ዜና ዜና

የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር እንደቀጠለ ነው

ፓርቲዎቹ በሀሙስ ውሏቸው የምርጫ ስርአቱ ምን አይነት መልክ ሊኖረው ይገባል በሚለው ጉዳይ ላይ ባለፈው ሀሙስ ባቀረቡት ምክረ ሃሳብ ላይ ተጨማሪ ነጥቦችን በማንሳት ተከራክረዋል፡፡ ኢሕአዴግ በዛሬው ክርክርም የህዝቦችን ዴሞክራሲያዊ ውክልናና ወሳኝነት በተሻለ መልኩ የሚያረጋግጠው የአብላጫ ድምፅ ስርዓት የሀገሪቱ ምርጫ ስርዓት መገለጫ መሆን እንዳለበት አስምሮበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ም/ቤት የድርጅትና የመንግስት ስራዎችን አፈፃፀም በመገመገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ም/ቤት ጳጉሜ 3 እና 4 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ2009 ዓ.ም የድርጅትና የመንግስት ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን ማጠናቀቁን የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የሚገኝበት ሁኔታ፤ በተሃድሶው የተገኙ ውጤተችና በቀጣይ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች በዝርዝር በመገምገም በሁሉም ደረጃዎች በተካሄዱ መድረኮች በተዛቡ አመለካከቶች ላይ ነጻ፣ ግልጽና መተክላዊ ትግል መደረጉን ፈትሻል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የንባብ ቀን በብሔራዊ ቤተመንግስት ተከበረ

የ2010 አዲስ ዓመት የዋዜማ አከባበር 5ኛው ቀን ነሐሴ 30/2009 ዓ.ም “ንባብ ባህላችን እናደርጋለን” በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ቤተመንግስት ታዳጊ ህጻናት በተገኙበት ተከብሯል፡፡ ቀኑን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ “የሀገር ፍቅር” ከሚል መጽሓፍ ‹የዜግነት ስሜትና ለጋራ ኃብት መቆርቆር› በሚል ርዕስ የሰፈሩትን ጽሁፎች ለታዳጊ ህጻናት አንብበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የድርጅትና የመንግስት ስራዎችን አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነሐሴ 27 እና 28 ቀን 2009 ዓም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የ2009 የድርጅትና የመንግስት ስራዎች አቅድ አፈፃፀምን በጥልቀት በመገምገም መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የደረሰበትን ደረጃ፣ ያስመዘገበውን ውጤትና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በዝርዝር ገምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…