የኦዴፓ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ሊካሄድ ነው

በሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

በዚሁ መሰረት የኦዴፓ ወጣቶች ሊግ ከጥር 14-17 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን የወጣቶች አንድነት ለመሰረታዊ ለዉጥ በሚል መሪህ ቃል በአዳማ ከተማ ያካሂዳል፡፡

ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቁ እና የሊግ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ይጀመራል ተብሏል፡፡

4ኛው መደበኛ ጉባኤ በ3ኛው መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፡፡

በዚህም ጥንካሬዎች የሚጎለብቱበትንና እጥረቶች የሚታረሙበትን አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡
በመጨረሻ አራተኛው የኦዴፓ ወጣቶች ሊግ ጉባዔ አዳዲስና ለውጥ ፈላጊ የተማሩ ወጣቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት/በማቀላቀል የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

ድልና ድምቀት ለኦዴፓ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