Amharic Amharic English English

የ (ደኢሕዴን) ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ የ (ደኢሕዴን) ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ
ድርጅታችን ደኢሕዴን/ኢሕአዴግ ገና ከምሥረታው ጀምሮ ባነገባቸው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ዓላማዎች በመመራት ጠንካራ ድርጅትና የክልሉን ዴሞክራሲያዊ አንድነትን በመገንባት የፈርጀ ብዙ ድሎች ባለቤት አድርጎናል፡፡ በዚህም ዴሞክራሲን በጽኑ መሠረት ላይ ከመገንባት ባሻገር የህዝቦችን የማምረት አቅም በማሳደግ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገቶችን በማፋጠን ለኪራይ ሰብሳቢነት የተመቸውን ፖለቲካል ኢኮኖሚ በልማታዊነት ለመተካት ሰፊ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ክልላዊ ለውጥን እየመራ ለሀገራዊ ህዳሴ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ የማስፈፀም አቅምን ለማጎልበት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና የተደራጀ ሰፊ ሕዝባዊ አቅም በመገንባት በማያቋርጥ የለውጥና የዕድገት ጉዞ እየገሰገሰ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ 
ለዚህም ብቃትና ጥራት ያለውን አመራር በቀጣይነት በመገንባት የጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እያቀጣጠለ በፖለቲካል ኢኮኖሚው ለውጥ ራሱን እየለወጠ የተሀድሶ መስመር ግቦቹን ለማሳካት ድርሻውን እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ባለፉት ተከታታይ 11 ዓመታት ባለሁለት አሃዝ ዕድገት ማስመዝገባችን የመሥመራችን፣ የድርጅታችን፣ የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችንና የህዝባችን አንፀባራቂ ድሎች ናቸው፡፡
በገጠር አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን በመምራትና የተደራጀ የኤክስቴንሽን ሥርዓት በመዘርጋት በተሰጠው ሙያዊ ድጋፍ በሰብል ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት፣ በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በገጠር መሠረተ ልማትና በግብይት መስኮች ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበናል፡፡ በገጠር የአርሶ አደራችንንና የአርብቶ አደራችንን ምርታማነት የዛሬ 22 ዓመት ከነበርንበት በሰባት እጥፍ በማሳደግ ግብርናችን የነበረበት እጅግ ኋላቀር የአመራረት ዘይቤ ካስከተለው የተመጽዋችነት ችግር ደረጃ በደረጃ በማላቀቅ ክልላችንን በምግብ ሰብል ምርት ራሳችንን ወደ መቻል አሸጋግረናል፡፡
በከተሞቻችንም የህዝቡን አጠቃላይ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተለይም የወጣቶችንና የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችንና ስቲራቴጂዎችን በመቅረጽና ተግባራዊ ርብርብ በማድረግ በርካታ ድሎችን ለመቀዳጀት ችለናል፡፡ በዚህም መሠረት በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አማካይኝነት ሰፋፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የከተሞችን ነዋሪዎች የድህነት መጠንን ደረጃ በደረጃ በመቀነስ ውጤት እያስመዘገብን መምጣታችን፤ ከተሞቻችን ምቹ የመኖሪያና የመሥሪያ አካባቢ እንዲሆኑ በፕላን እንዲመሩ ለማድረግና መሠረተ ልማቶችን በቀጣይነት በማስፋፋት እንዲሁም ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር የሚያስችል አደረጃጀት በመፍጠር ከተሞቻችን በማያቋርጥ የለውጥና የዕድገት ጉዞ ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ ችለናል፡፡ 
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት አውታሮችን በማስፋፋት ረገድም ፍትሃዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ማዕከል ያደረጉ በርካታ ውጤቶችን አስመዝገበናል፡፡ በዚህ ረገድ በትምህርትና በጤና፣ በሰው ሀብት ልማት ላይ በማተኮር አምራችና ጤናው የተጠበቀ ዜጋ በማፍራት ባደረግነው ርብርብ ለሀገራዊ ህዳሲያችን ብቁ የሆነ ትውልድ እየተገነባ ነው፡፡ የመንገድና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የተከናወኑ ተግባራት ክልላዊ ዕድገታችንን ከማፋጠን በተጨማሪ የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት በማጎልበት ረገድም ሁነኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ 
በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር መስክም ብዙሃነትን የማያስተናገድ ሥርዓት ሀገራችንን ወደማያባራ እልቂትና ጥፋት እንደሚያስከትል ገና ከጅምሩ የተገነዘበው ድርጅታችን አሁን ባለንበት ደረጃ ክልላችን የግልና የቡድን መብቶች የተከበሩበት ህዝቦች በመቻቻል እና በመፈቃቀድ ጠንካራ አንድነት የሚገነቡበትና በፀረ ድህነት ትግሉ በጋራ በመዝመት ባለፉት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የቻልንበት ክልል ለመሆን ችሏል፡፡ መልካም አስተዳደርን በማረጋገጥ ረገድ በየደረጃው የህዝባችንን ተሳታፊነትንና ውሳኔ ሰጪነትን በማጎልበት የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር ተግባራዊ በማድረግ ድርጅታችን በህዝባችን ዘንድ ያለው ተአማኒነትና የመሪነት ሚና እየጎለበተ መጥቷል፡፡ ለግጭትና አለመግባባት መንስኤ የነበሩ ኋላ ቀር አመለካከቶችና ደባል የጥገኝነት አጀንዳዎችን በየወቅቱ በመመከት የክልሉን ህዝቦች አንድነትና ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ የተቻለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ 
እነዚህ አንጻባርቂ ድሎች እንደተጠበቁ ነው መድረስ ከነበረብን ትራንስፎርሜሽን አንጻር ግን ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅብን በመተማመን እኛ የደኢህዴን ድርጅታዊ የአባላት ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የሚከተለውን ባለ አሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

