ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡

ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጽ/ቤቱ ገልፀዋል::

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.