው ራስችን እየሆንን ስለሆነ ነው፡፡ የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠሩ ዘግናኝ ነገሮችን ሁላችንም በአንድ አፍ እያወገዝን ለምን ዞሮ ጌዴኦና ጉጅ ላይ ተደገመ፣ ለምን ቡራዩ ላይ አየን፣ ለምን ቤንሻንጉል ላይ ተመሳሳይ ነገር ተደገመ፡፡

ያጣሉን ከእኛ ውጭ ያሉ ሌላ እኩይ አላማ በጉያቸው ይዘው የሚንቀሳቀሱ ይሁኑ እንጂ ያጣሉን እርስ በእርስ ነው እኮ፡፡ በአንድ ቦታ የተከሰተው ነገር ለምን ትምህርት አልሰጠንም፤ እያየን እየሰማን ለምን ደገምነው? ይሄ ነው ለሚወረወርልን እሳት ጭድ እየመገብነው ነው ወይስ ውሃ እየቸለስነበት ነው? ብዬ እንድጠይቅ ያደረገኝ፡፡

አሁን ደግሞ ይሄው ከአዲስ አበባ ለመጀመር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲደገስ የነበረው ሞት አልሳካ ሲል የሃይማኖትና ብሄር ልዩነት ጌጡ አድርጎ ትዳር መስርቶ ጎጆ ቀልሶ ልዩነት ውበት በሆነበት ህዝብ ባለተራ ሆነ፡፡ የአንድነታችንና የአብሮነታችን መሰረት የሆነው ሸዋ የእኩይ አላማቸው ማስፈፀሚያ ቦታ ሆነ፡፡

ትናንት ማታ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው እንደገለጹት በእነዚህ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ሰው ሞቷል፣ አካል ጎድሏል፡፡ ይህ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ሁነት ነው፡፡

ልብ እንበል የእነደዚህ አይነት ችግር ሰለባ እንዲሆኑ የሚፈለጉ አካባቢዎች አብሮነትና የመፈቃቀራችን መሰረት ብሎም ምሳሌ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ነው፡፡ ለሰው ፍቅር ሟች ነው ተብሎ የተነገረለት የተዘፈነለት የሃረርና የድሬደዋ ላይ ነው፣ ተሰናስሎ የመኖር ሚስጥራችን መነሻ የሆነችው አዲሰ አበባና አካባቢዋ ላይ ነው፣ የህብረ ብሄራዊነት መሳያ የሆነችው ደቡብ ላይ ነው፣ አሁን ደግሞ የሃይማኖትና የብሄር ልዩነት ውበት እንጅ ምንም አለመሆኑን ያስተማረን ወሎና አካባቢው ነው ሰለባ እንዲሆን እየተፈለገ ያለው፡፡ ይህ የሚያሳው ምን ያህል እሴቶቻችንን፣ እኛነታችንና አብሮነታችንን ለመሸርሸር እየተሸረበ ያለ ሴራ እንደሆነ ነው፡፡

አካሄዳቸውንም ልብ ብለን ብናይ መጀመሪያ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለሁለት በተከፈለ ሁለት ወገን የሚመስል የተቃርኖ ሃሳቦች በተጠና መልኩ የጥላቻ ስብከት ሲካሄድ እያየን ነው፡፡ እዛ ውስጥ ሰዎችን ወደ ስሜት ለማስገባት ህዝቡ የሚወዳቸው ሰዎች ላይ ወይም አንድ ብሄር ላይ ጸያፍ የሆኑ ስድቦችን መሰንዘር፣ ካለሆነ ደግሞ እየተበደልክ ነው፣ እርስት እየተቀማህ ነው በሚል ህዝቡን በስሜት ለመከፋፈል ሲሞከር አይተናል፡፡

በመቀጠልም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንዱ ብሄር ተለይቶ እየተተነኮሰ ነው፣ ወገንህ አየተነካ ነው ተነስ የሚል ይከተላል፡፡ በዚህ የተነሳ ሁለት ሰው እንኳን ቃል ከተለዋወጠ፣ እሳትን በእሳት ነው፣ አይን ያጠፋውን አይኑን ማጠፋት ነው በማለት ለከፋ ጥፋት የመቀስቀስ አዝማሚያዎችን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተመለከትን ነው፡፡

ግጭቱ መቆሚያ እንዳይኖረው ደግሞ እከሌ የሚባል ድርጅት አስገደለህ፣ እከሌ የሚባል ግለሰብ ቀሰቀሰብህ እያሉ እራሳቸው የደገሱትን ጥፋት ለሁለት ቡድን ከፍለው መፈረጅ ደግሞ እየተከተለ ነው፡፡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉ ብሄራዊ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ምንም በቂ ማስረጃ ስም እየጠሩ መፈረጅን እየተመለከትን ነው፡፡  

አላማው ግን ገልጽ ነው፡፡ ህዝቡ የተሻለ ቀን ለማየት በጥረቱ የለኮሰውን ለውጥ ችቦ ለማጥፋት ነው፡፡ እኛ ደግሞ እንደ ህዝብ ይህንን ቀድመን ከተገነዘብን የለውጥ ችቦአችን እንደበራ እንዲሻገር ከብልሃት ጋር መትጋት ይገባናል፡፡ እንዲፈጀንና እንዲያፋጀን የሚወረወርልን እሳት ላይ ውሃ እንቸልስ እላለሁ፡፡ የጥፋት ሃይሎች ጎትተው ማስገባት ወደሚፈልጉት መቀመቅ ከመግባት ተቆጥበን ርምጃችን ሁሉ ጥንቃቄ የተሞላበት፤ ሁለቴ አስበን አንዴ የምንራመድበት ይሁን፡፡

ሰላም ለእኛ ይሁን!!


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.