Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚመጥን የአደረጃጀት ስርዓት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ • በአዳማ ከተማ የአባላትና የአመራር መረጃ ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ዲጅታላይዜሽን) የተደገፈ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በአዳማ ከተማ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ የብሄራዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት በዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አጠቃላይ የድርጅቱ አደረጃጀትን በተመለከት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የ28ኛውን የግንቦት ሀያ በዓልን አከበሩ

የበዓሉ መርሃግብር በጽዳት ስራ የተጀመረ ሲሆን በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና ርዕዬተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ጓድ መለሰ ዓለሙ ግንቦት ሀያ በሀገራችን ለተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ፈር ቀዳጅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

Back

እንደገና ወደ ኋላ ለማን በጀ?

በሚራክል እውነቱ

በአንድ ወቅት በስልጣኔ ማማ ላይ የነበረች የምስጉን ህዝብ ሀገር፣ በእንግዳ ተቀባይነቷ አለም የመሰከረላት፣ ከገባችበት የድህነት አዘቅት ውስጥ ለመውጣት ትግል የጀመረች፣ እንኳን ለሀገሬው ሰው ይቅርና ለሌሎች ሀገራት ህዝብ እንኳ የሚበቃ የለምለም ምድር ባለቤት-ኢትዮጵያ፡፡ አሁን አሁን ለዘመናት አብሮ የኖረው ሰላማችንና አብሮነታችን ከእጅ መዳፋችን ሲርቅ እያስተዋልን ነው፡፡ እንደሚታወቀው አገራችን በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋ ዛሬ አዲስ የለውጥ ኡደት ውስጥ ገብታለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ታዲያ በማናቸውም የውጭም ሆነ የውስጥ ሀይል ሰላሟና መረጋጋቷ ሊረበሽ አይገባም፡፡ ወደኋላ የምንመለስበት ሁኔታ መቼም አይኖርም ብቻ ሳይሆን አገርና ህዝብ ቁልቁል የሚወስድ የጥፋት አስተሳሰብ ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ጠበቅ ያለና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡

ኢህአዴግ መስከረም ወር ላይ ካካሄደው ጠበቅ ያለ ግምገማ በኋላ በሀገሪቱ መሰረታዊና ተጨባጭ ለውጦች መጥተዋል፡፡ ይህንንም በብቃት መወጣት የሚያስችል የአመራር ስብስብ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ መሪው ድርጅትም ሆነ መንግሥት ከምንም ነገር በላይ ሀገራዊ ጥቅምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት የክልሉን ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በመተሳሰብና በመቻቻል አብሮ ከኖረው ከወንድሙ የኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና እርስ በእርስ የጥርጣሬ መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ የመተባበርና የመደጋገፍ አቅሙን ለማዳከም ታልሞ የተሰራ ሴራ ነው፡፡

በአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተጀማመሩና የኢኮኖሚ ምህዋሩን አንድ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችሉ ልማቶችን ከመደገፍና ደጀን ከመሆን ይልቅ ኢ-ምክንያታዊ በሆኑ ነገሮች ሰበቦችን በመፍጠር ብሔርን መሰረት አድርገው ሁከትና አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ አንዳንድ አፍራሽ ኃይሎች መንግስትን የማዳከም ስራ ላይ ተጠመደዋል፡፡ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ የህዝብና መንግስት ንብረቶችን ማውደም፣ እንዲሁም ይህንኑ ግርግር መነሻ በማድረግ በዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ በመሰማራት በህገ ወጥ መንገድ የግል ሀብታቸውን ለማፍራት የሚኳትኑ ጥቂት እፉኝቶች የሌት ተቀን ስራቸው አድርገውታል፡፡

እነሱ የሚለኩሱት እሳት ህዝብ ለህዝብ ከማጫረስ አልፎ የሐይማኖት ይዘት እንዲኖረው በማድረግ አገራችንን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ በዚህም የራስን እርባና ቢስ ጥቅም ለማጋበስ ሲኳትኑ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረው አሳዛኝ ድርጊትም ከዚህ አኩይ ሃሳብ የመነጨ ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም በሰዎች መልካም ይሁንታና በጎ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ከፍና ዝቅ የሚል፤ ወደ ኋላና ወደ ፊት የሚመለስ መሆን አይገባውም፡፡ የአገራችንን ልማት ማረጋገጥ የሚቻለው ከምንም በላይ የህዝቦቿን ሰላም ማስጠበቅ ሲቻል ነው፡፡  ሰላም በሌለበት ልማትን ማሰብ አይቻልም፡፡ ትኩረታችንን ወደልማት እንዳናዞር እዚህም እዚያም እሳት በመለኮስ ወደኋላ እንድንመለስ የሚደረገው የሴራ ጉዞ በህዝባችን የተባበረ ክንድ ከመንገድ የሚቀር እንጂ የሚሳካ እንዳይሆን ሁሉም መንቃት ይገባዋል፡፡ ላይበጠስ የተጋመደው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ መካከል ቁርሾ ለመፍጠር የሚለኮሰው እሳት ላይ በስሜት ጭድ ከመጨመር መቆጠብ ይገባል፡፡ እነዚህ የደም ትስስር ያላቸው ህዝቦች እንደ አንደ ሆነው ድህነትን ለመታገል የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያደናቅፋቸውን አካል ከመንገዳቸው እንዲወገድ አብረው መታገል ይገባቸዋል እንጂ እርስ በእርስ ቁርሾ ለመፍጠር ለሚጥረው አካል ሰለባ ሊሆኑ አይገባም ባይ ነኝ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረው ችግርም የሁለቱን ህዝቦች የማይወክልና በእነዚህ ህዝቦች መካከል ያለውን ገመድ የሚያጠብቅ እንጂ የሚያላላ አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ነገም የሚጠነሰሰውን ሴራ በብልሃት ለማለፍ የሚፈጠሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ዘለቅ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ወደኋላ ከሚመልሰን ነገር ይልቅ ወደፊት የሚያሻግረን ጉዳይ ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ድህነትን ፊት ለፊት ተዋግቶ ብልጽግናን ማምጣት የሚያስችልና የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ የህዝባችንን ተሳትፎ ያረጋገጠ ሥራ መስራት ላይ በማተኮር ወደፊት መሻገር ያስፈልጋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጠረው ችግር ህይወታቸውን ያጡ፤ ቤት ንብረታቸውም የወደመባቸው ዜጎቻችን ጉዳይ ሁላችንንም እንዳሳዘን ግልፅ ነው፡፡ በተፈጠረው ሁኔታ ከማዘን ባሻገር አሁንም የነበረውን ሰላም በመመለስና በቀጣይም ከጎናቸው በመሰለፍ እርስ በእርስ በመተጋገዝ የተጋረጠውን አደጋ በጋራ መመከት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡


ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.