ለውጡን የሚመጥን የአመራር ስምሪት መስጠት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን ብቸኛው የለውጡ አማራጭ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ አመራር ኮሚቴመደበኛ ስበሰባውን ባካሔደበት ወቅት የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በከተማችን የ6 ወር ወጣት ዘርፍ ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም ለውጡ በከተማችን አዲስ አበባ ወጣቶች ዘንድ የፈጠረውን መነሳሳት በማቀጣጠል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ትክክለኛ የወጣቶች የትግል መድረክ ሆኖ ለመውጣት ለውጡን የሚመጥን የአመራር ስምሪት መስጠት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን ብቸኛው የለውጥ አማራጭ መሆኑን በመግለፅ አደረጃጀቱ የአዲስ አበባ ወጣቶችን የስነ ልቦና እድገት ያማከለ የወጣቶች መሰባሰቢያ ጥላ ለመሆን መስራት እንደሚጠበቅበትና በወጣት ዘርፍ ተግባራት ላይ በተለየ ተነሳሽነት መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ የስራ አስፈጻሚ አመራር ኮሚቴ በአፅንዖት በመገምገም በቀጣይ ወራት ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ተግባራት ላይ በመግባባት መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡

ጥር 06 2011ዓ.ም