Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

የሃዘን መግለጫ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ቦይንግ 737 በረራ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

መልካም እሴቶቻችን ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችን

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያስተሳስሯቸው በርካታ መልካም እሴቶች አሏቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ሐቀኝነት፣ መረዳዳት፣ መከባበር፣ ተዋዶና ተፋቅሮ በአብሮነት መኖር መፈቃቀድ እና የመሳሰሉት እሴቶች ይገኙበታል ፡፡

የህዝቦች የአንድነት ቃል ኪዳን- የሁሉም ስኬቶች የጀርባ አጥንት

ህዳር 29 ቀን 1987 ዓም በኢትዮጵያ ታሪክ ጎላ ያለ ስፍራ የሚሰጣት ቀን ነች፡፡ ይቺ ቀን የዘመናት የኢትዮጵያ ብሄሮች/ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች የትግል ፍሬ የሆነውን የሀገራችን ህገ መንግስት በህዝቦች የነቃ ተሳትፎ የጸደቀባት ቀን ነች፡፡

ያልተንበረከኩት

ስንቶች ተኮላሽተዉ ከአረንቋዉ ዘቀጡ፤ ስንቶች ተሸንፈዉ ከጎዳና ወጡ፤ ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረከክነዉ፤ ነገ እልፍ እንሆናለን ታሪክ ምስክር ነዉ፡፡

የሕዳሴ ጉዟችንን የሚገታ እንቅፋት ከስሩ ይነቀል!

አገራችን በተለያዩ ጊዜያት የከፉ እልቂቶችን ያስከተሉ የተለያ ግጭቶችን ጦርነቶችን አስተናግዳለች፡፡ ወንበራቸውን ክብራቸውንና ከበርቴነታቸውን ለመጠበቅ ህዝብን ዋጋ ባስከፈሉ ገዢ መደቦች የአገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአገራቸው ሁለንተናዊ ሃብት መጠቀም ሲገባቸው ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከሀብታቸው፤ ከመብታቸውና ከተጠቃሚነታቸው እንዲነቀሉ በመደረጋቸው በድህነት ተቆራምደው ለዘመናት የበይ ተመልካች ሆነው እንዲቆዩ ሆነዋል፡፡

የዘርፈ ብዙ ድሎች ባለቤት- ደኢህዴን

ሁሉም የሀገራችን ህዝቦች በበርካታ የጭቆና ታሪክ አልፈዋል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦችም በአፄዎቹም ሆነ በአምባገነኑ የደርግ ስርዓት የደቡብ ክልል ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ረጅም ጊዜ የቀጠለ አስከፊ ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናና አድሎ ሲደርስባቸው ቆይቷል፡፡ ስርዓቶቹ ጸረ- ብዙኃነት መሆናቸው ደግሞ የተለያዩ ማንነቶች፣ ቋንቋዎች፣ እምነቶችና እሴቶች ባለ ቤት ለሆኑ የደቡብ ክልል ህዝቦች ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናዉ የከፋ እንዲሆን አድርጎት ቆይቶዋል፡፡

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

ጎብኝዎች ጎብኝዎች

Today       

906

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

914

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

44113

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

198047

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

302713

       አጠቃላይ ጎብኚ

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.