Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

የማህበራዊ ዘርፍ ስኬት ሲለካ

ሀገራችን የቀደምት ስልጣኔ መነሻ ከሚባሉት እንደነ ቻይና፣ ግብጽ፣ፋርስ የመሳሳሉት ጋር የምትመደብ ናት፡፡ እንደነ ላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስትያናትና የአክሱም ሀውልት የመሳሰሉ የስልጣኔ አሻራዎች ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሶስት ሺህ ዓመታት በላይ እድሜ ያላቸው ቅርሶች የሀገርቷ ስልጣኔ ጥንታዊ መሆኑንና ቅርሶቹ ይዞታቸውን ጠብቀው ከትውልድ ትውልድ መተላለፋቸው በወቅቱ የነበረው ትውልድ በእውቀት መመራቱን የሚያመላክት ነው፡፡

ለከፍታው ዘመን መደላደል የተፈጠረባቸው ዓመታት

መስከረም 1 ቀን 2000 ዓ.ም ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የተለመደው የዘመን መለወጫ ቀን ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደኛውን ሚሊንየም ሸኝተው ሌላኛውን ሚሊንየም የሚቀበሉበት ብሎም ከአንደኛው ወደ ቀጣዩ ክፍለ ዘመን መሸጋገሪያ ዘመን በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለየ ስሜት ውስጥ ሆነው ነበር ይህንን ቀን የተቀበሉት፡፡ በርግጥም ሺህ ዓመታትን ቆጥሮ የሚመጣውን ሚሊንየም ለማየት መታደል ልዩ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ይህ እድለኝነትም ጭምር ነው፡፡

ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጠበቆች ነን

የአለም ሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ እንደ የአለም ሜትሮሎጂካል ድርጅት/WMO/ መረጃ የአለም ሙቀት መጨመር ከቅድመ ኢንዱስትሪያል ጊዜ ከ 0.5 ከኢንዱስትሪያል ዘመን በኋላ በ2016 ወደ 1.1 በዲግሪ ሴልሽየስ ደርሷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ያደጉ ሀገራት ሳይቀር የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ውጤት በሆኑት በኤልኒኖ እና ላኒና መዘዝ ምክንያት በጎርፍ መጥለቅለቅና በድርቅ መጠቃት የተለመደ የዓለማችን ክስተት ሆኗል፡፡

የሰላም ዋጋ ውድ ነው!

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ሲገናኙ ቅድሚያ ስለ ሰላማቸው ሁኔታ የሚጠያየቁት፡፡ ጠዋት ከእንቅላፋቸው ተነስተው‹‹በሳላም አውለኝ›› ማታ ሲተኙም›› በሰላም ያዋልከኝ በሰላም አሳድረኝ›› ብለው ምስጋናቸውን የሚገልጹም የሰላምን ትልቅ ዋጋ በመረዳት ነው፡፡ እናም ሁሉም ሰው ሊባል በሚችል መልኩ ሰላም በህይወቱ ላይ ትልቁን ዋጋ ያለው ውድ ነገር መሆኑን ይገነዘባል፡፡

የታላቁ ሰው አሻራዎች ሲታወሱ

የታላቁ ሰው የህይወት ጉዞ የአፍሪካ የነጻነት አድባር የሆነውን ሰንሰለታማውን የአድዋ ተራሮች ጥግ ከምትገኘው የአድዋ ከተማ በ1947 ዓ.ም ጀመረ፡፡ ወላጅ አባቱ ተምሮ ሀኪም እንዲሆን ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው፡፡ የብላቴናው የትምህርት ውጤትም የአባቱን ተስፋ ይበልጥ አለመለመዉ፡፡

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.