"የእንን ኣደረሳቹ መልእክት!!"

ከሁሉ ኣስቀድሜ ለሁሉም የኢህኣዴግ ወጣቶች ሊግ ኣባላትና ደጋፊዎች በሙሉ ለ4ተኛ ግዜ የሚከበረውን የኢህኣዴግ ወጣቶች ሊግ መደበኛ ጉባኤ እንካን በሰላም ኣደረሳቹ ኣደረሰን ስል በራሴና በህ.ወ.ሓ.ት ወጣቶች ሊግ ስም ልገልፅላቹ እወዳለሁ።

      የኢህኣዴግ እህት ድርጅቶች ከትጥቅ ትግሉ ወቅት ጀምረው ኢህኣዴግ የሚለውን የጣምራ ስም ኣንግበው በትጥቅ ትግሉ ወቅት ታሪክ የሰሩ፣ ከትጥቅ ትግሉ ማግስትም ሃገሪቱን የመምራት ሃላፊነት ተረክበው የብሄር ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች መነሃርያ የሆነችውን ሃገራችን በፈጣን የእድገት ጎዳና እንድትጋዝ ከሌሎች ኣጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የየራሳቸው የማይተካ ኣሻራ ያኖሩ እህትማማች ድርጅቶች ናቸው። የኢህኣዴግ ወጣቶች ሊግም ከዚ በፊት 3 ጉባኤዎች በተሳካና ባማረ መልኩ ኣሳልፎ እነሆ ኣሁን ለ4ተኛ ግዜ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ያሁኑ ጉባኤያችን ከሌሎች ጉባኤዎች ለየት የሚያደርገው ሃገራችን በጎ ገፅታዋ የሚያጎድፉ የመፈናቀልና ብጥብጥ ኣደጋዎች ኣንዣብቦውባት በሚገኙበት ወቅት በመካሄዱ ነው።

     ድርጅታችን ኢህኣዴግ ከጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴው ማግስት የኣመራር ለውጥ ኣድርጎ ብቅ ባለበት ወቅት ተስፋ ሰጪ ለውጦች ቢመዘገቡም እነኚህ ለውጦች ህገ-መንግስታዊ ኣካሄድን በጠበቀና ቀጣይነት ባለው መልኩ ከማስኬድ ኣካያ ብዙ ችግሮች እየታዩበት ይገኛሉ። ከዚህም በመነሳት እቺ ወደ ስመ-ገናናነት እየተጋዘች የነበረች ሃገር በኣሁኑ ሰኣት በሃገሪቱ የተለያዩ ኣካባቢዎች የብጥብጥ እና መፈናቀል ኣደጋዎች ተጋርጠውባት ይገኛሉ። በዚህም የችግሮቹ ገፈጥ ቀማሽ እየሆነ ያለው ወጣቱ የህ/ሰብ ክፍል መሆኑ ሁላችንም እያየነው ያለነው ሃቅ ነው። ስለዚ እኛ ወጣቶች ከስሜታዊነት ወጥተን ነገሮችን በምክንያት የምንተገብር እና እጃችንን ወደ ሌላ ከመቀሰር በፊት የራሳችን ችግር በራሳችን የመፍታትና እርስ በርሳችን የመከባበር ባህላችንን ጠብቀን መጋዝ ይጠበቅብናል እላሎህ።

    በመጨረሻ በዚ 4 መደበኛ ጉባኤያችን ኣባሎቻችንና ሰፊው የሃገራችን ወጣቶች ነገሮችን ኣብጠርጥረው በመለየትና ምክንያታዊ ሆኖ በመንቀሳቀስ ከኣሉባልታ ወሬዎች ራሳቸውን በማራቅ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ጉባኤ ሆኖ እንደሚቃጭ ተስፋ እያደረግኩ ኣሁንም በድጋሜ እንካን ኣደረሳቹ ኣደረሰን ለማለት እወዳለሁ።

ኣማኑኤል ብርሃነ

የህ.ወ.ሓ.ት ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር