Back

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በንግግር ከፍቱ

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች  5ኛ ዘመን፣ ሁለተኛ ዓመት አንደኛ የመክፈቻ ስብሰባ ንግግር በማድረግ ከፍተውታል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ  በንግግራቸው የ2008 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2009 በጀት ዓመት አቅጣጫዎችን ዳስሰዋል፡፡ በ2008 ዓም በኤልኒኖ ምክያት በ50 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም ድርቁ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል መቻሉን አንስተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በአንዳንድ አከባቢዎች በተከሰቱ ሁከቶች የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ንብረት መውደሙን አሳዛን ክስተት እንደነበርም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡ በተከሰቱ ግጭቶች  የዜጐች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉንና በዚህ የተነሳ ደፋ ቀና ብለው ሰርተው ኑሮአቸውን ለማሸነፍ የሚንቀሳቀሱ ዜጐች ለብዙ ፈተናዎች መዳረጋቸውንም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ሀገሪቱ በእድገት ጎዳና መገስገስ በጀመረችበት በዚህ ወቅት የኒዮ ሊበራል አጀንዳቸውን ሊጭኑብን የተዘጋጁ ኃይሎች ወደትርምስ እንድንገባ አቅደው አገራችንን ለማተራመስ በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የማንንም እጅ ሳንጠብቅ በመላ የአገራችን ህዝቦች ተሳትፎና በአገራዊ አቅማችን በመተማመን መገንባት መጀመራችን ያስቆጣቸው አገሮች፣ ረዘም ላሉ ዓመታት ውስጥ ውስጡን ሲዘጋጁ ከርመው በአሁኑ ጊዜ ፅንፈኛ የዳያስፖራ ኃይሎች ከቀሰቀሱት ነውጥ ጋር በመመጋገብ አገራችንን ለማተራመስ በቀጥታ እየተረባረቡ ይገኛሉ ብለዋል
 እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ በቀላሉ ሊያነሳሱዋቸው የሚችሉ ወጣቶችን የጥፋት ሃሳቦች፣ እንዲሁም ክብሪትና ነዳጅ እያስታጠቁ ለአገራችን ቁልፍ ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ያላቸውን ፋብሪካዎች፣ የአበባ እርሻዎችና ሌሎች ተቋማት በማጋየት ከፍተኛ ውድመት ሊከተል ችሏል፡፡
በ2009 ዓም ህዝቡ ያነሳቸው ፍትሃዊ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንዲሁም ከህዝቡ ጥያቄ ውጭ ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚፈልጉ ኃይሎች ሴራ ለማክሸፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት 10 ቢሊዮን ብር ተንቀሳቃሽ ፈንድ መያዙንም ተናግረዋል፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች  ተጠቃሚ የሚያደርጉ መርሃግብሮች እንደሚተገበሩ ገልጸው ለሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ታሳቢ ዋደረገ የደሞዝ ማስተካከያ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡  
በቅርቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስራውን በሚጀምርበት ወቅት የፌዴራል መንግስትን በአዲስ መልክና ቅኝት ለማዋቀር ተግባራዊ እርምጃ በማድረግ የመንግስት ስልጣንን ካላግባብ የመጠቀም ዝንባሌን የሚገታ፣ በውጤት አልባነት የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ መቆየት የማይቻል መሆኑን የሚያረጋግጥ አዲስ የመንግስት ምክር ቤት የማደራጀት እንቅስቃሴ እንደሚካሄድም አብራርተዋል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ

  በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ...

