ዜና ዜና

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ በመቐለ ከተማ ለሚያካሂደው ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመገምገም ላይ ነው።

ጉባኤው እንደ ድርጅት የተፈጠረውን አዲስ የሴቶች የለውጥ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ሊያስቀጥል በሚችል መልኩ የሚካሄድ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች በፅ/ቤቱ መሟላታቸውን የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰአዳ ኡስማን ለስራ አስፈፃሚ አባላት ገልፀዋል።

የሀሳብ ብዝሀነት በሚንሸራሸርበት መልኩ መካሄድ አለበት ተብሎ በተመከረበት በዚህ ጉባኤ ላይ እንደ ኢህአዴግም ሆነ እንደ ሀገር የሴቶችን አንድነት ሊያጠናክር በሚችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

ውይይቱን በበላይነት የመሩት የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር እና የሰላም ሚኒስትሯ ጓዲት ሙፈሪያት ካሚል ለእኛ ለሴቶች ጥቅማችን ሰላም ብቻ ነውና አሁን ያለውን የጥላቻ መንፈስ ለመስበር ያለንን ጉልበት አሟጠን መጠቀም አለብን በማለት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ከክልል ክልል የሚታዩ ቁርሾዎችን መቅረፍ እንዲቻል እና ሴቶች ለሰላም ቅድመ ሚናቸውን መወጣት እንዲችሉ ጉባኤው ሰላምን አጥብቆ መስበክ እንደሚገባው ጓዲት ሙፈሪያት ካሚል ገልፀል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ጉባኤው መዳረሻ የሚሄዱ ሴቶች በሚያልፉባቸው አካባቢዎች በሙሉ ሰላምን በመስበክ የፈረሱ የአንድነት ድልድዮች መጠገን የሚችሉበትን መሰረት እየጣሉ እንዲያልፉ ስራ አስፈፃሚው መክሯል።

ጉባኤው "የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 7 እስከ 9 በመቐለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።