Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡ ኮሚቴው የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ግምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ዛሬ ግንቦት 8ቀን 2011 ዓም ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ እየተወያየ መሆን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 28/2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ያለፉት ዓመታትን የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከ2003 እስከ 2010 ዓም በአገሪቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ የ9.6 እድገት ማሳየቱን በዚህም የግብርና ዘርፍ የ5.7 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ የ19.1 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 10.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ተመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሚያዝያ 28ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

PEACE IS PRECIOUS AND MUST BE KEPT UNDAMAGED

PEACE IS PRECIOUS AND MUST BE KEPT UNDAMAGED By Yohannes Gebresellasie (Ph.d) Addis Ababa Among many other things, there are things such as fresh air, clean water and peace that God gave his...

በአገር ግንባታ የግለሰብ ሚና ወሳኝነት

“በሙሃመድ ሰጠኝ” ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አንድ የሞራል ታሪኮችን ያሰባሰበ በውጭ ቋንቋ የተፃፈ ፅሁፍ ነው፡፡ ታሪኩ ግለሰባዊ ሚና ለአገር ግንባታ ያለው አስተዋፅኦ ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌና አስተማሪ ሆኖ ስላገኘሁት ላካፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡

ዓለማቀፋዊ ክብርና ተሰሚነት ያጎናጸፈ ፖሊሲ

ዓለማቀፋዊ ክብርና ተሰሚነት ያጎናጸፈ ፖሊሲ "የማነ ገብረስላሴ " ህዳር 1995 ዓም የተዘጋጀው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ሰነድ መግቢያ ላይ ‹‹ይህ የውጭ ጉዳይና አገራዊ የደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስጠበቅና አገራዊ ህልውናችንን የማረጋገገጥ ተልዕኮ ያለው ሆኖ የተቀረጸ...

ፈጣን ልማታችን ድርቅን መቋቋም አስችሎናል

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሀገራት በመከሰት ተፅዕኖውን እያሳደረ በሚገኘውና ኤልኒኖ ተብሎ በሚጠራው የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቀበል አለማችን ግድ እንደሆነባት በተለያዩ አካላት ሲገለፅ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሀገራችንም የኤልኒኖ ክስተት ባስከተለው የዝናብ ወቅትና ዓመታዊ የዝናብ መጠን መዛባት ምክንያት በተፈጠሩ ችግሮች ያልተጠበቁ ጉዳቶችን ለማስተናገድ ተገዳለች፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግና እርሱ የሚመራው ልማተዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስትም የችግሩን ስፋት አስቀድመው በመገንዘብ ችግሩን ለመቋቋምና በዜጎችና በኢኮኖሚው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት የሚያስችል አቅጣጫ ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡

ኢህዴን / ብአዴን - በትግል እሳት የተፈተነ “ወርቅ”

ኢህዴን / ብአዴን - በትግል እሳት የተፈተነ " ወርቅ " "በዘመኑ ፈረደ" መቼም ሁልጊዜም ቢሆን ጭቆናና ግፍ እስካለ ድረስ ይህንን የሚፃረር የመረረ ትግል መደረጉ አይቀሬ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጭቁን ብሔሮችና ብሔረሰቦችና ህዝቦች ታሪክም የሚያስረዳን ይህንኑ ነው፡፡ ህዝቡ በተለይ የፊውዳል...

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.