ዜና ዜና

ኢሕአደግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሄዳል፡፡

የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤን ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2011 .ም በመቀሌ ከተማ #በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ; በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠዓዳ ኡስማን ገለጹ፡፡

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ ጉባኤ በአጠቃለይ ከ700 አባላት የሚሳተፉበት ሲሆን 620 በድምጽ የሚሳተፉ 20ዎቹ ደግሞ ያለድምጽ የሚሳተፉት ተጋባዥ እንግዶች ናቸው ብለዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሰዓዳ እንደገለጹት ሴት ሚኒስተሮችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕዝብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ሴት ተጋበዥ እንግዶች እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ በሚያካሄደው ጉባኤ በተለያዩ አጅንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የጠቆሙት ኃላፊዋ በመተዳደሪያ ህገ-ደንብ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ገልጸዋል፡፡

በአገራችን አሁን እየታየ ያለው ለውጥ ከላኛው የአመራር መዋቅር እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ድረስ የሴቶችን ተጠቃነት ማዕከል ባደረገ መልኩ እንዴት ማስቀጠል ይቻላል እንዲሁም የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት እንዴት ማሳደግ ይቻላል የለውን ጉዳይ ጉባኤው ይወያያል ነው ያሉት ወ/ሮ ሰዓዳ ፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ዕለት ከ1000 እስከ 1500 ሴት ታሳታዎች እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