Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

አዲሲቷ ኢትዮጵያ- የብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብቶች የተከበሩባት

"በአሜሳይ ከነዓን" ስለ ትላንቷ ኢትዮጵያ ስናነሳ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ስለነበረችው ኢትዮጵያ ነው የምናነሳው፡፡ የትላንቷ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ መስክ ያለማቋረጥ በማሸቆልቆል ላይ የነበረች፤ የዜጎች ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች የሚረገጡባት ሃገር ነበረች፡፡ አብዛኛው የአገራችን ህዝብ በገጠር የሚኖር...

የፌዴራላዊ ስርዓታችን የመለወጣችን ምስጢር

"በአሜሳይ ከነዓን" አገራችን ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መናኽሪያ፣ የኃይማኖት ብዝሃነት ያለባት፣ የየራሳቸው ቋንቋ፣ ባህል፣ ስነልቦናና መልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ያላቸው ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባለቤት የሆነች አገር ናት። በአገራችን ታሪክ ያለፉት መንግስታት ብዝሃነትን...

ትምክህትና ጠባብነት የፀረ-ድህነት ትግላችን እንቅፋቶች

"ከአሜሳይ ከነዓን" ከዛሬ 24 ዓመት በፊት ከሁኔታዎች በመነሳት በአገራችን ያሟረቱ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትሆናለች ያሉም ቀላል አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ የትምክህት ኃይሎች በኢትዮጵያ ህዝቦች መራራ ትግል ላይመለስ የተቀበረውን ስርዓት ለመመለስ የዳከሩበት፤ የጠባብነት አስተሳሰብ ተሸካሚ...

የሰማዕታትን አደራ እያሰብን ቃላችንን እናድስ

"የማነ ገብረስላሴ" የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ በመሪ መድርጅቱ ህወሓት እየተመራ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የነበረውን አስከፊ የጭቆና ስርዓት ለማስወገድ ትግል የጀመረበት ቀን ነች፡፡ በዚህች ቀን 11 ታጋዮች በደደቢት በረሃ የመጀመርያውን የትግል ችቦ ለኮሱ፡፡ ጥቂት ታጋዮች ሲጀምሩ ከጥቂት ኋላ ቀር...

ልማትን በማፋጠንና ኪራይ ሰብሳቢነት አምርሮ በመታገል የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተሟላ መልኩ መመለስ ይቻላል

"ከአሜሳይ ከነዓን" ሰሞኑን ለስራ ጉዳይ ወደ አንድ ቦታ ተጉዤ ነበር፡፡ የቦታው ርቀት ከመዲናችን አዲስ አበባ ወደ 250 ኪሜ ገደማ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቦታ ከአንድ አምስት ዓመት በፊት እንዲሁ ለስራ ጉዳይ ብቅ ብዬ አውቃለሁ፡፡ በአምስት ዓመት ውስጥ የሚገርም ለውጥ ተመልክቻለሁ፡፡ ያኔ እኔ በመጣሁበት ወቅት...

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

983

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

914

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

44190

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

198124

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

302790

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.