Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

ለወንድማማቾች ዘላቂ ሰላም ሲባል የቀረበ ጥሪ

ኢትዮጵያና ኤርትራ ተመሳሳይ ባህልና ቋንቋ የሚጋሩ፤ የተዛመዱና የተዋለዱ ህዝቦች ያሏቸው በብዙ ጉዳዮች ተመሳሳይ የሆኑ ሀገሮች ናቸው፡፡ የሁለቱም ሀገራት ህዝቦች  ለበርካታ ዘመናት በአንድነትና በመልካም ጉርብትና ከኖሩ በኋላ ከ20 ዓመታት በፊት በአጋጠው ግጭት ግንኙነታቸው ተቋርጦ ይገኛል፡፡ በዚህ...

አፍሪቃዊቷ ፍሎረንስ

በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ መካከለኛው ዘመን ተብሎ የሚታወቀው ጊዜ አህጉሩ በተለይም ምእራብ አውሮፓ ከዳር - ዳር እግርከወርች በያዘዉ የጨለማ ዘመን The "Dark Ages" ውስጥ ያለፈበት ድህነት፣ ርሀብ፣ በሽታ እርዛትና ተስፋ ማጣት አሽመድምዶት ታሪክ የማይዘነጋው የሰቆቃ ጊዜን ለመቶ አመታት ያሳለፈበት ዘመን ነው፡፡

ሌላኛው የዕድገት ጮራ

ከዛሬ 120 ዓመት በፊት በአጼ ሚኒሊክ የተጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋታ ኢትዮጵያን ከጁቡቲ ለማስተሳሰር የተጀመረ ሲሆን ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ በ1910 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ይሄ የባቡር መስመር መገንባት በወቅቱ የኢትዮጵያ የሥልጣኔ መገለጫም ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ይሄው አገልግሎትም እስከ 1990ዎቹ ድረስ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በትውልድ ጅረት ያልተዛነፈ ፍትሃዊ አቋም

በሀገራችን ስነ-ቃል ውስጥ እንደ አባይ ግዙፍ ተዋናይ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ፍቅር፣ ናፍቆት፣ ቁጭትና ብሶትን ለመግለጽ በምንጠቀማቸው ተረትና ምሳሌዎች እንዲሁም ዘፈንና እንጉርጉሮ ውስጥ አባይ የላቀ ስፍራ አለው፡፡

ለሰላም ዘብ እንቁም!!

ዓለማችን ለሁሉም ሕዝቦች ንጽህ አየር እንድናገኝ የተዋበ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳሯን ሳናባላሽ እንድንጠቀም እንደ ስጦታ ሰጥታናለች፡፡ የዓለም ሕዝቦች ይህንን የተሰጠንን ስጦታ የማበላሽት አሊያም ደግሞ ተንከባክበን የመያዝ እሳቤ ግን በእጃችን ናት፡፡

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

999

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

914

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

44206

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

198140

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

302806

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.