ዜና ዜና

ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ሊቀ መንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኦዲፒ 29ኛ ዓመት የምስረታ ባስተላለፉት መልዕክት የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል።

ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም ከአዲስ አበባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ  ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ከራሷ ዜጎች በዘለለ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምትበቃ በመሆኗ ይህንን ከግምት ማስገባት መልካም ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ኦዲፒ ኅብረተሰቡ ከመልማት ፍላጎት ጋር በተያያዘ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች በማዳመጥ ፤ይቅርታ በመጠየቅ እና በጥልቅ ተሃድሶ ጉዞን በማደስ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን  አስታውቋል።

የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዘራፊዎች ላይ በተወሰደው ሕጋዊ እርምጃዎች እና በክልሉ በተጀመረው የኢኮኖሚ አብዮት በሕዝቡ ዘንድ ተስፋ ማድረጉን ተገልፃል፡፡ እንዲሁም የሕግ የበላይነትና ሰላምን ለማረጋገጥ  እየተወሰደ ባለው እርምጃ በክልሉ ውስጥ አስተማማኝ ሰላም እየተረጋገጠ መምጣቱን ተመላክቷል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ እና ሁሉም ሀገሪቱ ህዝቦች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በጥናት ላይ በመመስረት እንደ ቅደም ተከተላቸው ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የጀመራቸውን የለውጥ ስራዎች ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኦዲፒ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ደስታቸውን እና የሚያጋጥሙ ችግሮቻቸውን ወንድማቸው ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጋር አብረው ታግለው ያሳለፉ መሆኑን መጥቀስ የኦሮሞ ህዝብ እና ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ወንድማማችነትና አብሮነት እንዲሁም ችግሮችን በጋራ የመፍታት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠንካራ አቋም አላቸው፤ ለዚህም በቁርጠኝነት ይሰራሉ ብሏል ኦዲፒ።

እርስ በእርስ በመደማመጥና በመወያየት ለሕዝባችን ምሳሌ በመሆን ለአገር ግንባታ በጋራ እንስራ ሲል ለኢህአዴግ እህት እና አጋር ድርጅቶች መልዕክት አስተላልፏል፡፡

 

 

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.