Back

የቻይና ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋንቻኦ በኢትዮጵያ ይፋዊ ስራ ጎብኝት እያካሄዱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ እና የቻይና ህዝብ ኮሙኒስት ፓርቲ /ሲፒሲ/ የትብብር ስምምነት ነገ ይፈራረማሉ፡፡
ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝነት ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሰላኝ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሁለትዮሽ ውይይቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ለማስፋፋት የሚውል የብድር ስምምነትና የባቡር አካዳሚ ለመገንባት ከቻይና ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል፡፡
ጉብኝቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙተቶችን ከማጠናከሩም ባለፈ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በነገው እለትም በኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ከኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በፓርቲ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱና ሲፒሲን በመወከል የፓርቲ ለፓርቲ ትብብር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ተገልጾል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ የኢትጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባርና የቻይና ህዝብ ኮሙኒስት ፓርቲ በጋራ ያዘጋጁት ሴሚናር ላይ እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመርና የኢስተርን ኢንዳስትሪ ዞንን በመጎብኘት በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ቆይታ የሚጠናቅቁት ምክትል ፕሬዚዳንቱ  በኢትዮጵያ አየር መንገድ በራር አርብ ጠዋት ወደ ጆሃንስበርግ ያቀናሉ፡፡

 


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።