ወጣትነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ!

(ዘላለም መንግስቴ)

በሀገራችን በተለያዩ መስኮች የወጣቶች አሻራ ደምቆ ይታይል፡፡ በተለያዩ የመሰረት ልማት ግንባታዎች፤ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ሀገርን ከጠላት በመጠበቅ ረገድ ወጣቶች የማይተካ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በመጫወትም ላይም ይገኛሉ፡፡  

 በሀገራችን በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ይመረቃሉ፡፡ከእነዚህ መካከል   የቀሰሙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን በማበርከት በአካባቢው ባለው ቁሳቁስ በመጠቀም በቀላሉ ወደ ምርት መጠቀም ለማስቻል ጥረት የሚያደርጉ አሉ፡፡ በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችን ዜጎች የሥራ የፈጠሩ አሉ፡፡ አገራችን በድህነት ውስጥ ያለች  እንድመሆኗ መጠን ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማድረግ የስልጣኔ ምንጭ የሆኑትን አክሱምና የላሊበላን የህንጻ ጥበብ እውቀት እንደገና ለመመለስ  ለበርካታ በሽታዎች የፈውስ መድሃኒት የፈጠሩ፤ በስነ-ፈለክና ስነ-ከዋክብት የመጠቁ እውቀት ባለቤት የሆኑ አባቶችን አርእያ የሚከተለው ወጣቶችን ያንን የሥልጣኔ ማማ ለመመለስ የሚተጉ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተለያዩ ወቅቶች ከተካሄዱ የሳይንስና የፈጠራ ውድድሮች መገንዘብ ይቻላል፡፡

በክረምት የዕረፍት ወቅቶች ወጣቶች የሚያከናውንዋቸው የበጎ ፈቃድ ስራዎችም ሌላው ሊበረታታ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡የእረፍት  ጊዜያቸውን ለአገራቸውን አንድ እርምጃ ከፍ እንድትል በማሰብ እና ሌሎች  ይህን አርእያ  እንዲከተሉ ያላቸውን እውቀት፤ ክህሎት እና ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ በነጻ  በበጎነት ሥራዎች ላይ በመሰማራት በርካታ ወጪዎችን በማደን የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ጊዜያቸውን በአግባቡ የማይጠቀሙ እና ዓላማቸውን ከማሳካት ይልቅ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ወርቃማውን የወጣትነት ዘመናቸው የሚያባክኑ ወጣቶች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ አልለፍ ሲልም

የራሳቸውን ጥቅም ለማስበቅ ሲሉ በሚራራጡ የፓለቲካ ጥቅመኞች ተታለው እና ያለውነ የሥራ አጥነት ሁኔታ እንደመልካም  አጋጣሚ በመጠቀም ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ በመሆን ለጥፋት ተልዕኮ የሚሰማሩም አሉ፡፡  በዚህ በርካታ የሰው ህይወትና የንብረት መውደም አደጋ ይከሰታል፡፡ አገሪቷን ለተጨማሪ ኪሳራ ይዳርጋታል፡፡

በመሆኑም በመጪውዘመን ወጣቶች በሀገራቸው ሰላምና ልማት የበለጠ አስተዋጽኦ እምንዲኖራቸው መስራት ይገባል፡፡ መንግስት የስድራ ዕድሎችን ለማስፋት የጀመራቸው ጥረቶች አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት፡፡ የወጣቶችን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የበለጠ መስራት ይገባል፡፡ አዲሱ ዓመት ያለፉትን መጥፎ ባህሪያተ የምናስተካክልበት፤ የጀመርናቸው መልካም ሥራዎችን አጠናክረን የምንቀጥልበት፤ በህይወታችን ማሳካት የምንፈልጋቸው ነገሮች ለማሳካት ቃላችንን ማደስ አለብን፡፡

ስለዚህ ወጣቶች ያላቸው እውቀት ፤ጉልበት እና ክህሎች በመጠቀም አገራችን ካለችበት የእድገት ደረጃን ወደ ተሻለ ምዕራፍ  ለማሻገር እንዲሁም መጥፎ ባህሪያት ወደ ጎን ትተው በአደስ አስተሳሰብ ለአዳዲስ ድሎች የምንዘጋጅበት ጊዜ መሆን ይገባል፡፡ አገራችን በምታካሂዳቸው የልማት መርሃ ግብሮች የበኩላችንን ሚና በመወጣት ታሪክ ሰርተን ለቀጣዩ ትውለድ ማስተላለፍ አለብን፡፡ ያለፉትን ስህተቶች ነቅሰን የምናወጣበትና መፍትሄ የምንሰጥበት ዓመት እንዲሆን እንዘጋጅ፡፡