Pages: 1  2  

የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን

የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን 

የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ በደርግ ውድቀት ዋዜማ ላይ የኢህአዴግ ድርጅቶች በነበሩት በሕውሀት፣ ብአዴንና፣ ኦህዴድ ውስጥ ሲታገሉ ከነበሩና ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች አብራክ በፈለቁ ታጋዮች ማህበር መልክ በየብሔረሰቡ የተጀመረው የተደራጀ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል ከተከናወነው ከፍተኛ የፖለቲካና የማደራጀት ሥራ በኃላ በ1985 ዓ/ም ብሄረሰባዊ መሰረት የነበራቸውን 21 ድርጅቶችን በማሰባሰብ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ደኢህዴን/ ተመሰረተ፡፡

ከአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ደኢህዴን በየብሔራዊ አደረጃጀት የተበታተነውን ግንባር ደኢህዴግ/ን በ1995 ዓ/ም በማፍረስ ወደ አንድ ወጥ ክልላዊ ፖርቲነት የተሸጋገረ ሲሆን ንቅናቄው በክልሉ በሚገኙ በየዞኖችና ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን አደራጅቷል፡፡  እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ የጠራ አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት ፖለቲካዊና ድርጅታዊ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ንቅናቄው አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሣሰብና ዓላማን አንግቦ ባካሄዳቸው ትግሎች በክልሉ በህዝባዊ ምርጫ ተረክቦ ላለፉት 18 ዓመታት ንቅናቄዎችን በሚመራው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ለማስፈፀም የሚንቀሣቀስ በፈቃዱ በኢህአዴግ ውስጥ የታቀፈ የኢህአዴግን ውሣኔዎች ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ የሚያደርግና በግንባሩ ውሣኔ የሚገዛ ነው፡፡

ንቅናቄው እስከ አሁን 7 ጉባኤዎችን ያካሄደ ሲሆን ባለፋት 18 ዓመታት መንግስታዊ ስልጣን ይዞ የክልሉንና የአገራችንን ህዳሴ እውን ለማድረግ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ጎዳና በመምራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው

ደኢህዴን ከ56 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በሚገኙበት የደቡብ ክልል ሁሉንም ብሔረሰቦች በማሰባሰብ ለብሔረሰቦች ብሄራዊና መደባዊ ጥቅሞች መረጋገጥና በፈቃዳቸው ለሚዘልቅ ክልላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዎ አመራር እየሰጠ ይገኛል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የቋንቋና የባህል ልዩነት ሣይገድባቸው በመካከላቸው ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እየገነቡ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተው አገራዊ አንድነት ምሣሌ በመሆን እንዲጓዙ ከማድረጉም በላይ ድህነትንና ኃላቀርነትን በመፋለም ወደፊት እየገሰገሰ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

የደኢህዴን ኢህአዴግ ዓላማዎች

1. የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ

የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ የሚከበሩት፣ የዴሞክራሲ ባህልና ተቋሞች የሚያብቡበት፣ሕዝቡ በክልሉና በአገሪቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች የነቃ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ተሣትፎውን የሚያረጋግጥበት፣ በሕዝቦች መብት መከበር በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጠንካራ አንድነት የሚጎለብትበት፣ የዳበረ ህብረ ፖርቲያዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መፍጠር ነው፡፡ ይህን ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ ለማሣካትም የሚከተለውን የፖለቲካ ኘሮግራም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

 የዜጎችን መብት ማስከበር የዴሞክራሲ ተቋማትንና ባህልን ማዳበር፣

  በሰፊው ህዝብ የነቃ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ተሣትፎ ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገንባት፣

   በህዝቦች መብቶች መከበር፣ በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲፈጠር መታገል፣

     ጠንካራና ዴሞክራሲያዊ የአገር መከላከያና የህግ አስከባሪ አካላት በሀገር እንዲፈጠሩ መታገል፣

2. የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ዓላማ

የደኢህዴን ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ፈጣን እድገት በማረጋገጥ፣ ከዚሁ እድገት ህዝቡ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆንበት ክልላችን በአገር አቀፍ አገራችን ደግሞ በዓለም አቀፋዊው የኢኮኖሚ ትስስር ውስጥ ያላት ቦታና ድርሻ ተሻሽሎ ኢኮኖሚያዊ ነፃነትዋ እየጎለበተ እንዲሄድ ለማድረግ የሚያስችል የዳበረ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚከተሉትን ነጥቦች የያዘ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ኘሮግራም ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

Pages: 1  2