ዜና ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ፓርቲው ከግንባር ወደ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ ዛሬ አርብ 24/4/2012 የመጀመሪያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እያካሄደ ነው፡፡
በስብሰባውም የተለያዩ ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔዎች ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክክር ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል ብዘሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገትን መሰረት ያደረገው የ10 አመቱ መሪ እቅድ እና የምርጫ 2012 ስትራቴጂ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ወቅታዊ የሀገሪቱ ሰላም ሁኔታዎች ላይም በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.