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ማምሻቸውን በጠቅላይ ሚኒስተሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫቸው ሀገር ውስጥ ላሉ እና በውጭ ሀገራት ለሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ሰላም፣ ይቅርታና ፍቅርን ከማቀንቀን አቋርጠው እንደማያውቁም አንስተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የነበረውን አስፈሪ የፖለቲካ ፍጥጫ በማርገብ፣ በውጭ ሀገር የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ በማድረግ፣ ያለፈውን ታሪክ ዕሴቶች አስጠብቀን እንድንጓዝ ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት

ስለ አዲሱ ውህድ ፓርቲ በተሻለ ለመገንዝብ ይረዳ ዘንድ አላማውና አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው በስፋት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የሳምንት መወያያ ርዕስ ላይም ስለ ውህደቱ ላነሳችው ስጋትና ጥያቄዎች በተወሰነ መልስ ይሆናችሁል፡፡ በተከታታይነትም ግልጽነት የመፍጠር ስራ ይቀጥላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ሀገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለበለጠ ድል እንዘጋጅ

ኢትዮጵያ ከሶስት ሺኅ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላት ጥንታዊ ሀገር ናት፡፡ ሉአላዊነቷን ሳታስደፍር የቆየች የስልጣኔ መሰረት የሆነች ድንቅ ሀገርም ናት፡፡ እየተፈራረቁ የመጡት የውጭ ወራሪዎች የማሳፈር ታሪክዋ በዋናነት ዜጎቿ በብሄር፣ በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በሀገር ፍቅር ለመስዋዕትነት ዝግጁ መሆናቸው ነው፡፡

ውይይትና መደማመጥን በማጠናከር ሰላማችን እንጠብቅ!

የረጅም ዘመን የስልጣኔና ተምሳሌት የሆነችው ሀገራችን ዓለም በሁለት ገጽታዎች ያውቃታል፡፡ አንደኛው በምድራችን ውስጥ ከነበሩ ገናና እና አስደናቂ ስልጣኔዎች መካከል የአንዱ ባለቤት መሆንዋ ነው፡፡ የእነዚህን ስልጣኔዎች ማሳያ የሆኑ ሐውልቶች፣ ቅርሶች… ወዘተ የዚህ ህያው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ አሁንም የዓላማችን የታሪክ ተመራማሪዎች ያሉፉት የስልጣኔ አሻራ ላይ የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር እንደቀጠለ መሆኑን ስንመለከት ሐገራችን የነበረችበት የስልጣኔ ደረጃ መገንዘብ የሚያስችል ነው፡፡

ለተሻለ ውጤት የጋራ ጥረት

"በኤፊ ሰውነት" ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ ፋና ወጊ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በአገራችን አሁን እየተተገበሩ ያሉት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችም አገር በቀልና ውስጣችንን ያገናዘቡ መሆናቸው ከነተግዳሮታችንም ቢሆን በለውጥ ውስጥ...

አሰራሮቻችንን በማዘመን የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንረባረብ

"ከኤፊ ሰውነት" በአገራችን በተለይ ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በወጣቱ በኩል በተደጋጋሚ ሲነሱ የምንሰማቸው ጥያቄዎች በዋናነት ከተጠቃሚነት ጋር የተያያዙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሚባል ሁኔታ የወጣቱ መሰረታዊ ጥያቄ የስራ እድል ፈጠራ ጉዳይ እንደሆነም እንገነዘባለን፡፡ ውድ አንባብያን...

የዓድዋ ድል ጽናትን የህዳሴ ጉዞአችንን እውን ለማድረግ ልንጠቀምበት ይገባል!

"በኤፊ ሰውነት" አድዋ ሲነሳ አስቀድሞ በታሪክ መዛግበት እንደተፃፈው ወደ ሁሉም አዕምሮ የሚመጣው እውነታ አውሮጳውያን ኃያላን በበርሊን ያደረጉት ‹‹አፍሪቃን የመቀራመት›› ሴራ ይመስለኛል፡፡ ኃያሉን ከራሳቸው አልፈው ድንበር ጥሰው፤ የአገር ሉዓላዊነት ተዳፍረው አፍሪካን ሲቀረማመቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ደግሞ...

Visitorcounter Visitorcounter

Today       

1884

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1604

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

26021

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

232144

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

428333

       አጠቃላይ ጎብኚ